TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢቦላ⬆️

በኮንጎ #የኢቦላ በሽታ እንደገና በማገረሸቱ የተነሳ ወላጆች በፍርሃት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት #እያስቀሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በኢቦላ ቫይረስ በሽታ ምክንያት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #የትምህርት ተሳትፎ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ወረርሽኙ በነሐሴ ወር ከተከሰተ ወዲህ በኢቦላ #የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል፡፡

ይሄን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረትም በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው መላክ መጀመሩን አልጀዝራ በዘገባው አመልክቷል።

@tsegawolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በደቡብ ክልል ሸካና ከፋ ዞኖች የተከሰቱት #ግጭቶች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው አስቀድሞ መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር #ከሃዋሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በእነዚህ ቦታዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እና ግጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

በተለይም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ላይ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የገለፁት።

በእነዚህ ሶስት ዞኖች የዜጎች የመንቀሳቀስ እና ንብረት የማፍራት #መብት መገደቡን አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ወደ ሶስቱም አካባቢዎች መርማሪዎችን ቢልክም ምርመራ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን እና መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ነው የተናገሩት።

የፀጥታ አካላትም ግጭቶቹን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ እየወሰዱ አለመሆናቸውን ከአካባቢዎቹ መርማሪዎች ለኮሚሽኑ በስልክ ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁምም ገልፀዋል።

አሁን ላይ በይፋ በግጭቶቹ #የሞቱ እና #የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርንም በዚህ ምክንያት በአግባቡ ማጣራት አለመቻሉን በማንሳት ይህም የችግሩን ስፋት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ችግሩ በተፈጠረባቸው እነዚህ አካባቢዎች ገብቶ የማረጋጋት ፣ ህግ እና ስርዓትን እንዲሁም የዜጎችን መብት የማስከበር ስራ እንዲያከናውን ነው የጠየቁት።

እስካሁን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ግጭት ካለባቸው አምስት ወረዳዎች መካከል በሁለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመግባቱ የተሻለ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ዶክተር አዲሱ አስታውቀዋል።

በእነዚህ መከላከያ በገባባቸው ቦታዎችም ኮሚሽኑ ከነገ ጀምሮ ምርመራ እንደሚጀመር ነው ያስታወቁት። ምርመራውንም በኃላፊነት መንፈስ ያከናውናል ብለዋል።

ዶክተር አዲሱ በመግለጫቸው በተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን መነሻ በማድረግ ችግሮቹ ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ለመከላከልና ሲከሰቱም በዘላቂነት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ኮሚሽኑ አድርጎ ለመንግስት ማቅረቡን አስታውቀዋል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

" በቤጊ ሁለት ቀበሌዎች ረሃብ ተከስቷል "

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱ ተነገረ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ራሱን " የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ " ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀስባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል በቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱን የምዕራብ ወለጋ ዞን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ሸኔ የያዛቸውና ለጥቂት ጊዜያት ያስተዳደራቸው ወረዳዎች ነበሩ።  እነዛ ወረዳዎች ብዙ ችግሮች ገጥሟዋቸዋል " ብለዋል።

ለአብነት ታጣቂ ቡድኑ ሲንቀሳቀስባቸው በነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች #ረሃብ መከሰቱን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ፣ " እስፔሻሊ ጠረፍ ላይ የሚገኙ ቀበሌዎች ተጎድተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ተጋባና ሻንታ ቀበሌዎች ረሃብ አለባቸው " ብለዋል።

ረሃብ ተከሰተበት የተባለውን የቤጊ ወረዳ ሁኔታን ሲያስረዱም አቶ ሰለሞን ፣ " መሰረተ ልማት፣ ቀበሌዎች፣ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በጣም ጉዳት የደረሰበት ወረዳ ነው " ብለዋል።

" ከጤና ጋር በተያያዘ ቢያንስ 45 የሚሆን ጤና ኬላ ወድሟል ወደ አምስት ጤና ጣቢያዎች ተቃጥለዋል " ሲሉ አስታውሰው፣ ወረዳውን ታጣቂ ቡድኑ ሲቆጣጠረው አርሶ አደሩ እንዳያርስ በማዳበሪያ እንዳይጠቀም፣ ማኅበረሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረጉን አስረድተዋል።

" ሸኔ አገሪቱን ወደ ድህነት የሚመራ እንጂ ምንም አላማ የሌለው ነው " ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ ታጣቂ ቡድኑ " በቄለም ወለጋና  በቤጊ፣ በቆንዳላ በተለይ ገጠሩን አካባቢ ተቆጣጥሮ ጉዳት አድርሷል። ሰው ገድሏል። ብዙ ንብረቶች በዚህ ታጣቂ ቡድን ወድመዋል " በማለት ተናግረዋል።

ረሃብ የተጋረጠባቸው የሰሊጥ አምራቾች ናቸው ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ፣ " ሸኔ አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በሚወስድበት ጊዜ ቀቅሎ እንዲበላ ሲያደርግ ነበር። መብላት ማለት እንደ ምግብ እንዲበላ በማድረግ እንዳያርስበት፣ እንዳይጠቀምበት ማድረግ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች በበኩላቸው በተከሰተው ረሃብ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው፣ መንግሥት የምግብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ በወባ ወረርሽኝም የሰው ሕይወት እያለፈ መሆኑን አስረድተዋል።

በረሃብ የሞተ ሰው እንዳለና እንዴሌለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሰለሞን ፣ " ከረሃብ የተነሳ የሞተ ሰው ሪፓርት አልደረሰኝም። ከምግብ ጋር በተያያዘ ግን የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሰሞኑን 400 ኩንታል ዱቄት አድርሷል። እርዳታ ግን አሁንም ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከረሃብ ባሻገርም በዞኑ በሚጉኙ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ እንደተከሰተ፣ #የሞቱ ሰዎችም እንዳሉ ገልጽው፣ መንግሥትና መንግስታዊ ያልሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች እርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን ከላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀረበበት ክስ ዙሪያ ይፋዊ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia