TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተ የዝናብ እጥረት የተነሳ ድርቅ በሰው እና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳው ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል ተብሏል። በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት…
በሐመር እንዲህ እየሆነ ነው ...

የሐመር ወርዳ የግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ሼላ የተናገሩት ፦

" የአርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ በወረዳ ደረጃ የወይጦ ወንዝን በመተማመን ሠፊ ጥረቶች ተደርገው በኤርቦሬ ጓንዶሮባ፣ ጨርቀቃና ዘገርማ በርካታ የጓሮ አትክልቶችን እንደሙዝና የመሳሰሉትን ተተክለው ፍሬ በመስጠት ላይ ነበሩ።

ነገር ግን የወይጦ ወንዝ ሙሉ በሙሉ #በመድረቁ ምርት ሊሰጡ የደረሱ ሙዞችና በአስሌ ሬቦ መንደር በዘር ተሸፍኖ የበቀለው የቆላ ስንዴ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በሕይወት የቀሩ የቤት እንስሳት ሰውነታቸው አልቆ አጥንታቸው ቆዳቸውን እየገፋ ነው።

በየጥሻው የቀሩ የቤት እንስሳት የሐመር አርብቶ አደር የኑሮ መሠረት ነበሩ።

ውኃ የጠማቸው፣ መኖ የቸገራቸው የቀንድ ከብቶች በኦሞ ሸለቆ ለሚኖረው አርብቶ አደር ብቸኛ ጥሪት ናቸው።

በድርቁ ሰለባ የሆኑት አርብቶ አደሮች መንግስት እንስሳቱን የሚታደግ እርዳታ እንዲያቀርብላቸውና ቀሪዎቹ እንስሳት ተርፈውልን እኛም ከእነሱ የሆነ ነገር እያገኘን ራሳችንን የምናተርፍበት ሁኔታ ቢፈጠር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አርብቶ አደሮቹ ለእንስሳት ሣርና ግጦሽ ማግኘት አይችሉም። ይኸንን መነሻ አድርገው መኖ የሚቀርብበት መንገድ እዲመቻችላቸው፤ ውኃ እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል። እንስሳት ቢሞቱ እንኳን የሰው ልጅ ውኃ የሚያገኝበት ሁኔታ ቢመቻችልን በማለት አቤቱታቸውን ለመንግስት አቅርበዋል። "

ከሐመር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#ቲክቶክ

ካናዳ ከዛሬ ጀምሮ መንግሥት በገዛው ‘ኤሌክትሮኒክስ’ ቁሳቁስ #ቲክቶክ መጠቀም ክልል መሆኑን አሳውቃለች።

በዚህ ሳምንት መንግሥት ገዝቶ ለሠራተኞች ካደላቸው ተንቀሳቃሽ ስልኮች ውስጥ ቲክቶክ ይጠፋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ መተግበሪያው ለመረጃ ደኅንነት አስጊ እንደሆነ ጠቋሚ ፍንጮች ስላሉ ነው ውሳኔው የተላለፈው ብለዋል።

የቲክቶክ ቃለ አቀባይ በካናዳ መንግሥት ውሳኔ ኩባንያው እንደተከፋ ገልጠዋል።

ቲክቶክ ይህን ውሳኔ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የካናዳ መንግሥት ኩባንያውን ሳያማክር አሊያም በቂ ማስረጃ ሳይኖረው ይህን ማድረጉ አሳዛኝ መሆኑን ገልጧል።

* የአውሮፓ ኮሚሽን

ከቀናት በፊት የአውሮፓ ኮሚሽን ተመሳሳይ ውሳኔ አሳልፏል። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ሠራተኞች ከመጋቢት 15 ጀምሮ ቲክቶክን በኮሚሽኑ ንብረት መጠቀም አይችሉም ሲል ነው ውሳኔ ያሳለፈው።

* አሜሪካ

ባለፈው የፈረጆቹ ዓመት የአሜሪካ የፌዴራሉ መንግሥት ሠራተኞች ቲክቶክን እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል።

ትላንት ዋይት ሐውስ የመንግሥት መ/ቤቶች በሚቀጥሉት 30 ቀናት ከኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎቻቸው ቲክቶክን #እንዲያስወግዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በርካታ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መተግበሪያውን ከኔትዎርኮቻቸው ላይ አስወግደውታል።

* ሕንድ

ሕንድን ጨምሮ በሌሎች የእስያ ሃገራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቲክቶክ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰዱ ነው።

#ቲክቶክ

ቲክቶክ ባይትዳንስ የተሰኘው ኩባንያ ንብረት ነው።

መተግበሪያው ግላዊ መረጃን በመበዝበዝ ከፍተኛ ወቀሳ የሚደርስበት ሲሆን ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው በሚልም ስሙ ይነሳል።

ኩባንያው የቻይና መንግሥት መረጃውን እንደማያገኝበትና ቻይና ያለው ቲክቶክ ከሌላው ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ደጋግሞ አሳውቋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ ለመላክ አስበዋል?

ቪዛ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው በካሽጎ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

ነፃ፣ ምቹ እና ቀላል፡፡

የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች 👇
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306
#CashGo #visa #mastercard #የሁሉም_ምርጫ
" 100 ሚሊዮን ብር ለግሻለሁ " - የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ የቦረና ወገኖቻችን 100 ሚሊየን ብር መለገሱን አሳውቋል።

ባንኩ በላከው መልዕክት ፤ ከሠራተኞቹ ጋር በመሆን የማህበረሰብ ተቆርቋሪነት እሴቱን እየኖረ እንደሆነ ማሳየቱን መቀጠሉን ገልጿል።

@tikvahethiopia
" መምህራን ከ20 ወራት በላይ የያለደሞዝ መቆየታቸው ኑሯቸውን ከባድ አድርጎታል " - አመማ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ከትግራይ ክልል መምህራን ማህበር ጋር በመቐለ ወይይት ማድረጉን አሳውቋል።

ዶክተር ዮሐንስ በንቲን ጨምሮ ሁለት  የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚዎች ወደ መቐለ በማምራት ከክልሉ መምህራን ማህበር አመራሮች ጋር ዉይይት እንዳደረጉ ማህበሩ ገልጿል።

የውይይቱ ዋና አላማ በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት ምክንያት ላለፉት ሁለት አመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት ለማስቀጠልና አጋርነታቸውን ለመግለፅ ነው ተብሏል።

ማህበሩ በውይይቱ ወቅት ባጋጠመው ጦርነት ምክንያት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፈጠራቸውን መረዳት እንደተቻለ ገልጿል።

በተለይም ደግሞ መምህራን ከ20 ወራት በላይ የያለደሞዝ መቆየታቸው ኑሯቸውን ከባድ አድርጎታል ብሏል።
       
የክልሉ የማህበር አመራሮች ኢመማ በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት አጋርነቱን ለማሳየት በመምጣቱ ልዩ ትርጉም እንደሚሰጡት መግለፃቸውንና ችግሩ በተፈጠረበት ወቅት ከክልሉ ተፈናቅለው አዲስ አበባ ለመጡ ከ30 በላይ መምህራን የአቅሙን ድጋፍ ማድረጉን እንዳመሰገኑ ተገልጿል።

ከምንም በላይ ደግሞ በክልሉ የነበረው ችግር በጠመንጃ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈታ ማህበሩ አቋሙን በተለያዩ ሚድያዎች በሰጠው መግለጫ በማሳወቁ መደሰታቸውን አስታውሰው በተግባር የታየውም ይሄው በመሆኑ " ክብር ተሰምቶናል " ማለታቸውን ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን የሚያዘጋጀው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ሽልማት ማደጉን አስታወቀ።

3 ብር የነበረው የአንድ ዕጣ ቁጥር ዋጋ 5 ብር ማደረጉም ተመላክቷል።

በ1ኛ ዕጣ 1,500,000 ብር ያሸልም የነበረው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ1ኛው ዕጣ ወደ 3,000,000 ብር መደጉ 2ኛው ዕጣ ደግሞ 1,200,000 ብር፣ 3ኛ ዕጣ 800,000 ብር መደረጉ ተመላክቷል።


አዲሱ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ ድልድል ዝርዝር የሚከተለው ነው ፦

1ኛ ዕጣ 👉 3,000,000
2ኛ ዕጣ 👉 1,200,000
3ኛ ዕጣ 👉 800,000
4ኛ ዕጣ 👉 400,000
5ኛ እጣ 👉 250,000
6ኛ ዕጣ 👉 150,000
7ኛ ዕጣ 👉 100,000
8ኛ እጣ 👉 50,000
9ኛ እጣ 👉 30,000
10ኛ እጣ 👉 25,000

በሌላ በኩል ፤ ሎተሪ አስተዳደሩ የ008- መደብ ሽያጭ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2015 ከለሊቱ 6 ሰዓት እንደሚያበቀ የገለፀ ሲሆን ከዚህ ሰዓት ጀምሮ የቀጣይ ወር ዕጣ ይጀመራል ብሏል።

የ008- መደብ ዕጣ የካቲት 23 ቀን 2015 በህዝብ ፊት ይወጣል ሲልም አሳውቋል።

አዲሱ የዕጣ ድልድል የሚጀምረው ከቀጣይ ወር / ከየካቲት 21 ቀን 2015 ከለሊቱ 6ሰዓት ላይ ከሚጀምረው ዕጣ ይሆናል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የካቲት 23/2015 ዓ.ም የሚከበረውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ ማለዳ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ #የሚዘጉ_መንገዶች

የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ በ #ምኒሊክ_አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር ስነ ስርዓቱ እንደሚጀምር ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል ወደ አድዋ ድልድይ የእግር ጉዞ እንደሚደረግና ዋናው ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም ፦

👉 በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነው የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት ፦

• ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ
• ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡

👉 ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነው ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

• ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ
• ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ
• ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ #ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

👉 በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ
• ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር
• አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር
• ከገነት መብራት ወደ ለገሀር
• ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ
• ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ
• ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ
• ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ
• ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት
• ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች #ሌሎች_አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

ከነገ እሮብ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን #አቁሞ_መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እና ት/ቤቶች እውቅናና ሽልማት ሊሰጥ ነው። ሚኒስቴሩ በ2014 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች ሀገር አቀፍ እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ አሳውቋል። የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ የፊታችን የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚካሄድ ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው። @tikvahethiopia
#Update

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች ተሸለሙ።

በዛሬው ዕለት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እና ትምህርት ቤቶችን መሸለማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia