TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የጥላቻ_ንግግር የሚያሰራጩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩና በማህበራዊ ሚዲያ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል። የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ ምክር ቤቱ በአሜሪካና በመላው ዓለም የኢትዮጵያውያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እየሠራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም HR-128 የተሰኘው የውሣኔ ሐሳብ በአሜሪካ ኮንግረስ እንዲፀድቅ መሥራታቸውን አስታውሰው አሁን በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በመደገፍ ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ እየሠሩ መሆኑንም አቶ አምሳሉ ተናግረዋል።

Via #አዲስ_ዘመን
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፎካካሪ ፓርቲዎች!

ግንቦት 2011 ዓ/ም-107 ፓርቲዎች
ነሀሴ 2011 ዓ/ም-137 ፖርቲዎች


አቶ ኤፍሬም ማዲቦ፦

• በኢትዮጵያ ሰዎች በፓርቲ ውስጥ መደራጀትን የሚያገናኙት ከኢኮኖሚ ጥቅም መኖሩ ነው ቁጥሩን ያበዛው፣

• በቅርቡ እንኳ ከምርጫ ቦርድ ጋር የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ድርድር ላይ የውሎ አበል ስጡን ብለው መንግስትን የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ምን ያህል ለጥቅም የቆሙ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው፣

• የፖለቲካ ፓርቲ በየትኛውም አገር ውስጥ ሲመሰረት በህዝብ ድጋፍና በአባላት መዋጮ ድጋፍ እንጂ በመንግስት አይደለም። በተቃራኒው በኢትዮጵያ ውስጥ ግን መንግስት ሲሸፍንላቸው መቆየቱ፣

• እያንዳንዱ ብሄር የእኔን ጥቅም የሚያስጠብቀው በብሄር የተደራጀው ነው በሚል ሁሉም በየዘውጉ እንዲደራጅ ምክንያት መሆኑ

• 100 ፓርቲ በመጪው ምርጫ ቢወዳደሩ ፓርቲዎች በመከፋፈላቸውና ድምጻቸው በመበታተኑ ምክንያት ብቻ ኢህአዴግ ተመልሶ ስልጣን ላይ እንዲመጣ ሊያደርግ ይችላል፣

• ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባላት አገር ከ10 ሺ በላይ ፊርማ ማሰባሰብ በጣም አነስተኛ ቁጥር ነው። ይህን የተቃወመ ሁሉ አለ።

• እኛም አገር ፓርቲ የቤተሰብ ፓርቲ ማለትም አባት ፕሬዚዳንት እናት ገንዘብ ያዥ፣ ወንድም የህዝብ ግኙነት ሀላፊ የሆነበት ፓርቲ ይዘን የትም አንደርስም።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EPA-08-12

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሃይ” ባይ የሚሻው የዋጋ ንረት!

አሁን ያለው የገበያና ግብይት ሁኔታ ማነጋገር ከጀመረ ሰንብቷል። በተለይም በከተሞች ያለው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሸማቹን አናት እያዞረ፤ አቅሙን እያሽመደመደ፣ ኑሮውን አደጋ ላይ እየጣለና ህልውናውን እየተፈታተነው ይገኛል።

የሰሞኑንም ሆነ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲከሰቱ የነበሩትን ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎችንና ንረትን ቀረብ ብሎ ለተመለከተ በአንድ የገበያ ስርአት ውስጥ አበይት የሆኑ ባህርያትን – መንግስት፣ ህዝብና ነጋዴው – እየተናበቡ ሳይሆን እየተገፋፉ፣ እየተቀራረቡ ሳይሆን እየተራራቁ መሆናቸውን፤ ይህም የገበያ ስርአት አልበኝነትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ መረዳቱ የግድ ነው። ለዚህ ደግሞ የግብይት ስርአቱ ሙሉ ለሙሉ በአንድ ወገን ተፅእኖ ስር መውደቁን ያሳያል።

የዚህ ስርአት አልበኝነት መንሰራፋት ለህገ ወጦች በተለይም ለደላላው ክፍል ሰፊ የመፈንጫ ሜዳን ያመቻቸ፣ ለሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ሲሆን የእነዚህ ድምር ውጤትም ሸማቹን እያማረረው ይገኛል። በዚህ ላይ የገንዘብ ግሽበት፣ የገበያ አሻጥር፣ ድህነት ወዘተ ሲጨመርበት ደግሞ ጉዳዩ ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።

የመጫወቻ ካርዱን “ነፃ ገበያ” ካደረገው የአገራችን የንግድና ግብይት ስርአት የታሪፍ ህዳግም ሆነ የምርቶችና የአገልግሎቶች የመናሻ ዋጋ የሌለው መሆኑ የመግዛት- መሸጡን ሂደት ቅጣንባሩን አጥፍቶታል። ይህም ለህገ- ወጥ ደላላውና በገንዘብና ንግዱ ዘርፍ የበላይነትን ለያዙ ጥቂት ወገኖች ምቹ የመፈንጫ ሜዳን ፈጥሮላቸዋል። ለሸማቹ ደግሞ በተቃራኒው።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-26
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ!

• ግጭትን በመሸሽ ወይም በማምለጥ ከቶውንም ለውጥ አናመጣም። የተሻለ አገርና ቤትም አንገነባም።

• ብዙ ጊዜ ግጭትና ግፊት የሚመጣው አለቅጥ ምቾት ከመፈለግና በተቃራኒው በጎረቤታችን ያለው ልዩ ምቾት በሚፈጥርብን ቅንዓት ነው።

• ግጭት ለምን ተነሳ አይባልም ። ጉርብትና በራሱ፣ አብሮ መኖር በራሱ፣ የሚያማዝዘው ቅራኔ አይጠፋምና።

• ግጭት እንዴት ሊነሳ ቻለ ብሎ መፍትሔውን መፈለግና እንዴትነቱን ማጤን ከአስተዋይ ልብ ይጠበቃል። አሁን ከእኛ የሚፈለገው ይህ ነው።

• የሰው ልጅ በራሱ ከራሱ ጋርም ይጋጫል። ሰው በህይወቱ የሚያጋጥመውን ነገር፣ በሥርዓት ማየት ሲያቅተው ከራሱ ጋር ይጋጫል። በአንድ ጊዜ ሁለት ሶስት ነገሮች ተደራርበው ሲገጥሙት ወይም አንዱን ችግር ተጋፍጦ ሳያበቃ ሌላኛው ሲጨመርበትና ለውሳኔ ሲቸገር ከመፍትሔው ይልቅ ችግሩ ላይ ሲያፈጥ በግለ ግጭት ውስጥ ገብቶ ይወጠራል።

• አንደኛው በተፈጠረብን ምቾት ሳቢያ የበለጠና የተሻለ ምቾት ፍለጋ የጎረቤት ድንበር እንገፋለን ፤የጎረቤት ሰው እንጋፋለን፤ ግጭትም ይፈጠራል። በሌላ ወገን ደግሞ፣ ለፍቶ ጥሮ ግሮ ያገኘው ሃብት ዓይኖቻችንን ሲያቀላብን የሌላውን መልካም ቤት ፣ መኪና፣ ሰው እንደፍራለን፣ እናንጓጥጣለን። በሁሉም ረገድ ግን ግጭታችን የፍላጎቶቻችን እስረኞች ከመሆን የሚመነጭ የሰብዕና ግድፈት የሚመነጭ ዋልጌነት ነው።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-03-2