TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጎንደር🕊

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #አደባባይ_ሙሉጌታ ከአብመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ዞኑ ወደ #ተረጋጋ ሕይወት መመለሱንና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የዞኑን ሕዝብ ዕድገት እና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ በማንነት ስም እየማሉና እየተገዘቱ ባሉ ጥቅመኞች የተሳሳተ አስተሳሰብ የተወለደ ግጭት ምክንያት የሰዎች ሕይወት ማለፉ፣ ንጹኃን ለጉዳት መዳረጋቸው፣ በርካታ ንብረቶች መውደማቸውና ሰዎች ቤት ንብረታቸውን አጥተው መፈናቀላቸው ትውልድ የማይዘነጋው የቅርብ ጊዜ ታሪክ መሆኑን ነው ዋና አስዳዳሪው ያስታወቁት።

በርካቶችም ለሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ያብራሩት አቶ አደባባይ ‹‹ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ከእርሻ ማሳቸው ርቀው ጉልበታቸውን አቅፈው በባይተዋርነት ተቀምጠዋል›› ነው ያሉት። ችግሩን ለመፍታት መንግሥትና ሕዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሠሩ እንደሆነና በተሠራው የሰላም ማስከበር ተግባር በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል። በዞኑ ይስተዋላሉ የነበሩ ‹‹የግድያና እና ተደራጅቶ የመጠቃቃት፣ የመፈናቀል እና ሌሎች ወንጀሎችን ማስቆም ተችሏል›› ብለዋል።

ተዘግተው የነበሩ 12 ትምህርት ቤቶች፣ ሦስት የጤና እና ሁለት የሕግ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ገልጸዋል። ከፍተኛ የስጋት ምንጭ የነበሩ ዋና ዋና መንገዶችም ከስጋት ነጻ ሆነው ሰላማዊ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተነግሯል።

በግጭቱ ወቅት ተዘርፎ የነበረ አምስት ሺህ የሚጠጋ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ለባለቤቶቻቸው መመለሳቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። በዞኑ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ በግጭቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ማደኛ ወጥቶባቸው የነበሩ 46 ግለሰቦችና ሌሎች 68 እጅ ከፍንጅ የተያዙ ግለሰቦች በድምሩ 114 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በሕግ አግባብ እየታዬ እንደሚገኝና ውሳኔም እንደ ጥፋታቸው ተሳትፎና እንደ ነፃነታቸው የሚወሰን እንደሆነ አስረድተዋል። የተፈናቀሉ ወገኖችን በቋሚነት በማቋቋም ሰላማዊ ኑሮ እንዲጀምሩ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከመላው የዞኑ ሕዝብ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ጋር ውይይት መደረጉንና በውይይቱም መሠረት ሕዝቡ የሰላምን አስፈላጊነት በመረዳት እርቀሰላም እንዲወርድ መጠየቁን ለአብመድ ተናግረዋል።

በተወሰኑ አካባቢዎች በአማራ ብሔርና እና ቅማንት ማኅበረሰብ መካከል እርቀ ሰላም መውረዱን ያስታወቀት አቶ አደባባይ ‹‹የተፈናቀሉትን በዘላቂነት ወደ ቀያቸው ለመመለስ በዞኑ የሚገኙ
ሁሉንም የአማራንና የቅማንት ማኅበረሰብ ለማስታረቅ እየተሠራ ነው። ይህንን እርቅ ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ ወገን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ እናቶች እና ነዋሪዎች የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቁሟል›› ብለዋል።

ኅብረተሰቡን በቋሚነት ለማቋቋም ዞኑ 15 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ቀበሌ ድረስ እንቅስቃሴ እንደጀመረና ሕዝቡም ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛነቱን እያሳየ መሆኑንም ዋና
አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ የአይን እማኝ...

"ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ ስንደርስ ያልተፈቀደ አርማ ያለበትን ልብስ ለብሳችኃል/ይዛችኃል/ በሚል አታልፉም አሉን/የፀጥታ አካላት/። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የለበሱም ነበሩ እሱን እንዲህ ሆነን ማለፍ እንደማንችል ተነገረን። መዘምራንም ጭምር። ይሄን አርማ ይዛችሁ እና ለብሳችሁ ማለፍ አትችሉም አሉን። እዛው የነበርነው ሰዎች እንደዛ ከሆነ እዛው ኪዳነ ምህረት እናበራለን ብለን ተመለስን። ወደኪዳነ ምህረት ስንመለስ ወደአዳባባይ የሄዱት ሰዎች አንድ ደብር ጎሎ #አናበራም ብለው ሁሉም ተሰብስቦ ወደ ኪዳነ ምህረት እየተመለሰ ነበር #አደባባይ ያለውን ሳያበሩ ቀርተው። ግማሹ ኪዳነ ምህረት ከሄደ በኃላ እላይ ያለውን ወደታች እንዳይወርድ ታች ያለውን ወደ ላይ እንዳይወጣ ከለከሉ። ሰዎች ወደቤት አንሄድም አሉ። ሰዎችን አሳምነውም ወደአደባባይ ለመውሰድ እና ደመራው እንዲበራ ለማድረግ ጥረት አድርገው ነበር ግን ሰው አልተስማማ። እየዘመርን ወደቤታች እንመለሳለን ብሎ እኛ ወደቤታችን ሄደናል።"

ቢሾፍቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር አልተሳካም። #BISHOFTU #ቢሾፍቱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia