TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoHETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ ስጋት አንዳንድ የጤና ተቋማት መደበኛ የህክምና አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም ሳቢያ እናቶች በቤት ውስጥ እንዲወልዱ ሆኗል፤ በህክምና ሊድኑ በሚችሉ በሽታዎች የሰው ህይወት እያለፈ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ እንዳስታቀው መንግስት የኮቪድ-19 ህክምናን ብቻ የሚሰጡ ተቋማትን ስለለየ ሌሎች የህክምና ተቋማት መደበኛ የህክምና ስራቸውን ከዚህ ቀደሙ በበለጠ ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጿል።

በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት የህክምና ተቋሞቻቸውን የዘጉ እንዳሉም የገለፀው ሚኒስቴሩ፥ ተግባራቸው ትክክል እንዳልሆነ እና በፍጥነት ሁሉም ክፍት እንዲሆኑ አሳስቧል።

የተሟላ የህክምና አገልግሎት በማይሰጡት ላይ የህግ ተጠያቂነት እንደሚኖርም አስታውቋል።

ማህበረሰቡም ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተሳሰተ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ጤና ተቃማት እየሄደ እንደማይገኝ የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ይህ ትክክል እንዳልሆነም አስገንዝቧል።

በአሁኑ ወቅትም መደበኛ የህክምና አገልግሎቶች በአግባቡ እንዲሰጡ ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ግብረ ሀይል ተቋቆሙ ወደ ስራ መገባቱንም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoHETHIOPIA

‘ፕሮጀክት ሆፕ’ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የፊት ጭምብሎችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ።

ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ድርጅቱ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ አገሮች ቅርንጫፎችያሉት ሲሆን፤ 56 ሺህ “ኤን 95” የተባሉትን ጭምብሎች ለግሷል።

ጭብሎቹ ሙሉ በሙሉ ኮሮናን በመከላከል ላይ ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የሚውሉና በሕክምና ተቋማት ብቻ እንደሚለበሱ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ ዶ/ር ዳዊት አብርሃም ድጋፉን ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ አስረክበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 20,770
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 2,016
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 0
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 59
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 3
• አጠቃላይ ያገገሙ - 69
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 133

#DrLiaTadesse #MoHEthiopia #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoHEthiopia

የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ከ03/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው።

ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ ነው ተብሏል።

አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ መስተዋሉ ተገልጿል ።

በመሆኑም ወጥ በሆነ ጋይድ ላይንና ቼክሊስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል ይጎበኛሉ ድጋፍም ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ይህ ድጋፋዊ ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን ይኖርበታል ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ!

መደበኛ 24 ሰአት ዕለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ለ #MoHEthiopia በደረሰው አዲስ መረጃ መሰረት በሃረሪ ክልል በተደረገ 12 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የ37 ዓመት የሀረር ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌለው ነው።

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoHEthiopia

ዴክሳሜታሰን (Dexamethasone) መድሃኒት በኮቪድ-19 በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታደግ ይረዳል መባሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጥናቶችና ምክሮችን እያሰባሰበች መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ለኤፍ ቢ ሲ /FBC/ እንደተናገሩት ፥ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ነዉ ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ጤናን በሚመለከት የተለያዩ አማካሪ ቡድኖች ጋር ይሰራል ያሉት ሚኒስትር ዴታዋ ፤ ከኮቪድ-19 በሀገሪቱ መከሰት በኋላም ይህ ከሀገር ውስጥና ዲያስፖራን በማካተት የሚሰራው አማካሪ ቡድንም የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የ“ዴክሳሜታሰን” መድሃኒት ጉዳይም መሆኑን በመግለፅ ፤ በጉዳዩ ላይ ሚኒስቴሩን የሚያማክሩ ቡድኖች ክትትል እያደረጉ ነው ብለዋል።

ቡድኑም በመድሃኒቱ ላይ እያደረገ ያለውን የጥናት ውጤት እስከ ዛሬ ምሽት ለሚኒስቴሩ የሚገለጽ መሆኑን በመጥቀስ፤ በቀጣይነት ለህብረተሰቡ ይፋ ይደረጋል ነዉ ያሉት።

እስከዛው ግን ህብረተሰቡ አላስፈላጊ ወጪ ከማውጣት በመቆጠብ የጤና ሚኒስቴር መግለጫን እንዲጠባበቅ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ 100 ቀናቶች!

#EPHI እና #MoHEthiopia ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ላለፉት 100 ቀናት (ከመጋቢት 4-ሰኔ 14) መጠነ ሰፊ የሆኑና በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።

የተሰሩ ስራዎችን እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦

- 216,328 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)

- 4,532 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)

- ንክኪ ያላቸው 31,573 ሰዎች ተለይተው 708 ሰዎች የኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል

- ለ764,948 ተጓዦች ልየታ እና ክትትል ተደርጓል (ከጥር 15 ጀምሮ)

- 32 ሚሊዮን ሰዎች በቤት ለቤት ዳሰሳ ታይተዋል

- 13,859 የማከምያ አልጋዎች ተዘጋጅተዋል

- ከ4,500 በላይ ተጨማሪ የጤና ባለሞያዎች ተቀጥረዋል፤ 12,000 በጎ-ፍቃደኞች ተሰማርተዋል

- 513 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግል መከላከያ ቁሳቁሶች (PPE) በሃገሪቱ ተሰራጭተዋል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoHEthiopia

ከነገ ነሐሴ 1/2012 ዓ/ም እስከ ነሃሴ 17/2012 ዓ/ም ‹‹ማንም›› የተሰኘ የኮቪድ-19 ምርመራ ዘመቻ ይካሄዳል።

የዚህን ዘመቻ ምርመራ ውጤት ተከትሎ በኢኮኖሚው በኩል አገልግሎት የሚሰጡ የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳሕርላ አብዱላሂ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የበሽታው ስርጭት በማያስፋፋ መልኩ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ ብለው ባለሙያዎች በሚሰጡት መመሪያ መሰረት ወደ ስራ የሚገቡት የአገልግሎት ዘርፎች እንደሚሊዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CHINA  🇨🇳 #ETHIOPIA 🇪🇹

በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ እና ይበልጥ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ቻይና ለገሰች።

በዛሬው እለት ክትባቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥያዎ ዢዮዋን ለዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ይህ ከቻይና መንግስት ለሶስተኛ ግዜ ድጋፍ የተደረገው 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በዋናነት በስራቸው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ይውላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ ድጋፉ ካለው የኮቪድ-19 ህሙማን መብዛትና የኮቪድ-19 ስርጭት መበራከት ጋር ተያይዞ ያለውን ጫና ከመቀነስ አንጻር ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ቻይና  🇨🇳 በዛሬው ዕለት የላከችውን 300 ሺህ ዶዝ ክትባትን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 1 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርጋለች፡፡

#MoHEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse " ...እየሞቱ ያሉ ሰዎች መሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ክትባት ያልወሰዱ ናቸዉ"- ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅታዊነት እና ክትባት እዲሁም በመጪው ቀናት የሚከፈቱ ት/ቤቶች ማድረግ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዙርያ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ሊያ በመግለጫቸው፦ -አደገኛው የዴልታ ዝርያ መኖሩ -በየቦታው መሰባሰቦች እና ማስክ…
ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ያስተላለፉት ማሳሰቢያ ፦

" ጊዜው ትምህርት የሚጀመርብት ወቅት እንደመሆኑ ፦ ትምህርት ቤቶችን ዝግጁ ማድረግ፣ መምህራን ክትባት መከተብ፣ ወላጆች ተማሪዎችን በስነልቦና ዝግጁ ማድረግና መከላከያ ዘዴዎችን ማስተማርና እንዲተገብሩ ማድረግ፣ ያለ ማስክ ትምህርት አለመሰጠቱንም መረጋገጥ ከሁሉም መምህራና እና የትምህርት ቤት አመራሮች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ይጠበቃል።

ትምህርት ቤቶች ያላቸውን የተማሪዎች ቁጥር እና የመማርያ ክፍሎችን መጠን (ስፋት) ግምት ውስጥ በማስገባት እርቀታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲሁም አስገዳጅ ከሆነም የፈረቃ ስርዓትን በመተግበር የመማር ማስተማር ሂደት ሊከናወን ይገባል። "

#MoHEthiopia

@tikvahethiopia