TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀዋሳ " ... በነዳጅ እጥረት ስራችንን መስራት አልቻልንም። ተሰልፈን ነው የምንውለው " - አሽከርካሪዎች " ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ ነው ችግር የተፈጠረው " - የከተማው ገበያ ልማት በሀዋሳ ከተማ የነበረዉ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረትና ሰልፍ ተስተካከለ ተብሎ ጥቂት ጊዜያት ሳይቆይ ድንገት ችግሩ ማገርሸቱን ተከትሎ መጨረሻ የሌላቸው የሚመስሉ ሰልፎች በየማደያዉ…
#ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ የህዝብ ትንራንስፖርት አገልግሎት (ታክሲ) የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ፤ " የነዳጅ ጉዳይ ስቃያችንን አበላን ፤ የመፍትሄ ያለህ !! " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ፤ "ሰርተን ከምንገባበት ለነዳጅ ሰልፍ ቆመን የምንውለበት እየበለጠ ነው " ብለዋል።

የነዳጅ ችግሩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑም በመግለፅ "
ካልሰራን ልጆቻን ምን ይብሉ ? ፤ እኛስ ምን በልተን እንደር ? ይህ ጉዳይ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት በዚሁ በሀዋሳ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች ፤ " በረዣዥም ሰልፍችና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ስራችን በአግባቡ መስራት አልቻልንም " በሚል ምሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተው ነበር።

አሽከርካሪዎች ፤ ሁሉም ማደያዎች በአግባቡ አለመስራትና ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ መኪኖች ለነዳጅ ሰልፍ ተገፍተዉ ከመግባት ባለፈ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ሳልቫቲዮ ገጥመዉ መምጣታቸው ቀኑን ሙሉ ተሰልፈዉ እንኳን መቅዳት እንዳይችሉ ምክኒያት እንደሆነባቸው ገልጸው ነበር።

በወቅቱ እየተነሳ ላለው ቅሬታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ገበያ ልማት ቢሮ የስነልኬት ባለሙያው አቶ ሀብታሙ መኮንን ፤ ችግሩ መኖሩን አምነው ፤ ከጅቡቲ የሚመጣው ነዳጅ መዘግየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ክፍተት ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ችግሩም " #ወደፊት_ይቀረፋል " የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ ማመልከታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia