TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#RUSSIA

ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል።

ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች) ° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ ማካሄዳቸው ተነግሯል።

ፖሊስ በርካታ የተመሳሳይ ጾታ ክለቦችን ውስጥ በመግባት የተወሰኑትን ታዳሚዎች አጠር ላለ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል።

በተጨማሪም የአንዳንዶች ፖስፖርት ተወስዶ ፎቶ እንዲነሳ ተደርጓል ተብሏል።

ፖሊስ የምሽት ክበቦች ላይ ዘመቻ ያካሄድኩት " አደንዛዥ እፅ ለመፈለግ ነው " ማለቱ ተነግሯል።

ሩስያ ፦

- ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴ ጽንፈኛ ነው በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች አግዷል።

- እግድ የተላለፈው የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው።

- በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

- በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

- እኤአ 2013 ላይ ከተለመደው ውጪ ያለ ጾታዊ ግንኙነት ላይ የሚደረግ ፕሮፖጋንዳን የሚከለክል ሕግ አውጥታለች።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን የሚያመለክቱ ይዘቶች ከመጽሓፍት፣ ከፊልሞች፣ ከማስታወቂያዎች እና ከቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንዲሰረዙ ተደርገዋል።

- በቅርቡ አንድ የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ የፕሮፓጋንዳውን ሕግ ጥሷል ተብሎ እንዳይከሰስ በደቡብ ኮሪያ የፖፕ ሙዚቃ ቪዲዮ ላይ የነበረውን የተመሳሳይ ፆታ መግለጫ የሆነውን ቀለም እንዲለውጥ መገደዱን ገልጿል።

መረጃው ከቢቢሲ / አስቶሮዥኖ ኖቮስቲ / ፣ ሮይተርስ፣ አልጀዚራ  የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)…
#ሩስያ

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia