TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BREAKING

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዳስታወቁት፥ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ ክልል አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች ያለምንም ችግር እንዲደርስ ወቅቱን የሚመጥን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ተጠይቋል ብለዋል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥያቄውን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማቅረቡን ገልፀዋል።

ይህ ጥያቄ የቀረበው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች ፣ ከቢሮ እና ዞኖች አመራር አባላት፣ በተለያየ ቦታ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ምሁራን፣ ከባለሀብቶችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ምክክር ካደረገ በኋላ ነው ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ENA-06-28-2

#ኢዜአ

@TIKVAHETHIOPIA
#ETHIOPIA

ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ እና ችግሩን በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ላይ ከተጠቀሱ #ወሳኝ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

• ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች በእለት ተእለት ኑሮዋችው ላይ እየገጠማቸው ያለውን ችግር መቀረፍ እንደሚገባ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተማማኝ እና ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ፣ እንዲሁም የመሰረተ ልማት እና የመሰረታዊ አገልግሎቶችን ዳግም ስራ ለማስጀመር አስቻይ የሆነ ሁኔታ በፍጠነት ለመፍጠር ፤ #የተኩስ_አቁም_ስምምነት ላይ በአጭር ጊዜ ላይ መድረስ እንደሚገባ አጽኖት ሰጥቷል።

• ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችል እና ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶች መሰረት የሚጥል የሰላም ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት በማድረግ የምክረ ሃሳብ ሰነድ አጽድቆዋል።

• የሰላም ምክረ ሃሳቡ በተቻለ ፍጥነት ለአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ወኪል እንዲቀርብ ወስኗል።

• ወደተኩስ አቁም ስምምነት ሲገባ በሚፈጠረው አስቻይ ሁኔታ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በተቻለ_ፍጥነት መልሶ ማቅረብ ይቻል ዘንድ፣ አስፈላጊ ቅደም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጿል።

• የአፍሪካ ህብረትም የሰላም ንግግሩ በአስቸኳይ ተጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻል ዘንድ፣ የሰላም ንግግሩ የሚካሄድበትን ቦታ እና ጊዜ በፍጠነት ወሰኖ ንግግሩ እንዲጀመር፣ ይህን ማድረግ ይቻል ዘንድ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ ገምግሟል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia