TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች ተሸለሙ። በዛሬው ዕለት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን እና ትምህርት ቤቶችን መሸለማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የፎቶ ባለቤት ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት @tikvahethiopia
#Update #UAE

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በምስራቅ ሀረርጌ  ዞን የተከሰተው ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ህጻናት አድን ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በዞኑ ውሃ ፤ የጤናና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንደሚያስፈልጉ አሳውቋል።

የኢትዬጵያ ህጻናት አድን ድርጅት የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ አብዱራዛቅ አህመድ  " የተከተሰው ድርቅ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ በመሆኑ በ35 ወረዳዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው " ብለዋል።

ድርጅቱ ከ2 መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ለተማሪዎች  ምገባ እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

በድርቁ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ በድርቁ ከ2 ሚሊየን በላይ እንስሳት እስካሁን መሞታቸውን አንስተዋል፡፡

ቦረና ላይ ከተከሰተው ድርቅ ባልተናነሰ በምስራቅ ሀረርጌም በዜጎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጸው በዚህ ምክንያት ግን እስካሁን የሞተ ሰው ስለመኖሩ ያገኙት መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ድርቁ ነአርሶ አደሩ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ዝናብ ካልዘነበ አሁንም በዞኑ ያለው ችግሩ እየተባባሰ እንደሚመጣ አመልክተዋል።

በዞኑ ካለው ችግር፤ አንፃር የሚደርሰው እርዳታ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ ድርጅቱ ቦረና ላይ ለደረሰው ድርቅ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ ድጋፎችን እያሰባሰበ መሆኑን አሳውቀዋል።

Credit : አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba 🛫 #Mekelle

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ትግራይ መቐለ አቅንተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ዛሬ ወደ መቐለ አቅንተዋል።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው ነው ወደ መቐለ የተጓዙት።

ቅዱስነታቸው ወደ ትግራይ፣ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ መቀበላቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ምንጭ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ መቐለ ገቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት በሰላም መቐለ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው መቐለ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Photo : Social Media

@tikvahethiopia
" ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው "

ከሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ያሳለፈው አዲስ አደረጃጀት በጉጂ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እንደገጠመው የቲክቫህ አባላት ከየአካባቢው አሳውቀዋል።

ትላንት ከዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቦሬ ማቲ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ተሰምቷል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ የሚወስደው የሃይል እርምጃ ሊቆም ይገባዋል " ሲል አሳስቧል።

" በቦሬ ማቲ የምስራቅ ቦረና ዞን አወቃቀርን ተቃውመው ባዶ እጃውን ሰልፍ ወጥተው የነበሩ ሶስት ሰዎች (2ቱ ተማሪዎች ናቸው/ሌላ አንድ ነዋሪ) በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።

" ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃ መቆም አለበት " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል "ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ሲል አሳስቧል።

በዛሬው ዕለት ከአዲሱ አወቃቀር ጋር በተያያዘ በሻኪሶ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የቤተሰባችን አባል ፥ " ክልሉ ውሳኔውን ሲያሳልፍ ከህዝብ ጋር አለመከረም፣ ህዝቡ ውሳኔ እንዲሰጥበትም አልተደረገም " ሲሉ ተናግረዋል።

እስካሁን ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ቡሌ ሆራ እና ሻኪሶ ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የክልሉ ም/ቤት ያሳለፈው የአደረጃጀት ውሳኔ ምንድነው ? በዚህ ያንንቡ https://t.iss.one/tikvahethiopia/76667

@tikvahethiopia
ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች የቀረበ ጥሪ !

የ " ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር " በድርቅ ምክንያት ለጉዳት የተጋላጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከቅርብ አመታት ወዲህ በደቡባዊና ደቡብ ምስራቃዊ አካባቢዎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰውና በእንስሶች ላይ ያስከተለውና እያስከተለ ያለው ጉዳት #እጅግ_አስከፊ መሆኑን ገልጿል።

ማኅበሩ እ.አ.አ በ2022 ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባባር ፦
- በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮና ጋሞ ዞኖች፣
- በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች፣
- በሶማሌ ክልል ሸበሌ፣ ፋፈን እና አፍዴር ዞኖች ከዚህ በተጨማሪ ሞያሌ አካባቢ በድርቅ አደጋ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ 14,530 አባዎራዎችን ህይወት ለመታደግ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በተለይም #በኦሮሚያ እና #ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ሞያሌ አካባቢ በ206.3 ሚሊዮን ብር መሰል ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ድርቁ በሰውም ሆነ በእንስሶች ላይ እያስከተለ ካለው ጉዳት አንፃር እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ማህበሩ የተጎጂዎችን ህይወት ለመታደግ እያደረገ ያለውን ጥረት መላው ኢትዮጵያውያን በአይነትም ሆነ በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

እንዴት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል ?

1ኛ. #የአይነት_ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አዲስ አበባ ስቴዲየም አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መ/ ቤት ግቢ ድረስ በማምጣት መለገስ ይችላሉ።

2ኛ. የገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚፈልጉ በ #ቴሌ_ብር ሂሳብ ቁጥር 0907 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

3ኛ. ለቦረና ድርቅ ምላሽ ተብሎ በተከፈት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 👉 1000529766916 እንዲሁም 907 አጭር የሂሳብ ቁጥርን በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በዳሽን ባንክ፤ በአቢሲኒያ ባንክ፤ በአዋሽ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

4ኛ. የእጅ ስልክ በመጠቀም በ9400 ላይ OK ብሎ በመላክ 1 ብር መለገስ ይቻላል።

#EthiopianRedCrossSociety
#ETHIOPIA🇪🇹

@tikvahethiopia
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia