TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ' አክሲዮን እናሻሽጣለን ' የሚሉ ማስታወቂያዎችና ግለሰቦች ህገወጥ ናቸው " - የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፤ " የአክሲዮን ድርሻ እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ይወቅልኝ አለ።

በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ የካፒታል ገበያ አማካሪ አቶ አሰፋ ስሞሮ ፤ " በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ከአክሲዮን ገበያ ጋር በተገናኘ #የድለላ ስራ እየሰሩ ያሉ #ህገወጥ ግለሰቦች መኖራቸውን መረጃውን አለን ነገር ግን አንዳቸውም ከባለስልጣኑ ፈቃድ አላገኙም " ብለዋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ለጊዜው ፈቃድ መስጠት አለመጀመሩን የገለጹት ባለሙያው የፈቃድ መመሪያው ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በማንሳት በሚደረጉ ቀጣይ ውይይቶች ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ወቅት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ውጪ " አክሲዮን እናሻሽጣለን " የሚሉ ማስታወቂያዎችም ሆነ ግለሰቦች ህገወጥ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል ሲል አስገንዝበዋል።

በተቀመጠው አዋጅ መሰረት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች በሚል መጠሪያ ተቋሙ ፈቃድ እንደሚሰጥ በመግለጽ አስፈላጊው ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግባቸው እንደሚሆኑም ከአሁኑ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ በይፋ ፈቃድ መስጠት ሲጀምርም በመሰል ህገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ ግለሰቦችን በህግ #ተጠያቂ እንደሚያደርግም አሳውቋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ #የአሃዱሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia