TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህክምናው ከዛሬ ጀምሮ ይሰጣል!

ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት #የደም_ስር_መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የፒሲአይ የነጻ ህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ህክምናው የሚሰጠው የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በጋራ ባስገነቡት የልብ ህክምና ማዕከል ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

ማዕከሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ የሚገኝ ሲሆን፥ ህክምናው ከኮሪያ በሚመጡ የህክምና ቡድን አባላትና በማዕከሉ ባለሙያዎች ይሰጣል ተብሏል፡፡

ህክምናው የሚደረግላቸው ታካሚዎች በማዕከሉ ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ የነበሩ መሆናቸውን ማዕከሉ ይፋ አድርጓለ፡፡ይህ ህክምና ለዘጠነኛ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን፥ በዚህ ዙር የፒሲአይ ህክምና ብቻ እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡

ህክምናው በጣም ውድ ከሆኑ የልብ ህክምና አገልግሎቶች አንዱ ሲሆን፥ በግል ሆስፒታሎች ከመቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ ተግልጿል፡፡

በመሆኑም ከፍለው መታከም ለማይችሉ ታካሚዎች ማዕከሉ በነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠቱ ለታካሚዎቹ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም ከኮሪያ፣ ከአሜሪካና አውስትራሊያ በመጡ የልብ ህክምና ቡድኖች የፒሲአይ አገልግሎትን ጨምሮ የቫልቮቶሚና የፔስሜከር የልብ ህክምና አገልግሎቶች መሰጠታቸው ይታወሳል፡፡

ባለፉት ጊዜያት ከዘጠና በላይ ለሚሆኑ #ታካሚዎች አገልግሎቱን ማግኘታቸውን ከቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia