TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የመቐለ ከተማ አስተዳደር 13 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ላስመዘገቡ 222 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት #መሬት በዕጣ ማስረከቡ ተገልጿል፡፡ ባለሀብቶቹ ለ22 ሺ 9 መቶ ዜጎች #የሥራ_ዕድል ይፈጥራሉ ተብሏል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BelaynehKindie

ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገነቡት በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን #መገጣጠም የሚያስችል የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ገለፁ።

ይኸው በደብረ ብርሃን ከተማ ላይ ለተገነባው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሁለት (2) ቢሊየን ብር ወጪ እዳደረጉበት ተሰምቷል።

አቶ በላይነህ ፤ " ፋብሪካው ከ3 ወር በኋላ ወደማምረት ሥራ ይገባል፡፡ " ያሉ ሲሆን " በዓመት 1ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም አለው " ብለዋል።

ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሥራ ሲገባ በዚህ ዓመት ከ250 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጠሙ አቶ በላይነህ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው #ለ500 ሰዎች #የሥራ_ዕድል እንደሚፈጥር መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia