TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተቃውሞ ሰልፉ ሳይካሄድ ቀረ‼️

በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የጸደቀውን የስደተኞች አዋጅ #በመቃወም በጋምቤላ ክልል ተወላጆች ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ሰልፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ ሳይካሄድ ቀርቷል። ረፋድ 3፡30 ገደማ ከ35 እስከ 40 የሚሆኑ የጋምቤላ ክልል ተወላጆች በመስቀል አደባባይ ቢሰባሰቡም ፍቃድ ያገኙበትን ደብዳቤ ለጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች ማቅረብ ባለመቻላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የጸደቀው አዋጅ በጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ እና፣ ህዝቡ ተወያይቶ #መግባባት ላይ ያልደረሰበት መሆኑ ሰልፍ ለማድረግ እንዲነሳሱ እንዳደረጋቸው በቦታው የጀርመን ድምፅ ራድዮብያነጋገራቸው ወጣቶች ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ሊካሄድ የነበረው ሰልፍም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለው የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ባለመሆኑ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ አለመከናወኑን የጀርመን ድምፅ ራድዮ በስልክ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ #አረጋግጠዋል

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ👆

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት አንድ ተማሪ መሞቱን ተማሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ። ሟች ሰዓረ አብርሃ እንደሚባልና የሶስተኛ ዓመት የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ተማሪ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

በዩኒቨርስቲው ከዓርብ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት እስከዛሬ ድረስ #አለመረጋጋቱን ተማሪዎቹ ገልጸዋል።

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ደሳለው ጌትነትም በተቋሙ ከባለፈው አርብ 11 ሰዓት ጀምሮ ግጭቶች መኖራቸውን #አረጋግጠዋል

በዚህም አርብ ግንቦት 16 ላይ 3 ልጆች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረው ልጆቹ አሁን ሆስፒታል ይገኛሉ ብለዋል። የተጎዱት ተማሪዎች በባህርዳር እና አዲስ አበባ ሪፈራል ተጽፎላቸው ወደዚያው መወሰዳቸውንም ጨምረው ያስረዳሉ።

በግጭቱ ሁለት ተማሪዎች በድንጋይና በዱላ ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን እማኞቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል

በተፈጸመበት ጥቃት ምክንያት አንደኛው ተማሪ ወድያውኑ ህይወቱ ማለፉንና ሌላኛው ተማሪ ደግሞ ለህክምና እርዳታ ወደ ባህርዳር መወሰዱን ከተማሪዎቹ መረዳት ተችሏል።

የረብሻውን ምክንያት እስካሁን ማረጋገጥ አልቻልንም ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አርብ ዕለት ተሳትፎ የነበራቸውን የተወሰኑ ልጆች ፖሊስ ተከታትሎ ከግቢ ውጭ ይዟቸው ፖሊስ ጣቢያ ስለሚገኙ ጉዳያቸው እየተጣራ ነው በማለት የግጭቱ መንስኤ ከዚያ በኋላ ተጣርቶ የሚታወቅ ይሆናል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ የተጠለሉ ተማሪዎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን ትላንት የሟችን አስክሬን ለመሸኘት የተሰበሰቡ ተማሪዎችም "ትምህርቱ ይቅርብን ወደ መጣንበት መልሱን" በማለት ለዩኒቨርሲቱው ፕሬዚዳንት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው በፖሊስና የፌደራል ጸጥታ ሃይሎች እገዛ ደህንነታችሁ ለማስጠበቅ እንሰራለን በማለት ምላሽ መስጠታቸውን ተማሪዎቹ ይናገራሉ።

አሁን ረብሻ የለም፤ ተማሪዎች ግን ወደ ትምህርትም ሆነ ወደ ጥናት የሚያመሩበት ሁኔታ የለም። ችግሩ ስለማይታወቅ ከፖሊስ ጋር ችግሩን በመለየትና መፍትሔ ለመስጠት እየሠራን ነው ያሉት ደግሞ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ናቸው።

ግጭቱ በብሔር መካከል የተነሳ አይደለም የሚሉት ኃላፊው ትምህርት አለመጀመሩን አረጋግጠው የመማር ማስተማሩ ስራ ግን ማክሰኞ ይቀጥላል ብለዋል።

ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ የተላከው የሟች ተማሪ አስከሬን ዛሬ ከሰአት ወደ ትውልድ ስፍራው ትግራይ ሽረ እንዳስላሴ ከተማ እንደሚላክ አንድ ስሟ እንዲገለጽ ያልፈለገች ተማሪ ለቢቢሲ ተናገራለች። አቶ ደሳለው በበኩላቸው አስከሬኑ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ እንዳልተላከና ወደ ቤተሰቦቹ እንደተሰኘ ገልፀዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪ ከጤና ሚኒስትሯ ውጭ #ሁሉም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ለቢቢሲ #አረጋግጠዋል

በኮቪድ-19 የተያዙት ሁሉም ሚኒስትሮች በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሲሆን በሙሉ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የባለስልጣናቱ ጠባቂዎች እንዲሁም ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥም ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኮቪድ-19 ተይዘዋል የሚለውን ሪፖርት #አጣጥለውታል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ ሱዳን ሌላኛው ምክትል ፕሬዝዳንት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀምስ ዋኒ ኢጋ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን #አረጋግጠዋል

ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀምስ ዋኒ ኢጋ ከዚህ ቅደም በቫይረሱ የተያዙትን ዶክተር ሬክ ማቻር (ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት) ፣ ሁሴን አብድልበጊ አኮል (ምክትል ፕሬዘዳንት) ፣ አንጅሊና ቴኒ (የመከላከያ ሚኒስትር) እንዲሁም ሌሎች የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀላቅለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች 'በጥይት ተመትቶ' ህይወቱ አልፏል።

አርቲስት ሃጫሉ በዛሬው ዕለት ምሽት 'ገላን ኮንዶሚኒየም' አካባቢ በጥይት መመታቱንና ህይወቱ ማለፉን በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን 'ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር' #አረጋግጠዋል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራው ሳይጠናቀቅ ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ሲሉ #አረጋግጠዋል

በሌላ በኩል ፦

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራሉ እና የክልሉ መንግሥት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ንግግር እንዲመለሱ ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ ማህማት ጠይቀዋል፡፡

ግጭቱን ለመፍታት የሚደረግን ማንኛውም ጥረት ለማገዝ የአፍሪካ ኅብረት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገሪቱ ወደ ዕርስ በዕርስ ግጭት ውስጥ እንዳታመራ ኅብረቱ ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ባለፈው እሁድ ጥሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" ... የት እንኳን እንዳለ አላውቅም። #መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " - አባ ገዳ ጎበና ሆላ

የቱልማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) አባል የሆነ ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ።

ከ1 ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል ፣ የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን የ ‘ ሸኔ ’ ቡድን አባል ነው የተባለውን የአባ ገዳ ጎበና ልጅ " ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል " ብሎ ነበር።

ኮሚኒኬሽኑ " የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ (ፎሌ ጎበና) ላይ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል  " ነው ብሎ የነበረው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ ምን አሉ ?

- የልጃቸውን የመገደል ዜና የሰሙት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሆነ እና እስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

- የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን #አረጋግጠዋል

- ልጃቸው ፎሌ ጎበና ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ 6 ዓመታት ማለፉን ገልጸዋል።

- " ከ6 ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት " ብለዋል።

- " የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " ብለዋል።

- ልጃቸው ሰላማዊ ሰዎች እየዞረ እንደሚገድል በመንግሥት የቀረበበትን ክስ በተመለከተ ፥ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

- " እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም ፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከ6 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት " ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባ ገዳው 7ኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@tikvahethiopia