TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤

ቤተክርስቲያኗ ከባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዙ የሚነገሩባት #አሉባልታዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገለፀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ ከቤተክርስትያኗ የባንክ አገልግሎት  ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታ ይነሳል ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን የምትሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ከዓባይ ባንክ ጋር ሥራ የጀመርነው በህጋዊ አሰራር በጨረታ በተደረገ ሂደት  አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። " ብለዋል።

" ከዓባይ ባንክ ይልቅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኦሮሚያ ባንክ ያለን ገንዘብ ይበልጣል። " ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " ዓባይ ባንክ ያለን ገንዘብ ተንቀሳቃሽና ለሰራተኛው የብድር አገልግሎት በማቅረብ ለሰራተኛው የመኪና፣ የቤትና የልዩልዩ ግዤዎችን ለመፈጸም የሚያስችል አገልግሎት የሚሰጥበት የባንክ አገልግሎት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፤ ቤተክርስቲያኗ በኦሮሚያ ባንክ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ ማስቀመጧን ብፁዕነታቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው " በጣም መጠነኛ ገንዘብ በአዋሽ፣ በሕብረትና በአቢሲኒያ ባንኮች አስቀምጣለች ፤ ከዚህ ውጪ በሌላ ባንክ  ወይም በአማራ ባንክ የተቀመጠ  ምንም አይነት የማዕከላዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ገንዘብ የለም። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" የተቀመጠ ገንዘብ አለ ከተባለም  #በማስረጃ  ማቅረብ ይቻላል " ያሉ ሲሆን " አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው ። " ሲሉ ገልጸዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት ነው።

@tikvahethiopia