TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ዋስትና ታገደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

የተጠቀሱባቸው #የሕግ ድንጋጌዎች #ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiop
#StateofEmergency #EHRC

" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።

ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።

በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

@tikvahethiopia