TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ThomasSankara

በቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን አስራ አራት ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ከ34 ዓመታት በፊት ነበር የወቅቱ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ " የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የተፈጸመባቸው።

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ሳንካራ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ነው በወታደሮቹ በጥይት ተገደሉት።

እንሆ ከ34 ዓመት በኋላ የቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን 14 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የቶማስ ሳንካራ ግድያን ተከትሎ ፥ የቅርብ ጓደኛቸው ብሌዝ ኮምፓዎሬ ነበሩ ወደ ሥልጣን የመጡት።

ከግድያው ከአራት ዓመታት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ለፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተው ነበር።

ኮምፓዎሬ ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል ናቸው።

በጎረቤት ሀገር አይቮሪ ኮስት በግዞት የሚገኙት ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣን ለቀው ነው የተሰደዱት።

ነገር ግን በቶማስ ሳንካራ ግድያ ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብለዋል። በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኙም አስታውቀዋል።

• የፍርድ ሂደቱ ለምን ረዥም ጊዜ ፈጀ ?
• የፍርድ ሂደቱ በሀገሪቱ ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል ?
#ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/Thomas-Sankara-10-11-2

Credit : BBC

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ_አገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ማቋቋሚያ_አዋጅ_Amhaic.doc
143 KB
#ያንብቡ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ እና የሃሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልዩነት እና አለመግባባት የሚታይ በመሆኑ ይህን ልዩነት እና አለመግባባት ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክሮችን ማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባትን ለመገንባትና በሂደትም የመተማመንን እና በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባህልን ለማጎልበት፣ እንዲሁም የተሸረሸሩ ለማሳለጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

አገራዊ ምክክሮች ተቀባይነት እና ተዓማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ ከሚያስችላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ምክክሮቹን የሚያመቻቸውና የሚመራው አካል ብቃትና ገለልተኝነት በመሆኑ፤ ምክክሮቹን በብቃትና በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ሰፊ ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚህም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሠረት ከላይ የተያያዘው አዋጅ ታውጇል።

ይህ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ለዘመናት የቀጠለውን ያለመግባባት አዙሪት በማስወገድ አገራዊ አንድነት እንደሚያረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበት ተነግሯል።

የህ/ተ/ምክር ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዜጎች ረቂቅ አዋጁን አንብበው ም/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል የሚሉትን ሀሳብ እንዲሰጡ ጠይቋል።

(እንደ ዜጋ ከላይ የተያያዘውን ረቂቅ አዋጅ አንብበው በም/ቤቱ ገፅ https://www.facebook.com/599208023518983/posts/4270721263034289/ ገብተው ሀሳቦትን ያካፍሉ)

@tikvahethiopia
#JawarMohammed

ኦፌኮ በብሄራዊ ምክክር ላይ አልሳተፍም ብሏል ?

አቶ ጃዋር መሀመድ (ምክትል ሊቀመንበር) ፦

" ትንሽ የግንዛቤ ችግር አለ። እኛ እንደ ኦፌኮ አንሳተፍም አይደለም ያልነው ቅድመ ሁኔታዎችን ነው ያስቀምጥነው። ብሄራዊ መግባባት (National Dialogue) የኦፌኮ አጀንዳ ነው።

... ስለዚህ ኦፌኮ የብሄራዊ ድርድርን ወይም የብሄራዊ መግባባትን አይፈልግም የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ነው፤ እንፈልጋለን፤ አሁንም ቢሆን እንፈልጋለን ፤ አሁንም ቢሆን ለሀገራችን የሚጠቅመው እሱ ነው ብለን ነው የምናምነው።

ነገር ግን ብሄራዊ መግባባት ሲባል ፕሮሰስ አለው ፤ ብሄራዊ መግባባት በሁለት ደረጃ ነው በአንድ ሀገር ውስጥ ሊካሄድ የሚችለው።

አንዱ የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ጦርነት እንዳያመሩ የቅድመ ጦርነት ንግግር የሚባል ነው የፖለቲካ ልዩነቶች ፣ የፖለቲካ ሽኩቻዎች ሀገርን እና የፖለቲካ ኃይሎችን ወደ ጦርነት እንዳያስገቡ በንግግር እና በድርድር ለመፍታት የሚደረግ ብሄራዊ መግባባት አንድ አለ፤ ያ ሳይደረግ እድል አምልጦ ሀገር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ ደግሞ ጦርነት ቆሞ ከጦርነት በኃላ ለጦርነት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችም ሆኑ በጦርነት የተፈጠሩ ክስተቶች ለሌላ ጦርነት እንዳይጋብዙ ከስር መሰረቱ ለመፍታት የሚደረግ ክንውን ነው ፤ ይሄን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ብሄራዊ መግባባት በጦርነት መካከል ሊካሄድ አይችልም። ሀገራችን በጦርነት መሀከል ነች፤ 2019/20 መጀመሪያ አካባቢ ቢሆን 2019/18 ጥሩ ጊዜ የነበረው ለውጡ እንደመጣ የመጀመሪያ ወራት መጀመር ነበረበት ያ አምልጧል አሁን ጦርነት ውስጥ ነው ያለነው።

ብሄራዊ መግባባት ሲባል የመጀመሪያው criteria ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አለበት።

በተለይ ጦርነት ከተገባ ፣ ከሁሉም የበለጠ ብሄራዊ መግባባት ውስጥ መግባት እና መሳተፍ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባው በጦርነት ውስጥ የተሳተፉት ቡድኖች ናቸው። ጦርነት እየተካሄደ እነዚህ በጦርነት የተሳተፉ ቡድኖች ማሳተፍ አልቻልም። Legally ሆነ በ Security wise ማሳተፍ አይቻልም። ይህ ስለሆነ ዋናው እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ብሄራዊ መግባባት ጥሩ ነው መንግስት ረጅም ጊዜ አልሰማም ብሎ አሁን የብሄራዊ መግባባት ማለቱ ጥሩ ነው ደስ ብሎናል ነገር ግን ይሄን ነገር በአግባቡ እንስራው ስለዚህ ጦርነት ይቁም ፤ ጦረኞቹ ሙሉ በሙሉ ይታረቁ አይደለም እያልን ያለነው ብሄራዊ መግባባቱ ላይ ሊታረቁ ይችላሉ ነገር ግን active fighting እንዲቆም ማድረግ በሰሜንም ፣ በትግራይ ድምበርም ፣ በቤኒሻንጉልም፣ በኦሮሚያም በተለያየ አካባቢ እየተደረገ ያለው ጦርነት መጀመሪያ መቆም አለበት... "

#ያንብቡ ➡️ https://telegra.ph/Jawar-Mohammed-05-27
#AddisAbaba

የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ !

ከነገ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ የሚኒባስ ታክሲ እና የሚድ ባስ (ሃይገርና ቅጥቅጥ) የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚመለከት ነው።

በሚኒባስ ታክሲ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 6 ብር ድርስ የጨመረ ሲሆን በሚድ-ባስ ላይ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 2 ብር ድርስ ጨምሯል።

የሸገር እና አንበሳ ከተማ አውቶብስ ታሪፍ በዚህ ወር መጨረሻ ይስተካከላል ተብሏል።

ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል #ያንብቡ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia
#ያንብቡ

የገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ የተደረገበት መመሪያ አውጥቷል።

መመሪያው " በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1007/2016 " ይሰኛል።

አዲሱ የተስተካከለ መመሪያ ከከዚህ ቀደሙ ጭምሪ የተደረገበት ነው።

የአልኮል መጠጦች እና የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) ኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ፦

➡️ ከብቅል የተዘጋጀ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ተመርቶ በበቀለ ገብስ የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው 35% ወይም 23 ብር በሊት ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ ውሃን ሳይጨምር ቢያንስ ከክብደቱ 75% የሚያህለው በአገር ውስጥ ግብዓት የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 30% ወይም 21 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ የሚፈሉ መጠጦች (ሲዳር፣ ፔሪ፣ ኦፓክ ቢራ፤ የሩዝ አልኮል መጠጥ)፣ የሚፈሉ መጠጦችና የአልኮል አልባ መጠጦች ድብልቅ፣ ስታውት፤ ሌሎች ከቢራ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መጠጦች፣ ዱቄት ቢራ፣ የአልኮል ይዘታቸው ከ7% ያልበለጠ - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ በድብልቅ የተዘጋጁ፣ የአልኮል ይዞታቸው ከ7% ያልበለጠ ጥንካሬ ያላቸው መጠጦች - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን

➡️ የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) - የተስተካከለው 103 ብር በኪሎግራም

ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶች የኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ

🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋሮች፤ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ - የተስተካከለው 30% + 644 ብር በኪሎግራም

🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋራዎች - የተስተካከለው 30% + 20 ብር በፓኬት (20 ፍሬ)

🔵 እንደ ትምባሆ ከሚያገለግሉ የተዘጋጁ ሲጋሮች፣ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ እና ሲጋራዎች - የተስተካከለ 30%+20ብር በፓኬት ( 20 ፍሬ)

🔵 የሚጨስ ትምባሆ፣ በማናቸውም ምጣኔ እንደ ትምባሆ የሚያገለግሉ ነገሮችን የያዘ ቢሆንም (የፍራፍሬ ጣዕም እንዲኖራቸው የተደረጉም ያልተደረጉም የትምባሆና ግላይሰሮል ቅልቅል የያዘ ትምባሆ ለማጨስ የሚያገለግል በውሃ ማስተላለፊያ ቱቦ የሚጨስ መዓዛ ሰጭ ዘይት እና ምዝሞዙች ፣ ሞላሰስ ወይም ስኳር ከተጨመረባቸውም ካልተጨመረባቸው በስተቀር) - የተስተካከለው 30% + 644ብር ኪሎግራም

🔵 " የተዋሐደ " ወይም " እንደገና የተዘጋጀ " ትምባሆ - የተስተካከለ 30%+644 ብር በኪሎግራም

🔵 ሱረት፤ የትምባሆ ምዝምዞችና ኤስንሶች - የተስተካከለ 30%+644ብር በኪሎግራም

መረጃው የተላከው ከገንዘብ ሚኒስቴር ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ባንኮች እና ፍቃድ የሚሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ላይ የሚሰሩ አካላት በራሳቸው መካከል እና ከደንበኞቻቸው ጋር በዋጋው ላይ ነጻ ድርድር በማድረግ የውጭ ምንዛሪ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንሰሚሆን ተነግሯል። ባንኮች በየዕለቱ ለሚያደርጉት የውጭ ምንዛሪ ግብይት የሚያውሉትን…
#ያንብቡ

የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ ምን አሉ ?

- የማይጠበቅ ነው ብዬ መናገር አልችልም። ግን በዚህ ፍጥነት መሆኑ ለእኔ አስደጋጭ ነው።

- በእርግጥ አሁን የተደረገው devaluate /ገንዘብ ማዳከም/  አይደለም። devaluation ማድረግ እና floating ይለያያል።

- devaluate የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተወሰነ መልኩ በመንግስት ውሳኔ ማዳከም ማለት ነው። አሁን ግን እንደዛ አይደለም የተደረገው። አሁን የተደረገው በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት / floating / ነው።

- የውጭ ምንዛሪ ተመን በ3 መልኩ ይመራል።

1. fixed exchange rate / 👉 በመንግስት ውሳኔ / መንግስት አንድ ዶላር በዚህ ያህል ብር ነው የሚወሰነው ብሎ ድርቅ ሲያደርግ በዛ ብር ብቻ ነው የሚወሰነው ሲል።

2. floating managing 👉 ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ስትመራበት የነበረው ነው። በመንግስት ውሳኔ አለው ግን በየቀኑ መንሸራተት ያለው ነው። በየቀኑ የሚምሸራተት ነው። በምዛሬው ላይ በየዕለቱ ለውጥ የሚታይበት ነው። መንግስት መነሻውን እያስቀመጠ ገበያው እየወሰነ ሲቆይ ነው።

3. floating 👉 በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር ሲመራ ነው። አሁን መንግስት የወሰነው በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር እንዲመራ ነው (floating exchange rate)።

- ብዙ floating እያደረጉ የሚመሩ ሀገራት አሉ ያደጉ ሀገራትን ጭምር።

- floating የሚመራው እንዴት ነው ? ብሔራዊ ባንክ 1 ዶላር በዚህ ብር ይመንዘር ማለት አይችልም። ለኢትዮጵያ ብር ያላቸው ፍላጎት ኢትዮጵያ ለውጭ ምንዛሬ ያላት ፍላጎት ዓለም አቀፍ ገበያው ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከግምት ይገባል። ገበያው የዕለቱን ፍላጎት ይወስናል። በዕለቱ ዶላር በጣም ከተፈለገ ከፍ ይላል። ካልተፈለገ ዝቅ ይላል።

-  floating ለገበያ በጣም መጥፎ ላይሆን ይችላል ግን በቂ የዶላር reserve ኢኮኖሚው መያዝ አለበት። floating በተጀመረ በጀንበር ውስጥ ገበያው ብዙ ሊለዋወጥ ይችላል። ፍላጎት ካለ ዶላር አሁን ካለው በእጥፍ ሆኖ ሊያድር ይችላል።  ይህ ደግሞ ገበያውን ያናጋዋል። ስለዚህ ይሄን የሚያመጣጥን ብቂ የዶላር reserve በባንክ ቤቶች በብሄራዊ ባንክ ይዞ መገኘት ይገባል።

- floating ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ብቻ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። የውጭ ጫና፣ ብድር ፣እርዳታ ፍለጋም ስላለበት ኢኮኖሚው ስለሚጠቀም ብቻ ሳይሆን የIMF ዓለም አቅፍ ተቋማትም ጫና ስላለ እሱን ለመቋቋምና በቀጣይ ትብብራቸውን ለማግኘት ሲባል ሊወሰን ይችላል።

- ገበያው በጣም shock / መናጋት የሚጠብቀው እንደሆነ ምንም ክርክር የሚያስፈልገው አይደለም። መጀመሪያ የሚሆነው import በጣም ውድ ያደርገዋል። floating ሲደረግ ገንዘብ devaluate መሆኑ / መዳከሙ አይቀርም። ይህ ማለት ወደ ጥቁር ገበያው ወዳለው ተመንና ከዛም ከፍ እያለ ነው የሚሄደው።

- ከባንክ ላይ 58 ብር ገዝተው / በጥቁር ገበያው ተመን ገዝተው ወደ ገበያው import ያደርጉ የነበሩ አሁን floating ከሆነ በጣም በከፍተኛ ገንዘብ 1 ዶላርን መግዛታቸው አይቀርም። በዚህም ከውጭ የገዙት ቁሳቁስ ሀገር ውስጥ ሲገባ ውድ መሆኑ አይቀርም። ይሄን መንግስትም የሚያምነው ነው።

-  ኢትዮጵያ ውስጥ ሸቀጣሸቀጥ ብቻ ሳይሆን ለProduction የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች import ይደረጋሉ፤ ስለዚህ ውድ መሆናቸው አይቀርም።

- ' በፍጹም ደመወዝ አልጨምርም ' የሚለው ዜና አሁን ደመወዝ እጨምራለሁ እደጉማለሁ እያለ ነው። ' ከነዳጅ ድጎማ እራሴን አወጣለሁ ' ይል የነበረው ዜና አሁን መደጎሜን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ስለዚህ import ቁሳቁስ ውድ እንደሚሆን ያሳያል።

- floating የተወሰኑ አካላትን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። ሌሎችን ተጎጂ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ ፦  በ58 ብር ተመን ጊዜ ዶላር ይዘው የነበሩ ሰዎች ምንዛሬ ሲጨምር የሆኑ አካላት ተጠቃሚ መሆናቸው አይቀርም በግልባጩም እንደዛው ነው።

- ብዙ ነገሮች import ስለሚድሩግ ገበያው ላይ ተፅእኖ ማሳደሩም አይቀርም።

- የውጭ ቀጥተኛ investment ላይ ማሻሻያው ጥሩ ጎን ሊኖረው ይችላል። አንድ ዶላር ይዞ የመጣ የውጭ ባለሃብት በ58 ብር ይገዛ ነበር አሁን floating ከሆነ devaluate ከተደረገ ይዞት የሚመጣው ከፍ ያለ ይሆናል ምንዛሬው።

- በቀጣይ ጊዜ የውጭ ባላሃብቶች ወደ ገበያ ብስፋት እንዲገቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።

- በዚህ ወቅት floating መደረጉ ግን በግሌ በጣም አስደንጋጭ ነው። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አልገምትኩም። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-29-2

@tikvahethiopia