" ዕድሜ አጭበርብረዋል " የተባሉት አትሌቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።
ከጥር 23 -28/2015 ዓ.ም በአሰላ አረንጓዴው ስቴድዮም ከ #ሃያ (20) ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ ውድድር ላይ ከእድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተፈጥረዋል፤ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወሩ የነበሩ ፎቶዎችም በርካቶችን " እንዴት እኚህን የሚያክሉ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች ይወዳደራሉ " በሚል አስገርመዋል።
ይህን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት ፤ ከእድሜ በላይ ሆነው የተገኙ አትሌቶችን በሠነድ እና በአካላዊ ምርመራ ከውድድር ውጭ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ ቁጥራቸው ከ80 የሚልቁ አትሌቶችም ስማቸውን ይፋ አድርጓል።
ተግባሩን በፈፀሙ ቡድኖች አሰልጣኞች ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለየክልላቸው፣ ከተማ አስተዳደራቸው፣ ክለባቸውና ተቋሞቻቸው ፌዴሬሽኑ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ እንደሚልክ አሳውቋል።
ማጣራቱ እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ የሚቀጥል እንደሆነ የገለፀው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከዚህ ሲያልፍ ከሳምንትም ሆነ ከወር በኋላም ቢሆን ተጨማሪ መረጃ ከተገኘ አትሌቱ የተሸለመው ሜዳልያም ሆነ የገንዘብ ሽልማት ተመላሽ እንደሚደረግ በጥብቅ አሳስቧል።
የእድሜ ተገቢነት ችግር ውስጥ የተገኙ አትሌቶችን ዝርዝር ከሥር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? - የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ #በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል። - ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ…
#Update
የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ 10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ?
ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።
ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል ፦
- በመላው አገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉ ተቋማት ጋራ የሚሠራ፣ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
- በትግራይ ክልል በሚገኙት አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ተሠይሞ በሥራ ላይ የሚገኘው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተልዕኮውን እንዲፈጽም ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ #ሃያ_ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ተወስኗል።
- በወቅታዊ ችግር ምክንያት በመላው ሀገራችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ በአጠቃላይ ችግሮቹን በጥናት በመለየት፣ ቤተ ክርስቲያኗ ምእመናን ልጆቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የማጽናናትና የመጎብኘት መርሐ-ግብሮች እንዲደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
- መቐለ የሚገኘው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሠራተኞችን ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲለቀቅና በ2016 በጀት ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የሆነ የመማር ማስተማሩ የሥራ ሂደት እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- በኦሮምያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ስለተቋረጠ፣ በርካታ ምእመናንና ካህናት በእስርና እንግልት ላይ ስለሚገኙ በዚሁ መነሻነት ችግሮች እንዲቀረፉና ወደ መደበኛው የአሠራር መዋቅር እንዲመለስ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሠየም ከፌዴራልና ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
- የመንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር በተመለከተ በኢሉ አባቦራ የመቱ ፈለገ ሕይወት የነገረ መለኮት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት የተፈቀደ ሲሆን በሌሎች አህጉረ ስብከት ሊከፈቱ የታሰቡ ኮሌጆችን እና የአብነት ት/ቤቶችን መሠረታዊ ጥናት ተደርጎ ለ2016 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
- ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ፣ ጉልህና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው በኦሮምያ ክልልና በደቡብ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ 9 ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ወደፊትም ተደርበው በተያዙና አስፈላጊ በሆኑ አህጉረ ስብከት እንደአስፈላጊነቱ በመንበረ ፓትርያርክ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)