TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update መግለጫው ተሰርዟል⬇️

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር #ስመኘው_በቀለን አሟሟት እና የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ምርምራን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ #ተሰረዘ። መግለጫ የተሰረዘው የፌደራል ጠቅላይ ዋና አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ #አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ ባልደረባ ለዲ ደብሊው እንደተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሄዳቸው መግለጫው ለሌላ ጊዜ #ተላልፏል።” መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ቢነገርም ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልተነገረለትም። በዛሬው መግለጫ የኢንጂነር ስመኘው #አሟሟት እና ከሰኔ አስራ ስድስቱ ቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።

ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ሲዘዋወር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. ይሰጣል ተብሎ የነበረው መግለጫ ወደ ዛሬ ጳጉሜ 1 መተላለፉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰንደቅ አላማ ቀን አከባበር መርሀ ግብር #ተሰረዘ። ከሰንደቅ አላማ ጋር ተያይዞ ያለውን አለመግባባት ታሳቢ በማድረግና አላስፈላጊ #ግጭት ላለማስነሳት የዘንድሮው የሰንደቅ አላማ ቀን አከባበር መሰረዙን የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴው ተናግሯል። በዓሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወስጥ እንግዶች በተገኙበት #ታስቦ ይውላል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ #ይነሳ #አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ…
#Update

ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia