TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
Alamata-Kobo-11-5-2018
በአላማጣ ከተማ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የኢትዮጵያ ክልሎችን ከሚያገኛኙ አውራ መንገዶች አንዱ የሆነው የአላማጣ ቆቦ መስመር ዝግ ሆኖ ቆይቷል። ከትላንት በስትያ #የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ በመግባት መንገዱ እንዲከፈት ማድረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

©voa
@tsegabwolde
ደምቢ ዶሎ🔝ላለፉት ወራት በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ወደ ቆየችው ደምቢ ዶሎ ከተማ #የመከላከያ_ሰራዊት የገባ ሲሆን፣ የሰራዊቱን መግባት የተቃወሙ ግለሰቦች መንገድ የመዝጋት ሙከራ ማድረጋቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት የሰላም ዕጦት በታየባቸው የምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የፌድራል ሀይሎች እንዲሰማሩ መወሰኑ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahevhethiopia
#Update ከኢትዮ ኤርትራ ድንበር የተንቀሳቀሱ #የመከላከያ_ሰራዊት አባላት በጎንደር በኩል ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሲሄዱ ማየታቸውን elu ከአይን እማኞች ተነግሮኛል ሲል ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

#የመከላከያ_ሰራዊት መዋቅር #እንዲሻሻል ተደረገ ከአሁን ቀደም 6 የነበረው የእዝ ብዛት ወደ 4 ተቀንሷል።

4ቱ እዞች የምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ሰሜን ናቸው። #የባህር_ሀይልን የሚያደራጅ ኮሚቴና የልዩ ዘመቻ እዝ ተዋቅሯል።

ይህንንም መሰረት በማድረግ የአዳዲስ አመራር ምደባ መካሄዱን ዛሬ የልዩ ዘመቻ አዛዥ ሌቴናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም መግለጫ ሰጥተዋል።

via-fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጊንቢ ከተማ ሁለት ወጣቶች #በታጠቀ ኃይል #መገደላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ከትላንት በስቲያ አንድ በጉልበት ሥራ የሚተዳደር ወጣት ሲገደል፣ ትላንት ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል ያለበት ወጣት ተገድሏል፤ ይላሉ የዓይን እማኞች፡፡ ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከተማውማዋ በከፍተኛ የጦር መሣሪያ ድምፅ ስትታመስ መቆየቷን ነዋሪዎች ተናግረዋል፤ የአካባቢው ኮማንድ ፖስት በበኩሉ #የመከላከያ_ሰራዊት ማንንም አልገደለም ብሏል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
OBN Live! 7ኛውን #የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን አከባበር #ከአዳማ በቀጥታ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ መከታተል ትችላላችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን አደረሰን!

#የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን!

#TIKVAH_ETHIOPIA ለመላው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ እንኳን ለ7ኛ ጊዜ ለሚከበረው #የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን በሰላም #አደረሳችሁ#አደረሰን ለማለት ይወዳል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር አይሻ መሃመድ‼️

#የመከላከያ_ሰራዊት_ቀን የሰራዊቱን አቅም በማሳየት እና የሰራዊቱ ሞራል በመገንባትም ጭምር ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር #አይሻ_መሃመድ አስታወቁ።

ሚንስትሯ በሰጡት የማጠቃለያ መግለጫ 7ተኛው የኢፊዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ቀን በስኬት ተጀምሮ በስኬት እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል።

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተዋቅሮ በአሉን እንዴት እናስኪድ በሚለው ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ እንደተገባ ሚንስትሯ አስታውሰዋል።

በተለያዩ ቦታዎች የተደረጉት የፓናል ውይይቶች እና የተለያዩ ዝግጅቶች ህብረተሰቡንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የበለጠ እንዲቀራረቡ እንዳደረገም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ሰአት የመከላከያ ሰራዊተ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች ህገ መንግቱን የማስከበር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ እና የሕብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ የሃገሪቱን ሉአላዊነት ከውስጥም ከውጭም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ እይተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው መከላከያ ሚኒስትሯ የገለፁት።

ምንጭ፦ EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረሪ

በሐረሪ ክልላዊ መስተዳድር ስር በሚገኘው #ጅኔላ_ወረዳ በአካባቢው የሚኖሩ ከስልሳ በላይ ቤቶች ከሌላ አካባቢ መጡ በተባሉ አካላት ጥቃት ተፈፀመባቸው።

የተወሰኑ ነዋሪዎች በሁኔታው በመስጋት ቤታቸውን ጥለው ስለመውጣታቸው ጀርመን ራድዮ ደረሰኝ ባለው መረጃ ጠቁሟል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤት በመዝለቅ የተለያዩ ንብረቶች ሰባብረዋል ተብሏል። በስፍራው የተገኘው የDW ዘጋቢ የአንዳንድ መኖርያ ቤት አጥሮች ፈርሰው፣ አንዳንዶችም በስለት (ባንጋ) መቆራረጣቸውን ታዝቧል። የውሀ መስመር እና የመብራት ቆጣሪ የተሰባበረበት መኖርያ ቤትንም ተመልክቷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው “የአካባቢው መሬት የእኛ በመሆኑ ልቀቁ በሚሉ አካላት” መሆኑን የሚናገሩት ተጎጂ ነዋሪዎች በድርጊቱ ማዘናቸውን ለጀርመን ራድዮ ገልጸዋል። “አሁንም ችግራችንን #አውጥተን ለሚዲያ #ለመናገር እንሰጋለን፤ ህይወታችንም ያሳስበናል፤ ምን ዋስትና አለን” ሲሉ ስማቸውን ለመግለፅ የፈሩ ነዋሪ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ኃላፊ “ግጭቱ መኖርያ ቤቶቹ ከተገነቡበት ቦታ የይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ” መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በግጭቱ የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ነገር ባይኖርም በጥይት የተመታ አንድ ሰው ግለሰብን ጨምሮ አራት ሰዎች ተጎድተዋል። በጥይት ተመቷል የተባለው ግለሰብም በሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ እንደሚገኝም አስረድተዋል። በግጭቱ በስልሳ አንድ መኖርያ ቤቶች ላይ ጥቃት ሲደርስ ዝርፊያና ንብረት ማውደም ተፈፅሟልም ብለዋል።

ህብረተሰቡን የማወያየት ስራ እየተሰራ መሆኑ እና የተፈጠረው ሁኔታም #ተረጋግቷል ቢባልም ችግሩ መሰረታዊ መፍትሄ ያላገኘ በመሆኑ በነዋሪዎች አንድ አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ናቸው።

#የመከላከያ_ሰራዊት አባላት ግጭቱን ለማረጋጋት በአካባቢው ሲዘዋወሩ የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ የተመለከተ ሲሆን ነዋሪዎች ዱላ፣ ስለታም ነገሮች (መቁረጫ ባንጋ) ይዘው አካባቢያቸውን ሲጠብቁ አስተውሏል። ሐኪም ጋራ እየተባለ በሚጠራው በዚህ አካባቢ የተፈጠረው ሁኔታ ባለመረጋጋቱ ከ150 በላይ ነዋሪዎች በየዕለቱ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ተሰባስበው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ (አማርኛው አግልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia