TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BahirDar

በባሕር ዳር ከተማ ውሃ ተበክሏል እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ #ሀሰት መሆኑን የባህር ዳር ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ለአብመድ ገልጿል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የውሃ እና ፍሳሽ ባለሙያዎች በየዕለቱ በሁሉም ቦታዎች ማለትም (ታንከር ላይ ፣ መሥመር ላይና ቤት ለቤት በመዞር) የፊዚካል ፣ ባዮሎጂካል እንዲሁም የኬሚካል ናሙና ምርመራ ይደርጋሉ።

ዛሬ እና ትናንት በተደረገው የናሙና ምርመራ ምንም ችግር እንደሌለ መረጋገጡን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት አሳውቋል።

ዛሬ ህዳር 25/2013 ውሃ ተበክሏል በሚል ሥጋት ጥቆማ በተደረገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ናሙና ተወስዶ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩ ተረጋግጧል።

የከተማው ውሃ በቀላሉ የሚበከል አለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይም አጠራጣሪ በሆኑ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ ነው።

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም በኋላም የጥበቃ ሥራው መጠናከሩ ተገልጿል።

ሕዝቡ እውነቱን ተገንዝቦ 'ያለምንም መረበሽ' የእለት ተዕለት ተግባሩን እንዲከውን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት መልዕክት ተላልፏል። (AMMA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...የውሸት መረጃ ነው፤ የኢትዮጵያ መከላከያ አንዳችም የአፀፋ እርምጃ አልወሰደም" - አቶ ተስፋሁን ሲሳይ

ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "የኢትዮጵያ መከላከያ በሱዳን ኃይሎች የተያዘውን ቦታ አስለቀቅ፤ ሱዳኖቹም አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል" የሚሉ የተለያዩ ወሬዎች ሲሰራጩ ነበር።

የምዕራብ ጎንደር ዞን የኮሚኒኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋሁን ሲሳይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚወራው #ሀሰት መሆኑ ለቢቢሲ ሬድዮ የትላንት ስርጭት ተናገረዋል።

የሱዳን ኃይል ከዚህ ቀደም የያዘውን አካባቢዎች አሁንም ለቆ አልወጣም ብለዋል።

አቶ ተስፋሁን፥ "አሁን ባለው ሁኔታ ምንም አይነት ግጭት የለም፤ አሁንም ቦታዎቹን እነሱ እንደያዙት ነው ያለው፤ የተለየ የተደረገ እንቅስቃሴ የለም በኢትዮጵያ በኩል" ሲሉ ተደምጠዋል።

በአካባቢው የመከላከያ እና ሌሎችም የፀጥታ ኃይሎች ስለመኖራቸው እና የወሰዱት የአፀፋ እርምጃ/ቦታዎቹን ለማስለቀቅ ያደረጉት ጥረት እንዳለ የተጠየቁት ኃላፊው ፦ በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች መኖራቸውን ገልፀው እስካሁን ቦታውን ለማስለቀቅ ያደረጉት ጥረት እንደሌለ /የአፀፋ እርምጃም እንዳልተወሰደ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጦር እርምጃ ወስዶ የሱዳን ኃይል የያዘውን ቦታ ለቆ ወጥቷል ተብሎ የሚወራውን ጉዳይም አቶ ተስፋሁን ፥ "ይሄ የውሸት መረጃ ነው፤ የኢትዮጵያ መከላከያ አንዳችም የአፀፋ እርምጃ አልወሰደም፤ያደረገውም ነገር የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ አንድ ነዋሪ በሰጡት አስተያየት ፥ አሁንም የተያዘው መሬት በሱዳን እጅ እንዳለ ገልፀዋል። "እስካሁን መፍትሄ ሳይገኝ ክረምት ገብቷል፤ ለማረስም አይታሰብም፤ ተስፋ ቆርጠን ያለን የሌለን ንብረት አጥተን ነው ቁጭ ብለን ያለነው" ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/BBC-05-08

@tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_መረጃ

የመቐለ ጊዜያዊ ከንቲባ የነበሩት አቶ አታኽልቲ አዲስ ሹመት እንደተሰጣቸው ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰተኛ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ ፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን አዲስ ሹመት ስለማግኘታቸው የተሰራጨው ዜና #ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል።

የቀድሞው ጊዜያዊ ከንቲባ ፥ "አሁን የመቐለ ነዋሪ ብቻ ነኝ ሲሉ" አስረድተዋል።

ምንጭ፦ www.addiszeyeb.com

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እስካሁን የዘጋችው ኤምባሲ አለ ?

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ የዘጋችው ኤምባሲ የለም” ሲሉ ዛሬ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙት ኤምባሲዎቿን እንደዘጋች የሚናፈሰው መረጃ #ሀሰት መሆኑን አስገንዝበዋል።

“ነገር ግን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደማንኛውም ተቋም ሪፎርም ላይ ይገኛል ” ያሉ ሲሆን የኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች መጥራት የተለመደ የስራ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ወደፊት የሚቀነሱና የሚዘጉ ኤምባሲዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግን ሳይጠቁሙ አላለፉም። #ENA

@tikvahethiopia
ቱርክ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ዘመቻ ድሮን ሰጥታለች ?

በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ፥ ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰራዊት ግልጋሎት ይውላሉ የተባሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን /ድሮኖች/ እያቀረበች ነው #ሀሰት ሲል አስተባበለ።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ለወታደራዊ ዘመቻ የሚሆኑ ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች ወደ አገር ውስጥ አስገብቷል የሚሉ ሪፖርቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭቶ ነበር።

ይህን ተከትሎ ነው ኤምባሲው ምላሽ የሰጠው።

በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ፥ "በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቱርክ ለኢትዮጵያ መንግሥት ድሮኖችን እያቀረበች ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሐሰት ነው" ብሏል።

በኢትዮጵያ ቱርክ አምባሳደር የሆኑት ያፕራክ አልፕ ፥ "በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የቱርክ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን ወይንም ድሮኖች በኢትዮጵያ የሉም።" ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#DireDawa : " ሙሉ እና ጎዶሎ በሚል የተጀመረ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም " - የት/ባለስልጣን

በት/ባለስልጣን የድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት ፥ በድሬደዋ የታክሲ አገልግሎት ሙሉ ጎዶሎ በሚል
መሰጠት ስለመጀመሩ እየተሰራጨ ያለው መረጃ
#ሀሰት ነው ሲል አሳውቋል።

ቅ/መስሪያ ቤቱ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከመሰል የሀሰት ማደናገሪያዎችበመጠበቅ አገልግሎት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉም አሳስቧል፡፡

የሚቀየሩ የአገልግሎት አሰጣጦች ሲኖሩ ከትራፊክ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት እንደሚወጡና ይህንንም በተቋሙ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅና በሌሎች ሚዲያዎች ይፋ እንደሚደረግ አሁን ላይ ግን ምንም አይነት የሙሉ ጎዶሎ አገልግሎት እንዳልተጀመረ እና እንደማይጀመር ገልጿል።

ከሰሞኑ በከተማው የታክሲ አገልግሎት ጎዶሎና ሙሉ በሚል እየተሰጠ አንደሚገኝ ተደርጎ ምንጩ ያልታወቀ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopia
#ሀሰት_ነው !

" ከሱዳን ጋር #በቅርቡ በድንበር ጉዳይ የተደረሰ ስምምነት የለም " - በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ሰሞኑን አንዳንድ ሚዲያዎች በሱዳን የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በመጥቀስ የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር በተመለከተ ስምምነት እንደተደረሰ ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በተለይ Alsharq AL-awsat English ጋዜጣ በድህረ ገፁ “Addis Ababa, Khartoum Reach Deal on Border Dispute” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ፌብርዋሪ 13 ቀን 2022 ያስነበበው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጣው የመረጃውን ምንጭ ሳይጠቅስ ያቀረበው ሲሆን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከዚህ ጋዜጣ ጋር ግንኙነት እንዳላደረጉ እና መረጃ እንዳልሰጡ ኤምባሲው ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ አዘዘ። የመጥሪያ ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። በነ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ የሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ነው መጥሪያ እንዲደርሳቸው የታዘዘው።…
#ሀሰት_ነው !

የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከእስር ተፈቱ እየተባለ በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው።

ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከተከሰሱባቸው የሙስና ክሶች መካከል የመርከብ ግዢ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ጋር ተያይዞ የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ ር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎችም የመከላከያ ምስክሮች እንዲቀርቡ በታዘዘው ትዕዛዝ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ፍርድ ቤቱ በቀጠሮ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከህዳሴው ግድብ ምንጣሮ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው ሌላኛው የሙስና ክስ ነጻ የተባሉ ቢሆንም በቀሪ ክሶች ግን በቀጠሮ ላይ ይገኛሉ።

ከእስር ተፈተዋል እየተባለ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰት ነው።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#ሀሰት_ነው !

" ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የለም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች " ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል አሉባልታ ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተዉ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪ ⬇️

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚኒስቴሩን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚሰረጩት መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በማወቅ በትኩረት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል። ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦ - በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣ - የመዝናኛ ሥራዎች፣ - ካፍቴሪያዎች፣ - ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን - የህፃናት መጫወቻ - አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ - የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።…
#አፄምኒሊክ #እቴጌጣይቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት መግቢያ ፊለፊት ላይ የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት እንደሚኖር ገልጿል።

ምኒሊክ አደባባይ የሚገኘው " የአፄ ምኒሊክ ሃይውልት ሊፈርስ ነው፤ ከቦታው ተነስቶ ወደ ሙዚየም ሊገባ ነው " የሚባለው ፍፁም #ሀሰት ሲል ገልጿል።

የከተማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ቃል ፤ " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊትለፊት ላይ ገና መግቢያው ላይ አለ፤ አዲስ ተጨምሮ። ያንን አዲስ የሚሰራ እንዴት ነው አሮጌውን የሚያፈርሰው ? ይሄ ያስኬዳል ? እንዴት ነው የበዓል ማክበሪያ ቦታ በዛ በኩል የሚደረገው ? " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " አፄ ምኒሊክ የራሱ ትክክል አይደለም የምንለው የሰራቸው ጥፋቶች አሉ ብለን እናምናለን። በዓድዋ ላይ ደግሞ የሰራቸው ትልልቅ ታሪኮች አሉ። አንድ የሆነ ጥፋት ካለ  ሌላውን ሁሉ እውነት በዛ እንሸፍናለን ማለት አይደለም። የሆነ እውነት ካለ በጥፋቱ ሸፍነን እናያለን ማለት አይደለም። ታሪክን ጥፋትም ይኑር በጎ ገፅታውን ፣ መልካም ገፅታውንም እንዳለ እውነቱን ማስቀመጥ ነው ከእኛ የሚጠበቅ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኛ አልሰራነው፤ ለምን የአሁኑ ትውልድ መከራውን እንደሚያይ ብዙ አይገባንም። እኛ አልሰራነው ፤ ይሄ ትውልድ አልሰራው የጥፋቱንም የጀግንነት ፓርቱንም ይሄ ትውልድ አልሰራውም። ግን የራሱ ሃገር ታሪክ ነው፤ የራሱ ህዝብ ታሪክ ነው በመልካምነት የሚይዘውን ይኮራበታል፤ ይይዘዋል፤ ያሳይበታል። ትክክል አልነበረም የምንለውን አንደግመውም፤ በእኛ ዘመን መደገም የለበትም። " ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች " አሮጌ አካባቢን ባደስን ቁጥር ቅርስ ፈረሰ ነው የሚባለው ይሄ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ የልማት እንቅፋት ሆኖብናል " ሲሉ አክለዋል።

የ " ዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት ከጥቂት ቀናት በኃላ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች…
#AmharaRegion

° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ

በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ላይ ግጭት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

በተደጋጋሚ ፦
- የሰዎች ደም በሚፈስበት፣
- ንብረት በሚወድምበት ፣
- ሰዎች ቄያቸውን ለቀው በሚፈናቀሉበት በዚህ ቀጠና ባለፈው የካቲት ወር ውስጥም በርካቶች መገደላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ #ከ8_ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ መባባሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመነሻው ላይ በሁለቱም በኩል እርስ በእርስ መወነጃጀል ያለ ሲሆን በኤፍራታ ግድምና ቀወት ውስጥ ግጭቱ ከፍቶ መዋሉ ነው የተሰማው።

በሁለቱም በኩል ያሉት ነዋሪዎች ፣ የአጣዬ ከንቲባ ፣ የአካባቢው አባገዳ ምን አሉ ?

በኤፍራታ ግድም ወረዳ የአላላ ከተማ ነዋሪ ፤ ጦርነት ከተጀመረ 8 ቀን መያዙን ፣  ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪው " የአርሶ አደሮች ዱቄት ሳይቀር ፣ በግ ፣ ፍየል ፣ ግመል ፣ አህያ፣ ከብት በሙሉ ሙልጭ አድርገው ወስደውብናል። ኃላሸት የሚባል ሰውም ገድለውብናል እኛው ክልል ላይ ገብተው " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ካደረጉ በኃላ ህዝቡ ተሬ እና ዘንቦ ወደሚባለው አካባቢ በለበሰው ልብስ ሸሽቶ ተጠልሎ እንደሚገኝ ገልጸዋል። " በተከታታይ 18 ሰዎችን ገድለውብናል "ም ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ነዋሪ ፤ " እስከ ጅሌ ጥሙጋ ባርሲሳ ፣ ካራ ሌንጫ ፣ መከና ወይም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከትላንትና ጀምሮ ተኩስ ነበር። ትላንት አንዲት ሴት እንዲሁም ግመልና ከብቶችም ተመተው ነበር ግጭቱ የቀጠለው በዚህ ነው፤ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰው ቆስለዋል፤ አንዱ ወደ አዳማ ተልኳል። ዛሬ ደግሞ 4 ሰው ሲሞት 3 ሰው ቆስሏል " ብለዋል።

ዋነኛው እቅዳቸው የጅሌ ጥሙጋ ከተማ #ሰንበቴን " እንይዛለን ፣ እናጠፋለን " የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የአጣዬ ነዋሪ ደግሞ ፤ ሰሞኑን ግጭት ተባብሶ ዛሬ አጣዬን በተኩስ ልውውጥ ሲያናውጥ መዋሉን ፣ 5 ሰው መገደሉም. ጥቃት ፈፃሚዎቹ የታጠቁ አካላት " ሸኔ " ናቸው ብለዋል።

ሌላው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የሰንበቴ ነዋሪ " ግጭቱ የጀመረው #መጋቢት_አንድ ላይ ነው። ይህም በጅሌጥሙጋ ኮላሽ የሚባል ስፍራ 1 ሰው ገድለው 2 ሰው አቁስለው ከብቶችንም ነድተው ከሄዱ በኃላ ነው ግጭቱን የተስፋፋው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከባልች ቀበሌ እስከ ሰንበቴ እና መከና አጣዬ ድረስ ጦርነት ነው። የዛሬውን ለየት ያደረገው ታጣቂዎቹ #ከሰሜን_ሸዋ ተሰባስበው ፤ እራሳቸውን አደራጀትው ሌሊቱን በተሽከርካሪዎች ተጉዘው መጥተው ውጊያ መክፈታቸው ነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 10 ቀናት 29 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረው የተወሰዱት ከብቶችና የወደመው ንብረትም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አስተያየት #አልቀበልም ያሉት የአላላ ነዋሪው ፤ " አማራው ሲያጠፋ በአማራው አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ፤ ከኦሮሞውም ሲያጠፋ አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ ሰላም የሚያሰፍነው ይሄ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህግ እና በሽምግልና  ነገሩ መክሰም አለበት እነሱ የሚሉት ከጨፋ ጀምሮ እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የኦሮሞ ቦታ ነው። አጣዬም #የኛ_ነች ፤ አላላም ፣ ሞላሌም ፣ ማጀቴም ... ሁሉም የኛ ነው የሚሉት። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ሊፈታው ይገባል " ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #አባገዳ አህመድ ማህመድ " መንገድ የለም። ከጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች እንዲሁም ከዞን መገናኘት አልቻልንም " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሃይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ተሰባስበው መፍትሄው ምንድነው ? ለማለት መንገዱ ተከፍቶ ለህዝቡ ምግብ ለማድረስ ፣ የቆሰሉትንም ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ ጥረት ላይ ነን። መንገድ ከተዘጋ 1 ወር ሊሆነው ነው። እኛም ሆነ መንግሥታዊ አመራሩ ሄደን ማየት አልቻልንም። የአማራ ክልልም #ታጣቂዎቹን_ስለሚፈሯቸው ቀርበው ለማነጋገር አልተቻለም። እኛ ጋር ያሉትን #ወሰናችሁን አልፋችሁ አትሂዱ እያልን እየመከርናቸው ነው ። " ገልጸዋል።

ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሮች ጥቃቱን የከፈቱት " ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ናቸው ቢሉም አባገዳ አህመድ " ሀሰት ነው " ብለዋል።

" ሀሰት ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እዚህ አልገባም። እየተዋጋ ያለው እራሱ ነዋሪው ነው " ብለዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባው ተመስገን ተስፋ ፤ ከተማዋና ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረጉት ብለዋል።

አጣዬ ላይ ' #ወረራ ' መፈፀሙን ገልጸው " ሰውም አልቋል፤ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለዋል።

ይህን የሚፈፅሙት ከአጎራባች  " #ሸኔ በሏቸው " ሲሉ የጠሯቸውን የታጠቁ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ዋናው መፍትሄ መንግሥት ጠንከር ብሎ #እርምጃ መውሰድ ያለበት ላይ እርምጃ መውሰድ ፤ ይሄ ነበረ መፍትሄው  አሁን ባለው መንገድ ፣ #በእሹሩሩ ሰውም አለቀ " ብለዋል።

#የአጣዬ_ህዝብ የገዛ ከተማው ላይ እንዳለ መአት እንደወረደበት የገለጹት ከንቲባው " እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንግስት ቢደርስልን ጥሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በኩል ለጥፋቱ ለችገሩ " የፋኖ ታጣቂዎችን " ተጠያቂ ሲያደርጉ ከሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ደግሞ " ሸኔን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ተጠያቂ ያደርጋሉ።

NB. ባለፉት አምስት ዓመታት አጣዬ ከ10 ጊዜ በላይ የመቃጠል አደጋ አስተናግዳለች።

እስካሁን የአማራ ክልል መንግሥት ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የቪ.ኦ.ኤ. ራድዮ (ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia