TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreechaa2019

ታላቁ “የሆራ ፊንፊኔ” የኢሬቻ ሩጫ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። ሩጫው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዘም ቢሮ ከ’ዲሲቲ ኢንተርቴይመንት’ ጋር በመሆን እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል።

በዚህ የሩጫ ውድድር ላይም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋቅጋሪ ተናግረዋል። እንደ አቶ አድማሱ ገለጻ የሩጫው ቲ-ሸርት በፌዴራልና በክልሉ በመሰራጨት ላይ ያለ ሲሆን ሽያጩም እየተካሄደ ይገኛል።

የአንድ ቲ-ሸርት ዋጋ 250 ብር ሲሆን የመሸጫ ቦታዎች በፌዴራልና በክልሉ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞንና በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኦሮሞ ባህል ማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። በክልሉ ሌሎች ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ በዞን እና በወረዳ እንዲሁም በሁሉም ከተሞች ባሉት የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የኢሬቻ በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ታዬ ግርማ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እና ከዚያ በፊት ለሚከበሩት ፌስቲቫሎች ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ኢሬቻ2012
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019 #TIKVAH_ETHIOPIA

ኢሬቻ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ነው በሚል ርዕስ ከመስከረም 18 ጀምሮ በኤግዚቢሽን ማዕከል የተዘጋጀውን ባዛር TIKVAH-ETH ተዟዙሮ ቃኝቶታል፡፡ በባዛሩ ላይ ልዩ ልዩ እቃዎች እየተሸጡ ሲሆን በብዛት ግን የባህል እቃዎችና በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጁ ቲሸርቶች እየተሸጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ባዛር ከሌላው ለየት የሚያደርገው ነገር ከተለያዩ አከባቢዎች የመጡ ባህላቸውን ለማስተዋወቅ የገቡ ተሳታፊዎችን መመልከት ችለናል፡፡ ይህም ለባህል ልውውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ተዟዙረን ለማየት እንደሞከርነው የአርሲ፣ የባሌ፣ የቦረና፣ የወለጋ እና የሌሎችም ባህላዊ መገልገያዎች እንደ ቆሪ( ለገንፎ ፣ ለጭኮ ማስቀመጫ የሚውሉ) ኤሌላን(በቦረና አከባቢ እንደ ቤት ማስጌጫ የሚጠቀሙበት) የከሎ( ራስ ለማስዋብ የሚያገለግል) ሜት(የሴት አንባር) ቡዳ(የቅቤ ማስቀመጫ) ባህላዊ ልብሶች፣ በተለያዩ ህብረቀለማት ያጌጡ ዘንጎች ለህዝብ ዕይታ ውለዋል፡፡ ከዛም በተጨማሪ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን በባዛሩ የተሳተፉ ሸማቾችም በመሳተፋቸው ደስተኛ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ይህ ባዛር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን በርካታ ሰዎች እየጎበኙት ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆራ ፊንፊኔ #Irreechaa2019

PHOTO: EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019 ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል!!

TIKVAH ETHIOPIA FAMILIES

PHOTO: HANI, FUAD & DIGO

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል!

PHOTO: FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019 ኢሬቻ ሆራ አርሰዲ! #ቢሾፍቱ

PHOTO: OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia