TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ክልል⬇️

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል በተሰራው ስራ የተለያዩ ሕጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

#ሱሉልታ

በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡

#ሻሸመኔ

ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ቡራዩ

የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት ሲጠይቅ የነበረ፣ ቲተር: ማዕተምና የመታወቂያ ወረቀት በቄሮ ስም አዘጋጅቶ በመሸጥ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#ለገጣፎ_ለገዳዲ

በቄሮ ስም የ62 ወጣቶችን ፎቶ በማሰባሰብና ወረቀት ላይ በመለጠፍ የቄሮ አደረጃጀት ከቀበሌ እስከ ላይ መኖር አለበት በሚል ወጣቶችን
ሲያታልሉና ሲያደረጁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ጅማ

በሕገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሕገ ወጥ ግንባታ ሲያካሄዱ የነበሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰዎች ላይ ሙሉ መረጃ ተሰባስቦ ለሕግ ሊቀርቡ ነው፡፡
ድንገት በተደረገው ፍተሻም 2ሽጉጥና 180 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

#አዳማ

በቅርቡ በከተማው ለተከሰተው ግጭት መነሻ በመሆን ሰዎችን ሲያነሳሱ የነበሩና ግጭቱ የብሔር መልክ እንዲይዝ አድርገዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ሞጆ

ጨለማን ተገን በማድረግ ፋብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአንደኛው ግለሰብ እጅ ሽጉጥ ተይዟል፡፡

#ሰበታ

በሕገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሰማሩ፣ ምግብ ቤት ገብተው በመመገብ ሒሳብ የማይከፍሉና ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሞጆ

ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም


ዛሬ ጠዋት በሞጆ ከተማ በተከሰተ ሁከት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመተዋል። በከተማዋ ዛሬ ጠዋት 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት ሰልፍ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ከንቲባ ወ/ሮ መሰረት አሰፋ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ሌሊት ላይም በከተማዋ በምሽት ሰልፍ ተካሂዶ እንደነበር ከንቲባዋ ተናግረዋል። "ቅዳሜ ሌሊት 'ቤተክርስቲያን ተቃጥለ' የሚል ወሬ ተናፍሶ ሌሊቱን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በንብረት ላይ ጉዳት ደርሶ ነበር" ብለዋል።

ከንቲባዋ ጨምረው እንደተናገሩት ቅዳሜ ሌሊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃጥሏል እየተባለ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት መሆኑን እና ይህ የተደረገው "በከተማው ሆን ተብሎ ረብሻ ለመፍጠር" ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ዛሬም 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት አደባባይ እንደወጡ እና ከጸጥታ አካላት ጋር እንደተጋጩ እንዲሁም በተከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን አስረድተዋል። እስካሁን የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ፤ ዛሬ ተከስቶ የነበረው ሁከት በቁጥጥር ሥር ውሎ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጨምረው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛው አገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ADAMA #BAHIRDAR ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል። ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል። የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች…
#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል።

ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

#ቢሾፍቱ 📍

በቢሾፍቱ ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ከኦዳ ነቤ ሆቴል ጎን እና ከመዘጋጃው ፊትለፊት)፤

#ሞጆ📍

በሞጆ አንድ መናኸሪያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር፤

#ደብረብርሃን 📍

ከዘርዕ ያዕቆብ አደባባይ ወረድ ብሎ ባለው ኖክ ማደያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት መሆኑን ገልጿል።

በቢሾፍቱ፣ በሞጆ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia