TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

በመጪው ክረምት በሕዳሴ ግድቡ የውሃ መሙላት እንደሚጀመር እና የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ መሰረት እንደሚቀጥል የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በግድቡ ሁለት ተርባይኖች የሚጀመረው የቅድመ ሀይል ማመንጨት ስራም በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እና ሂደት እንዲሁም የድርድር ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው አሜሪካ የግድቡን ሙሌት በተመለከተ ያወጣችው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካ የተፋሰሱ አገራት በራሳቸው ወደ ስምምነት እንዲደርሱ ግፊት በማድረግ በጎ ሚናዋን ብቻ እንድትወጣ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ እና በሌላ ተፅዕኖ የሚሆን ነገር እንደሌለም ሚንስትሩ አረጋግጠዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ስለሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ!

- የሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 88 በመቶ ተጠናቋል።

- ከሞጆ መቂ ከሚዘልቀው 56 ኪሎ ሜትር ውስጥ የ50 ኪሎ ሜትሩ የግንባታ ሂደቱ ተጠናቋል።

- የሞጆ – ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ 202 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን 13 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት ተይዞለታል።

- የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከአምስት ወራት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመኪና ሥርቆት ወንጀል በአዲስ አበባ፦

በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ-ከተሞች የመኪና ሥርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናዋ አዲስ አበባ የመኪና ሥርቆት ወንጀሎች እየተበራከቱ መጥተዋል የሚሉ ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ ፖሊስ የምርመራ ቡድን በማዋቀር ጠንካራ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን በኮሚሽኑ የከባድ ሌብነትና ዘረፋ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ገልፀዋል፡፡

ኮማንደር አለማየሁ እንዳሉት ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ወደ 31 የሚጠጉ የመኪና ስርቆት ወንጀሎች የተመዘገቡ ሲሆን ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ኢቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠቅላይ ሚንስትሩ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ገብተዋል!

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በታርጫ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በከተማዋ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚወያዩ ሲሆን በስታዲየም ለተሰበሰቡ ነዋሪዎችም ንግግር ያደርጋሉ።

#ኢቢሲ #ዳውሮቲዩብ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Forbes

የፎርብስ መጽሔት የአፍሪካ እትም የሆነው ፎርብስ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴን ከ50 ተጽዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ ሴቶች አንዷ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

መጽሔቱ ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ በተጨማሪ የሶልሬብልስ ኩባንያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቤተልሔም ጥላሁንንም ከ50ዎቹ ተጽዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ ሴቶች መካከል አድርጎ መርጧታል፡፡

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ በሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላህ ሀምዶክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አውግዟል፡፡ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶክተር ወርቅነህ ገበየው በሰጡት መግለጫ በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የተሞከረው የግድያ ሙከራን አውግዘዋል፡፡

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ባይኖርም በሽታውን ለመከላከል ማኅበረሰቡ የግል ንጽሕናውን በአግባቡ በመጠበቅ የራሱን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በሽታው ወደ ሀገር ቢገባ ከሚደረጉ ቅድመ ጥንቃቄዎች መካከል የተለያዩ ማእከላትን ግብዓት በማሟላት አስፈላጊ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑንም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው በማቆያ ማእከላት ውስጥ አምስት ግለሰቦች የሚገኙ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በማእከሉ ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ ከ900 በላይ ሰዎች ክትትላቸውን ጨርሰው መውጣታቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

#ኢቢሲ #የህብረተሰብጤናኢንስቲትዩት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን በአዲስ መልክ ለማዋቀር በወጣው አዋጅ መሠረት ለተቋሙ የቦርድ አባልነት የቀረቡ አዳዲስ እጩ ተሿሚዎችን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት፦

1. አወሉ አብዲ - ሰብሳቢ
2. አበበች ሺከታ
3. ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ
4. ማንያዘዋል እንደሻው
5. ዳንኤል ክብረት
6. ኦባንግ ሜቶ
7. ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ
8. ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ
9. ጌትነት ታደሰ አባል

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ትላንት ጎረቤታችን ሱዳን ውስጥ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ፤ ይህ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ እንደነበረ ሀገሪቱ አስታውቃለች፡፡

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ በዚህ ወር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጎብኝቶ እንደነበረ ነበረና ሀሙስ እለት ህይወቱ ማለፉ ነው የታወቀው፡፡

በ50ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረው ግለሰብ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ መሞቱን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

#ሮይተርስ #ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መወሰኑን #ኢቢሲ ዘገበ።

ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እንደገለፁት በቤተክስትያኗ አጥቢያዎች የሚሰጠው አገልግሎት መቋረጡ በምዕምኑ መንፈሳዊ ህይወት ላይ ችግር ማስከተሉን አብራርተዋል፡፡

እናም ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ አገልግሎቱ እንዲቀጥል ሲኖዶሱ መወሰኑን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል። ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው። በክልሉ…
#Afar

በአፋር ክልል ፣ ዱለቻ ወረዳ ሳጋንቶ ቀበሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የፈለቀውን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላለፈ።

ማሳሰቢያውን ያስተላለፈው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ነው።

ዩኒቨርሲቲው " በክልሉ በቅርቡ በተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ በተሰማው ርዕደ መሬት ሳቢያ በአካባቢው ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውኃ መፍለቅ ጀምሯል " ሲል ገልጿል።

ይህንን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ሰዎችም ሆኑ እንስሳት እንዳይጠቀሙት ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

በሬክተር ስኬል 4.9 በተመዘገበው ርዕደ መሬት የተሰነጠቀው መሬት 1.5 ሜትር ስፋት ያለው ስለመሆኑ አመልክቷል።

ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአፋር ክልል የተከሰተው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መሰጠንቅ፣ መኖሪያ ቤቶች ላይ መፍረስና መሰንጠቅ እንዲሁም እስሳት ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መጠነኛ ጉዳት ስለማስከተሉ ዩኒቨርሲቲው አስረድቷል።

ህብተረተሰቡ በተፈጥሮ አደጋው ከተሰነጠቁ አካባቢዎች፣ ድልድዮች እና ተራራዎች እንዲርቅ ጥሪ ቀርቧል። #ኢቢሲ

@tikvahethiopia