TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አብዲ ኢሌ‼️

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት እና አሁን በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሀመድ ኡማር ለጠ/ሚር #አብይ_አህመድ ጥቅምት 14 በፃፉት ደብዳቤ ካሉት ዋና ዋናዎቹ፦

* በክልሉ የሰው ህይወት #እንዳይጠፋ እና ንብረት #እንዳይወድም አንተ (ጠ/ሚር አብይ) የሰጠኸኝን ምክር እና ሀሳብ #ችላ ብያለሁ።

* እንደገናም ችግሩ ከተከሰተ በሁዋላም ሳትተወኝ የሰጠኸኝን ጥሩ ሀሳብ ባለመቀበሌ የለውጡ እንቅፋት ነበርኩ። ለዚህም ከልቤ #ተፀፅቻለሁ

* አሁንም ቢሆን ቃልህን እንደማታጥፍ እና ፊትህን #እንደማታዞርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

* ከመጀመርያ ጀምሮ አመጣጥህንና እያመጣህ ያለውን አመርቂ ለውጥ በጣም #አደንቃለሁ

* እኔም ስህተቴን አርሜ ከህዝብ እና መንግስት ጋር በመሆን የለውጡ #ቸርኬ ሆኜ እሰራለሁ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikahethiopia