ቪድዮ ፦ ቱርክ እና ሶሪያ በሚወሰኑበት የድንበር አካባቢ ባጋጠመው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸውን ባለስልጣናት አሳወቁ።
ዛሬ ሰኞ ጠዋት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ አስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ እንዲሁም በሶሪያ በኩል ደግሞ ወደ 800 የሚደርሱ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል።
ቱርክ ከሶሪያ ጋር በምትዋሰንባት በደቡብ ምሥራቋ ጋዚያንቴፕ ግዛት ውስጥ ባጋጠመው በዚህ አደጋ በአጠቃላይ በሁለቱ አገራት ወደ ሁለት ሺህ እየተጠጉ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
የነፍስ አድን ሠራተኞች በፍርስራሾች ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ፈልጎ የማውጣት ሥራ እያከናወኑ ሲሆን፣ በዚህም የአደጋው ሰለባዎች ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቪድዮ ፦ Ahmit Sahu
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ መንግሥት በተርኪዬ በመሬት መንቀጥቀጥ ለደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገለፀ።
መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ፤ በደቡባዊ ተርኪዬ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት መውደም ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።
መንግስት ጉዳት የደረሰባቸው በቶሎ እንዲያገግሙ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ገልጾ ፤ " በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርኪዬ መንግሥት እና ህዝብ ጎን የምትቆም መሆኗን እንገልፃለን " ብሏል።

Photo
ፖሊስ ዛሬ ስለነበረው ሁኔታ ምን አለ ?
የአዲስ አበባ ፖሊስ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጠዋት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰላማዊ እንቅስቃሴን የማወክ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተስተውለዋል ብሏል።
በኦሮሚያ ልዩ ዞን ክልል ውስጥ በምትገኘው ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን የተሰበሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ገብተው " የታሰሩብን ሰዎች ይፈቱልን " በሚል ምክንያት በድንጋይ መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር እንዲከሰት ለማድረግ ሞክረዋል ሲል ገልጿል።
ፖሊስ ፤ " ምንም አይነት የታሰረም ሆነ የተያዘ ሰው እንደሌለ በመግለፅ የተዘጋው መንገድ እንዲከፈት ቢያሳስባቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም " ሲል አስረድቷል።
ከፖሊስ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ወጣቶች የታሰረ ሰው አለመኖሩን በማስረዳት መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ አካሉን እያገዙ በምክር እና በተግሳፅ የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም የተሰበሰቡት ሰዎች ከቦታው ለመንቀሳቀስ እና መንገዱ እንዲከፈት ፍላጎት አልነበራቸውም ብሏል።
ፖሊስ በመግለጫው፤ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወቅቱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ እንዲከፈትና ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል የማድረግ ስራ ሰርቷል ብሏል።
በዚህ ወቅት ግጭቱ እንዲፈጠር በግልፅም ሆነ በስውር ሲቀሰቅሱና በተባባሪነት ሲሳተፉ በነበሩ ሃይሎች በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ሲል አሳውቋል።
(የፖሊስ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#MoE
በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

#NEBE
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የተካሄደው የሕዝበ-ውሳኔ ድምፅ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ መደረጉን ገልጿል።
ቦርዱ የድምፅ ቆጠራው ትናንት ማታ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱም የድምጽ አሰጣጥ በተካሄደባቸው በ31 ማዕከላት ሥር በሚገኙ 3 ሺህ 771 ምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ጠዋት ለህዝብ ይፋ ተደርጓል ብሏል።

#ቱርክ #ሶሪያ
በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።
ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።

#Tigray
ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል፣ መቐለ እና ዙሪያው #የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በትግራይ ክልል በመቐለ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

#Tigray ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል፣ መቐለ እና ዙሪያው #የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፤ በትግራይ ክልል በመቐለ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች የሚገኙ 31 የባንኩ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል። ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የባንክ አገልግሎት ዛሬ አስጀምሯል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከብሄራዊ ባንክ ለክልሉ የተላከውን ብር ለቅርጫፎች በማከፋፈል በመቐለ ከተማ በሚገኙት ሁሉም ቅርንጫፎች እንዲሁም በዓብይ ዓዲ፤ ማይ ለሚን፤ ሳምረ፤ ግጀት፤ ሃይቂ መስሓል፤ወርቅ አምባ፤ አፅቢ እና አጉላዕ በሚገኙ በአጠቃላይ በ31 ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።
በተጨማሪም በዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ ቅርንጫፎች በቅርብ ሰዓታት ውስጥ ባንኩ የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የባንኩ መቐለ ዲስትሪክት አሳውቋል።
የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሥራ የጀመረባቸው አካባቢዎች የቴሌ መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች የተሟላባቸው ሲሆን፣ የተወሰኑ የቴሌ መሰረተ ልማት ጥገና ባልተጠናቀቀባቸው አካባቢዎች በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ አሳውቋል።
Photo Credit : CBE

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሁንም በብፁአን አባቶች እና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና እንግልት መቀጠሉን ገለፀች።
ቤተክርስቲያኗ ከቀናት በፊት በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ገልጻለች።
ቤተክርስቲያኗ የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ሐረገወይን ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው በሕክምና ሲረዱ ቢቆዩም ህይወታቸው ሊተርፍ እንዳልቻለ አሳውቃለች።
በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ ፤ በፓሊሶች ፊት በአጣና ጭንቅላቱን ተቀጥቅጦ በሀዋሳ በፅኑ ህሙማን ክፍል ሕክምና ሲደረግለት የነበረ አያሌው ተረፈ የተባለ ምዕመን በደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ማረፉን ገልጻለች።
በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሌሎችም ተጎጂዎች እንደሚገኙ የገለፀችው ቤተክርስቲያን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስረድታለች።
ከሰሞኑ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በሻሸመኔ ከተማ እስካሁን አጠቃላይ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር ቤተክርስቲያኗ ይፋ አላደረገችም።
ከዚህ ባለፈ ቤተክርስቲያኗ ፤ በሻሸመኔና አርሲ ነገሌ በሌሎችም ስፍራዎች የቤተክርስቲያን አባቶች፣ ምዕመናን ሰብአዊ ክብራቸው ተጥሶ ዛሬም በየእስር ቤቱ እንደሚገኙ አሁንም እየታሰሩ የሚገኙ መኖራቸውን አሳውቃለች።
መንግስታዊዎቹ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዝምታን መምረጣቸው እጅግ እንዳሳዘናት ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።
በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ ወደ ከፋ ሸካና ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከታቸው የተጓዙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ክልሉን አቋርጠው ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ በማገዳቸው ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ገልጻለች።