TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update ለ2 ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሴራሊዮን የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጁልየስ ማዳባዮ ጋር በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ የጉብኝት ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በሴራሊዮን መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።

ምንጭ፡- ም/ጠ /ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጂንካ🔝

17ኛው የአርብቶ አደር ቀን በዓል #በጂንካ_ከተማ ስታዲየም ትከብሯል። በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ ዞን ጉብኝት🔝

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

በሙከራ ደረጃ 200 ሄክታር የሸፈነው የስንዴ ግብርና ልማት በመስመር እና በመስኖ የተዘራ በመሆኑ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አልሚዎቹ ተናግረዋል።

በሃገሪቱ መሰል ቆላማ እና ዝናብ አጠር አካባቢዎች ይህን ስኬታማ ተሞክሮ በሚገባ ሊማሩበት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አሳስበዋል።

በየአካባቢው የስንዴ ግብርና ልማት እየጎለበተ መሄድ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፥ ለዘርፉ መንግሥት ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያጠናክር አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 19/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
.
.
#ሐሰተኛ_የማስተርስና_የዶክትሬት ዲግሪዎች እንዲሰጡ አድርገዋል የተባሉት የሜቴክ ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ #የድሬዳዋ ተወላጆች በዛሬው ዕለት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተገኝተው ያላቸው ተቃውሞ እና ቅሬታ አሰምተዋል። የፌደራሉ መንግስት ለድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥና ያሉ ችግሮችን እንዲፈታ ጠይቀዋል።
.
.
#የሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትናንት ቅዳሜ "አንድ ቀን ለማህበረሰቤ" በሚል መሪ ሀሳብ #ፍቼ ከተማን ሲያፀዱ ውለዋል።
.
.
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን ቆላማ አካባቢ የስንዴ ግብርና ልማት የሙከራ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
.
.

4ኛው የኢህአዴግ የወጣቶች ሊግ ድርጅታዊ ጉባዔ #በሃዋሳ_ከተማ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባዔው "በተጠናከረ የወጣቶች ትግል ሀገራዊ ለውጡን ወደፊት" በሚል መሪ ቃል እስከ ጥር 19 እስከ 21 በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ይቆያል፡፡
.
.
በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተው #ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
.
.
በጅማ ከተማ "ንግዳችንን እናዘምን" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬ ዕለት ተካሂዷል።
.
.
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።
.
.
የቀድሞ ጦር ማህበር #የምስረታ_ጉባዔ ዛሬ #በደብረማርቆስ ፖሊስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
.
.
ለአራት ቀናት በመቀለ ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ አዋጆችንና ሹመቶችን በማጽደቅ #ተጠናቋል
.
.
የድሬዳዋን ሰላምና ፀጥታ #አስተማማኝ በማድረግ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንደሚሰራ #በምስራቅ_ዕዝ_መከላከያ የሚመራው ጊዜያዊ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ አስታውቋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣ DW፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የምክትል ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ etv፣ ዋልታ፣ ፋና፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
የነገ ሰው ይበለን!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የህዳሴ ግድብን #ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ማራዘሚያ ጊዜ ሊኖር አይገባም” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር #ደመቀ_መኮንን
.
.
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተያዘው የጊዜ መርሃ-ግብር ለማጠናቀቅ ርብርብ መደረግ እንደሚገባ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው ግድቡ ስምንት ዓመታት አለመጠናቀቁን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) መሰራት የነበረበት የግድቡ ኤሌክትሮ ሜካኒካልና ተያያዥ ተግባራት አፈፃፀም #በመጓተቱ ነው ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አራት ዓመታት አስፈልጓል፤ ይሁንና አሁን ላይ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክቱን በተያዘው የጊዜ ገደብ በጥራትና በብቃት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ክትትል ያደርጋል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር የካቲት 6 ቀን 2011 ተወያዩ። ካለፈው የቀጠለው ይህ ውይይት በዋናነት የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም ኮሚቴው ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንዲያጠናክር አቅጣጫ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሳት የሚዲያ ቡድን🔝

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን የኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ለኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላትም በሃገሪቱ #ተጨባጭ ሁኔታ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በለውጡ ጉዞ እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎችን እና ዕድሎችን ያብራሩ ሲሆን #ሚዲያው ለለውጡ ስኬት ሚዛናዊ እና ገንቢ ሚናውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢሳት ሚዲያ ቡድን አባላት በበኩላቸው የተጀመረው ለውጥ ዳር እስከ ዳር እንዲሰርጽ ሙያዊ #ሃላፊነታቸውን በሚዛኑ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ ህዝብን እና ሃገርን ባስቀደሙ አጀንዳዎች ዙሪያ የጎደለው እንዲታረም - የተሻለው ደግሞ እንዲጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ የኢሳት ሚዲያ ቡድኑ አባላት አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የገጠር መሬት አስተዳደር ስርዓት ግንባታ ሂደትን የ2ተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ የምርቃት በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄደዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፤ የመሬት ሃብት አጠቃቀም በላቀ ደረጃ እንዲሻሻል ፋና ወጊ ሚና እንዲጫወቱ ለተመራቂ አርሶ አደሮች የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን 5ተኛው የኢትዮ~ሱዳን ከፍተኛ የጋራ ኢኮኖሚ ትብብር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሱዳን~ካርቱም ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ፤ የሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት #ኦስማን_መሃመድ_ዩሱፍ_ኪቢር በወታደራዊ ማርሽ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Via Office of Deputy Prime Minister of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BREAKING

የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ቦታ #በመተካት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሊሾሙ እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ መረጃ ደርሶኛል ሲል THE FINFINNE INTERCEPT ዘገበ። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ-አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸውን በዶክተር አምባቸው መኮንን ምትክ አማካሪያቸው አድርገው ሊሾሟቸው እንደሆነ THE FINFINNE INTERCEPT ዘግቧል።

---ተጨማሪ መረጃዎች ከሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚሰሙ ከሆነ ተከታትዬ አሳውቃችኃለሁ--
@tsegabwolde @tikvahethiopia