TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Puntland #Somalia

ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።

ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።

የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።

ምክንያቱ ምንድነው ?

የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።

NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።

በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።

ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።

ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡

ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።

ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።

ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።

መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia