TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሻሸመኔ⬆️

ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ጃዋር መሀመድን ለመቀበል በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ችግር ተፈጥሮ ነበር። በዚህም ጥቂት ሰዎች ተጎድተዋል። በዝርዝር ጉዳዩ አጣርቼ አሳውቃለሁ።

#ዝግጅቱ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት እና ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት⬇️

"በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በተከሰቱ አንዳንድ ግጭቶች ምክንያት ህይወታቸው ላለፈና የተለያየ ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም በተፈጠረው ሁኔታ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ #ሃዘን እየገለፅን ከዚህም ጉዳይ ጋር በተያያዘ በንፁሀን ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳት ምክንያት በማድረግ እና እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ወደ አስተማማኝ መረጋጋት እስኪመለስ ድረስ ጉዳዩ ከሚመለከተው የከተማው አስተዳደር ጋር በመወያየት #ዝግጅቱ ከመስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም በኋላ አቅምና ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ እንደሚካሄድ እና የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቀን አስቀድመን እንደምናሳውቅ ስንገልፅ የመግቢያ ትኬቱን ቀደም ብላችሁ ለገዛችሁና ጥሪ ለተደረገላችሁ እንግዶች እንዲሁም ዝግጅታችንን ለመታደም ከተለያዪ የሃገራችን ክፍሎችና ከባህር ማዶ ጭምር ለመጣችሁ ክቡራን ወገኖቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት በተፈጠረው ተደጋጋሚ ሁኔታ ለገጠማችሁ #መጉላላት በዚህ አጋጣሚ ከፍ ያለ #ይቅርታ ለማቅረብ እንወዳለን።"

አዘጋጅ ኮሚቴው

@tsegabwolde @tikvahethiopia