TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዳማ⬇️

በአዳማ ተፈናቃዮች በሰፈሩበት አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ ዘጠኝ ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት አካባቢው ተረጋግቶ ሰላም መስፈኑም ተመልክቷል፡፡

የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነተ ባለሙያ ሳጅን ወርቅነሽ ጋልሜቻ ዛሬ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ሰፈረው በሚገኙበት አካባቢ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበሩ ተጠርጥረው ነው፡፡

በድርጊቱ የተጠረጠሩት እነዚህ ግለሰቦችን ለመያዝ የአካባቢው ህብረተሰብ ትብብርና ድጋፍ አድርጓል የግጭቱ መንስኤ ተፈናቃዮች በአካባቢው የግንባታ ድንጋይ ለማውጣት ከተሰማሩ ግለሰቦች ጋር ከስራው ጋር በተያያዘ ባለመግባባት በተነሳ ፀብ እንደሆነ ሳጅን ወርቅነሽ አመልክተዋል፡፡

በወቅቱ በተፈጠረው ችግር የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ጠቁመው 18 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውሰዋል፡፡

የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት አካባቢው ተረጋግቶ ሰላም መስፈኑን ገልጸው ግጭቱን በመቀስቀስ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ፍርድ ለማቅረብ የምርመራው ስራ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ከተያዙት ግለሰቦች መካከል አራት ከተፈናቃዮች እና ከአካከባቢው ነዋሪዎች ውስጥ ደግሞ አምስት መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በአካባቢው የእምነት ተቋማትን ለማቃጠል ነው የሚባለው #ከእውነት የራቀ መሰረተ ቢስ ወሬ በመሆኑ በኃይማኖት ሽፋን ከሚደረግ የጥፋት ቅስቀሳ ህብረተሰቡ መከላከልና እራሱን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“አቶ ገዱ አንዳርጋቸው #የመኪና_አደጋ አልደረሰባቸውም” አቶ አሰማኸኝ አስረስ
.
.
.
በማህበራዊ ሚዲያ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ #አሰማኸኝ_አስረስ ተናገሩ።

በምዕራብ ጎንደር ገንዳ ውሃ ከተማ ሰሞኑን በተከሰተው ግጭት ዙሪያ ትናንት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ያደረጉት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ባህር ዳር ሲመለሱ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸውና የሾፌራቸውም ህይወት እንዳለፈ በእርሳቸው ላይም ጉዳት እንደደረሰ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ትክክለኛ አለመሆኑን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ወደ ገደውሃ ሲሄዱም ሆነ ወደ ባህር ዳር ሲመለሱ በሄሌኮፍተር እንደተጓዙ አስታውሰው በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ #ከእውነት_የራቀ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ገዱ በተከሰተው ግጭት ዙሪያ ከገንዳ ውሀ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገው መመለሳቸውን አቶ አሰማኸኝ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል መንግስት‼️

በምእራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች መንግስት #የአየር_ጥቃት ፈፅሟል በሚል የሚናፈሰው ወሬ #ከእውነት_የራቀ መሆኑን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ላይ የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር ሙከራዎች እየተደረጉ ነው ብሏል።

የመንግስት ጦር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው የሚለው እና የአየር ጥቃት በመፈፀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው በሚል የተሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

በዚህ ዙሪያ ያለው ሀቅ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ስራውን በጥናት ላይ በመመስረት እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እያከናወነ መሆኑ ነው ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው ላይ ያለው የፀጥታ ችግር ይህን ያክል የአየር ጥቃት እስከመውሰድ የሚያደርስ አይደለም ሲልም ቢሮው አስታውቋል።

መንግስት አሁንም ቢሆን የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ያለበትን ሀላፊነት እና ግዴታ ለመወጣት የጀመረውን ስራ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠቱን እንዲቀጥል እና ለሰላም የሚያደርገውን ትብበር አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews በጅማ ከተማ አንድ አባት ታርደው ወንዝ ዳር ተጥለው ተገኙ ተብሎ በፌስቡክ እና በቴሌግራም የሚሰራጨው መረጃ #ከእውነት_የራቀ ነው። ይህንን ያረጋገጡልንም የጅማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ናቸው።

ሼር የምታደርጉትን መረጃ በቅድሚያ አጣሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia