TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum #EthiopianAirlines የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል። ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም። የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ…
#Axum

" እንደኛ ፍላጎትማ #ለህዳር_ጽዮን እንዲደርስ ነበር ... እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን የአክሱም ኤርፖርታችን ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን ይጀምራል " - አቶ ለማ ያዴቻ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጦርነት ምክንያት እጅግ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን እንደሚጀምር አሳውቋል።

በተለይም የአክሱም ነዋሪዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች ፣ በጦርነት የወደመው የአክሱም ኤርፖርት መቼ ስራ ይጀምራል የሚል ጥያቄ አላቸው።

ከዚህ ቀደም ከተሰጠው ማብራሪያ በኃላ
(https://t.iss.one/tikvahethiopia/82211?single) የጥገናው ስራ ከምን ደረሰ የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያደቻ ፤ የአውሮፕላን ማረፊያውን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ስራውን ማከናወን እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

አቶ ለማ ፤ " እንደሚታወቀው የመንግሥት የግዢ ስርዓት አለ፤ ጨረታ ወጥቶ በስነስርዓት evaluate ተደርጎ ጨረታው መሰጠት ያለበት " ብለዋል።

" እንደኛ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ለህዳር ጽዮን እናደርስ ነበር ፤ መሬት ላይ ያለው የግዢ ስርዓት የጨረታው ስርዓት ለዛ ጊዜ አላደረሰንም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው መቼ ነው ወደ አገልግሎት የሚመለሰው ? ለሚለው ጥያቄም አቶ ለማ " ኤርፖርቱ በጣም ነው የተጎዳው ፤ ስራው መሰረታዊ ስራ ይፈልጋል ፤ ተጫራች ምርጫ ጨርሰናል የመጨረሻዎቹ negotiation ላይ ነው ያለውነው ከ10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ታውቆ ስራውን ይጀምራል " ብለዋል።

" እነሱንም ግፊት የምናደርግባቸው በሁለት እና በሶስት ወር ውስጥ ሰርተው ሊጨርሱ ይችላሉ ፥ ግን ደግሞ ካንትራክተሩ ሲመጣ የራሱን Schedule / መርሃ ግብር  ይዞ ስለሚመጣ የነሱንም Schedule ማክብረ ይጠበቅብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሆነው ሆኖ ግን በእርግጠኝነት የምናገረው ክረምት ከመግባቱ በፊት የአክሱም ኤርፖርታችን ስራውን ይጀምራል ፣ ቱሪስቶችን እናመጣለን ፣ የአካባቢው ነዋሪም የሚገባውን አገልግሎት እንዲያገኝ እናደርጋለን ፀንተንም እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

እጅግ ከፍተኛ ምዕመን ይገኝበታል ተብሎ ለሚጠበቀው ለህዳር ጽዮን በዓል አየር መንገዱ አቅራቢው ባለው የሽረ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ በረራዎችን ለማሳደግ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው አቶ ለማ ያደቻ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃለምልልስ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia