TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሜሪካ ...

የግድያ ወንጀል ስትዘግብ የነበረችው ጋዜጠኛ ተገደለች።

አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ በኦርላንዶ ፍሎሪዳ አቅራቢያ ትላንት ከሰዓታት በፊት የተፈጸመን የግድያ ወንጀል እየዘገበች በነበረችበት ወቅት #በጥይት ተመታ መገደሏን ቢቢሲ አስነብቧል።

ጋዜጠኛዋ የተገደለችው እየዘገበችው በነበረው የግድያ ወንጀል #ተጠርጣሪ (ስሙ ኬዝ ሞሰስ 19 ዓመቱ) ነው።

ከጋዜጠኛዋ በተጨማሪ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ በተተኮሰባት ጥይት #ተገድላለች

ሌላኛዋ ጋዜጠኛ እና የታዳጊዋ እናት በተመሳሳይ ታጣቂ ተመትተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ ገልጿል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች " ስፔክትረም ኒውስ " ለተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሰሩ ሲሆን በአካባቢው የጣቢያው 13 ጋዜጠኞች የአንድ ሴትን ግድያ ሲዘግቡ ነበር።

ግለሰቧን (እድሜዋ በ20ዎቹ ሲሆን መኪና ውስጥ ነበረች) የገደለው ተጠርጣሪ ተመልሶ መጥቶ እንደተኮሰባቸው ፖሊስ ገልጿል። ጋዜጠኞቹ ግድያው የተፈፀመበት ቦታ ደርሰው ሲዘግቡ ነበር።

እነሱም ኢላማ ተደርጎባቸው ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።

ተጠርጣሪው ጋዜጠኞቹ ላይ ከተኮሰ በኋላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቤት ገብቶ አንዲት ህፃን እና እናቷ ላይ ተኩስ ከፍቶ ህጻኗን ሲገድል እናትየው በአስጊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ወቅት የጦር መሳሪያ ይዞ እንደነበርና ከፖሊስ ጋር ባለመተባበር እምቢተኝነቱን ማሳየቱን መርማሪዎች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በመላው #አሜሪካ በጦር መሳሪያ በሚደርሱ ጥቃቶች በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ።

@tikvahethiopia