TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GurageZone : የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም 1ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ ምክር ቤት የዞኑን ዋና እና ም/ አፈጉባኤ እንዲሁም የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ ፣ የመንግስት ተጠሪ፣ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀድቃል።

Credit : DAVO

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደቡብ ክልል ? በደቡብ ክልል ስር ያሉ 10 የዞን እና 6 ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ክልሉን በሁለት ክላስተር ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቀዋል። እስካሁን በአዲስ ክልል ለመደራጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል በም/ቤቶቻቸውም አፅድቀዋል የተባሉት ፦ - የወላይታ ዞን፣ - የጋሞ ዞን፣ - የጎፋ ዞን፣ - የደቡብ ኦሞ ዞን፣ - የኮንሶ ዞን - የጌዲኦ ዞን - የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ - የቡርጂ…
#GurageZone

የጉራጌ ዞን መንግስት የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ለብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት ፦

" ... የጉራጌ ዞን በክልልነት ለመዋቀር ለፌደሬሽን ም/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው።

የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው።

የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት ዙሪያ አልተወያየም። በቀጣይ በጉዳዩ መቼ ውይይት እንደሚደግ አይታወቅም።

በማህበራዊ ሚዲያ ዞኑ የክላስተር መዋቅሩን አጽድቋል ፤ በሌላ በኩል አላጸደቀም ተብለዉ የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው።

ይህ በዞኑ አመራሮች ላይ ጫናን ለማሳደር የታሰበ ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone የጉራጌ ዞን መንግስት የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ለብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት ፦ " ... የጉራጌ ዞን በክልልነት ለመዋቀር ለፌደሬሽን ም/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው። የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው። የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት…
#GurageZone

በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው በሁለት አዲስ ክልሎች ለመደራጀት በየም/ቤቶቻቸው ወስነው ውሳኔውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ካቀረቡ ቀናት ተቆጥሯል።

በጋራ በአዲስ ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ውሳኔ አሳልፈው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል ግን የጉራጌ ዞን እንደሌለበት ይታወቃል።

ዞኑ ከአጎራባቾቹ ስልጤ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ፣ ሀዲያ፣ ሀላባ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ ጋር ነበር በአንድ ክልል ይደራጃል ብሎ መንግስት አቅጣጫ አስቀምጦ የነበረው።

ነገር ግን የዞኑ ም/ቤት እስከ ዛሬ ድረስ በጉዳዩ ላይ አልተወያየም፤ አዲሱን አደረጃጀት አላፀደቀም ፤ ከዚህ በፊት ዞኑ እንደገለፀው የክልልነት ጥያቄን ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ ነው።

መንግስት በአሁን ሰዓት ዞኑን በክልል ለማደራጀት እንደሚቸገር በመግለፅ ከአጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳ ጋር ነው ክልል እንዲሆን ሀሳብ እያቅረበ መሆኑ ተሰምቷል።

የዞኑ ህዝብ ግን በክልል የመደራጀት ጥያቄው ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ መሆኑንና ለጠየቀው ህጋዊ የሆነ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጠው ፤ የ " ጉራጌ ክልል " አደረጃጀትም ተግባራዊ እንዲሆንለት በተለያየ መንገድ እየጠየቀ ይገኛል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ አንቂዎች ፤ የአካባቢ ነዋሪዎች መንግስት በሰላማዊ እና ህጋዊ መንገድ እየተጠየቀ ላለው የክልልነት ጥያቄ ህጋዊ መልስ እንዲሠጥ ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ከክልል እንሁን ጥያቄ ጋር በተያያዘ በዞኑ መቀመጫ በ ' ወልቂጤ ' የስራ ማቆም አድማ መመታቱ ተሰምቷል።

በከተማይቱ ባንኮች ፣ የተለያዩ መ/ቤቶች፣ የንግድ እና የትራንስፖርት እንደቆመ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ፎቶ ፦ ጀማል ሞሀመድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ " መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል። የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ…
#GurageZone

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ በክልል የመደራጀት ውሳኔን ማፅናቱና የክላስተር አደረጃጀቱን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ መሆኑን ደስታውን ሲገልጽ ግን በሰላማዊ መንገድ መሆን እንዳለበት በዞኑ የተቋቋመው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አሳስቧል።

ኮማንድ ፖስቱ ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናንት ኮሎኔል ፈጠነ ፍስሃ ፤ የጉራጌ ዞን ም/ቤት በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሀሳብን በአብላጫ ድምጽ ውድቅ ማድረጉን ገልፀው ምክር ቤቱ በክልል የመደራጀት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ህብረተሰቡ ደስታውን ሲገልጽ በሰላማዊ መንገድ መሆን አለበት ብለዋል።

የዞኑ ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

በቀጣይ የዞኑ ም/ቤት ያጸደቀው በክልል የመደራጀት ውሳኔ መንግስት ምላሽ እስኪሰጥበት ድረስ የዞኑ ህዝብ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

በተጨማሪ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ፤ የዞኑ ምክር ቤት የክላስተር አደረጃጀትን በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ መንግስት በቀጣይ አቅጣጫ እስኪያስቀምጥ እና ውሳኔ እስኪሰጥ የዞኑ ህዝብ ሰላሙን በመጠበቅ በልማት ስራው ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው ከዞኑ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#SNNPRS #GurageZone

" ሰዎች ለምን የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ በሚል እየታሰሩ ናቸው " - ነዋሪዎች

" ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የደቡብ ክልል ፖሊስ

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

እየታሰሩ ከሚገኙት መካከል በዞኑ በኃላፊነት ቦታ ያሉ ጭምር መሆናቸው ተጠቁሟል።

ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አቶ በላቸው ገብረማርያን የተባሉ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ የዞኑ ነዋሪ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ 13 ሰዎች እንደታሰሩ ከነዚህ ውስጥ ልጃቸውም እንደሙገኝበት ገልፀዋል። እሳቸውንም ፖሊስ እያፈላለገ መሆኑን አመልክተዋል።

እስሩ እየተካሄደ ያለው ለምን " የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ " በሚል እንደሆነ አንዳችም ወንጀል እንዳልተፈፀመ ተናግረዋል።

አንድ የወልቂጤ ነዋሪ ደግሞ ወንድማቸው ለወቅታዊ ስበስባ ተብሎ ተጠርቶ መታሰሩን ገልፀዋል።

የደቡብ ክልል ፖሊስ የዞን ስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎች መታሰራቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ አረጋግጧል።

የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ለሬድዮ ጣቢያው ተከታዩን ቃል ሰጥተዋል ፦

" ... ማንም ሰው ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በአግባቡ በስርዓት መጠየቅ መነጋገር፣ መወያየት፣ መወሰን መብቱ ነው ነገር ግን ተቀጥረው ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት ነው የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ምርመራ እየተጣራባቸው ነው። አሁን በአካባቢው የተለየ የፀጥታ ችግር የለም "

ያንብቡ : https://telegra.ph/VOA-08-24

@tikvahethiopia