TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Olusegun_Obasanjo ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ አፈላላጊው ሰው - ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ! በአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲፈታና ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ኦባሳንጆ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ ነበር፤ ከኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም…
#OlusegunObasanjo

የአፍሪካ ህብረት የጸጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በህብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ ገለጻ እንደተደረገለት አል ዐይን በድረገፁ አስነብቧል።

ህብረቱ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ ስብሰባው በበይነ መረብ የተካሄደ እንደነበር ተገልጿል።

በስብሰባው ላይ ፦

• የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ፣

• የህብረቱ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆ፣

• በአፍሪካ ህብረት የግብጽ ቋሚ ተወካይ መሃመድ ጋድ እና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተሳትፈዋል፡፡

ስብሰባው የተካሄደው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምክርና የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆን ገለጻ ለማድመጥ ነበር፡፡

በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከመከረና የኦባሳንጆን ገለጻ ካደመጠ በኋላ ያለው ወይም ያስቀመጠው ቀጣይ አቅጣጫ እንዳለ የታወቀ ነገር የለም፡፡

ነገር ግን ም/ ቤቱ የተሰበሰበበትን ጉዳይ የተመለከተ መግለጫን እንደሚያወጣ መረጃ እንዳለው አል ዓይን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OlusegunObasanjo

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ።

ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው ዝርዝር ነገር የለም።

በሌላ በኩል ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት በሚያደርጉት ጥረት ተልዕኳቸውን አልቀበልም ያለ አካል እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ይሁን በትግራይ ክልል ያሉ አካላት እሳቸውን አልቀበልም ያለ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጆ ፥ "የአፍሪካ ሕብረት ሰላም ለማምጣት፣ ንግግርን ለማስጀመር እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ልዩ መልዕክተኛ መሰየሙን ሁሉም ወገን በበጎ ነው የተቀበሉት" ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፥ "የጠየቅኩትን ትኩረት ሰጥተውኛል። በሚገባው ልክ አስተናግደውኛል" ሲሉ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ገልጸዋል።

ትግራይ ክልል ሲሄዱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ኤርፖርት ድረስ ሄደው እንደተቀበሏቸው ገልፀዋል።

ሁለቱም ወገኖች የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆን "አልተቀበሉንም የሚለው ሐሳብ ፍጹም ስህተት ነው" መሆኑን አሳውቀዋል።

አሁን ላይ የድርድሩ ሂደት ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ የሚፈጠረውን ጉዳይ በተመለከተ ኦባሳንጆ ፤ "አሁን ገና የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ነኝ። ድርድሩ ወዴት እንደሚሄድ የምናገርበት ጊዜ አይደለም" ብለዋል።

አሁን ያሉበት ደረጃ በተደራዳሪ ወገኖች ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ምን እንደሆነ የመለየት እንደሆነም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OlusegunObasanjo በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ። ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም። ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው…
#OlusegunObasanjo

ትናንት በወቅታዊ የአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስበስባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ ስላሉ የሰላም ጥረቶች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በአዲስ አበባ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጥረቱን ለማርገብ እና ለቀጣይ ውይይቶች ምቹ መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችል ፍሬያማ ንግግር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተነጋገሩና ወደ ትግራይ እንዲያቀኑ ከተስማሙ በኋላ እሁድ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመቐለ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔልን ጋር ተገናኝተው ውጥረቱን ለማርገብና አመርቂ መፍትሄዎችን ለመፈለግ የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በሰሜን ያሉ ሁሉም መሪዎች በመካከላቸው ያለው ችግር ፖለቲካዊ እንደሆነና በውይይት ሊፈታ የሚችል ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ በግለሰብ ደረጃ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ችግሩ የከፋ ማህበረ ምጣኔ ሃብታዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን በመጠቆም ዘላቂ እልባት ለመስጠት መፍጠን እንደሚያስፈልግ ኦባሳንጆ ተናግረዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመጡ፣ ያልተቆራረጠ የሰብዓዊ እርዳታዎች አቅርቦት እንዲኖር፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርግና ሁኔታዎችን በአንክሮ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopoa
#OlusegunObasanjo

ኢትዮጵያ 🇪🇹 " ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ " ለሚለው መርህ ባላት እምነት እና ቁርጠኝነት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለሚያደርገው ጥረት አክብሮት እንዳላት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ፡፡

ቢልለኔ ይህን ያሉቱ ከCGTN አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ተገኝተው ሰላምን ስለማምጣት የተወያዩት የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን አባሳንጆ በአፍሪካ ህብረት የተወከሉ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ችግሮችን ለመፍታት ስላለው ውሳኔ ኢትዮጵያ አክብሮት እንዳላት ገልፀው፤ ኦባሳንጆ በትልቅነታቸው፣ በአገር መሪነታቸውና የተለያዩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት ትክክለኛ ውክልናና ጥረታቸውም እንደሚሳክ እናምናለን ብለዋል፡፡

Credit : #CGTN #ENA

@tikvahethiopia
#JustinTrudeau #OlusegunObasanjo

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ልዩ መልዕከተኛው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ እና በሁሉም አካላት መካከል ውይይት እንዲፈጠር ለማበረታታት የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።

ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በአፍሪካ መሪነት ለሚደረገው የሽምግልና ጥረቶች ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ እና ካናዳ በዚህ ረገድ የአፍሪካ ህብረትን ስራ ለመደገፍ ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች ያለ ምንም እንቅፋት ሰብዓዊ ዕርዳታ በማድረስ ሂደት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሰላማዊ ዜጎችን መጠበቅ፣ ህይወት ማዳንና የሰብአዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia