TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በወልቂጤ ምን ሆነ ?

ዛሬ ረቡዕ በወልቂጤ ከተማ ውስጥ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ 7 ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል። 

በከተማው ነዋሪዎችን ካማረረ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለማቅረብ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ  ወስደዋል።

በዚህ የፀጥታ ኃይሎች እርምጃም 2 ሰዎች ሲገደሉ ቢያንስ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች እና የጤና ምንጮችን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የሟቾቹን እና የቁስለኞቹን ብዛት ማረጋገጡን ዘገባው አክሏል።

ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆነው ክስተት መነሻ፤ በአዲስ ክ/ ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላለፉት 3 ወራት መቋረጡ እንደሆነ የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ከመኖሪያቸው 14 ኪ/ሜ ርቀት ከሚገኙ አካባቢዎች ሲያጓጉዙ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

በተመሳሳይ ዛሬ ጠዋት ውሃ ለመቅዳት በተለምዶ " ዱባይ ካፌ አደባባይ "  ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ቢጓዙም፤ በስፍራው የውሃ አገልግሎት በመቋረጡ ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ መውጣታቸውን የዓይን እማኞች ገልፀዋል።

ነዋሪዎቹ የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የወልቂጤ ከንቲባ ጽ/ቤት እና የወልቂጤ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ወደሚገኙበት ስፍራ በማምራት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲገልጹ ቆይተዋል።

በአካባቢው ጸጥታ ለማስከበር የተሰማሩት #የደቡብ_ክልል_ልዩ_ኃይል አባላት የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን #የአስለቃሽ_ጭስ በመተኮሳቸው ሰልፈኞቹ ድንጋይ ወደ መወርወር መግባታቸውን የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ 2 ሰዎች ሲገደሉ 9 ሰዎች ቆስለዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Photo Credit ፦ ብስራት ዜዶ

@tikvahethiopia