TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ጊዜ ዝቅተኛው #አራት(4) ዓመት ሲሆን እንደ ምህንድስናና ህክምና የትምህርት ፕሮግራሞች ደግሞ #ስድስት(6) ዓመት እንዲሆን ሀሳብ ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት #ዋና_አፈ_ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት #ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።

የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛውም መመዘኛ #ትክክል አይደለም ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ በቀጣይ ተመሳሳይ #ስህተት እንደማይደገም በምክር ቤቱ ፊት ቃል እገባለሁ ብለዋል። በእርግጥ እንደምክንያት ማቅረብ ባይቻልም ምክር ቤቱ ማድረግ የነበረበትን መደበኛ ጉባኤዎች ሳያካሂድ የቀረው ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ የተነሳ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዓመት #አራት መደበኛ ጉባኤዎችን ማድረግ የሚገባው ቢሆንም ባለፈው የጥቅምት ወር የመጀመሪያውን ስብስባ ካደረገ ወዲህ ዳግም ሳይሰበሰብ ነው የበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው። በዚህም ምክንያት የክልሉ ዓመታዊ በጀት እስከአሁን ባለመፅደቁ የአስፈጻሚ ቢሮዎች ከሀምሌ 1 2012 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስራዎቻቸውን በምክር ቤት ባልጸደቀ በጀት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,880 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ አድርጋ 75 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ ሰዓት #አራት ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ይህ የሟቾች አሃዝ ከሁለት ቀን በኃላ የመተመዘገበ ነው።

ትላንት 80 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

እስካሁ ያለው ቁጥራዊ መረጃ ምን ይመስላል ?

የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 2929862 ሲሆን ከነዚህ መካከል 277,212 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ሲገኙ ከነዚህ መካከል 4,347ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 262,102 ሰዎች አገግመዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁ 2,064,777 ዜጎቿን የኮቪድ-19 ክትባት ከትባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ ያሉ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ለማየትና ለመጠየቅ እየተዘጋጁ ያሉ ዜጎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በቀን የሚያደርገውን በረራ ቁጥር እንዲጨምር እየጠየቁ ይገኛሉ። ሄርመን የተባለችና በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነች የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቷ በመቐለ እንደሚኖሩ ገልፃ በረራ መጀመሩን በመስማቷ እጅግ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረባት ገልፃለች። ትላንት…
#AddisAbaba #Mekelle

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቐለ ያለው የቴሌኮም መሰረተ ልማት እንደተስተካከለ በየዕለቱ የሚካሄደውን በረራ እንደሚያሳድግ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት ቃል አየር መንገዱ የአውሮፕላን ችግር እንደሌለበትና በቀን አራትም፣ አምስትም በረራ ማድረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን የተቸገርነው መቀለ የቴሌኮም አገልግሎት ስለሌለ የስልክ ግንኙነት እንኳን ማድረግ አልቻልንም። ከእዛ ለሚመለሱት እንኳን የ boarding pass እና የ baggage process እየተደረገ ያለው አዲስ አበባ ነው። የቴሌኮም ጥገናው እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ስለዚህ ይህ እንደተስተካከለ እኛም በራራውን እንጨምራለን። " ሲሉ አሳውቀዋል።

" ይህ ምናልባት በመጪው #ሶስት እና #አራት ቀናት ሊስተካከል ይችላል። " ሲሉም አክለዋል።

በሌላ በኩል ከየአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ጋር በተያያዘ 3 ሺህ የነበረው አሁን እስከ 9 ሺህ እየተሸጠ እንደሆነ ይነገራል ይህ ለምን ሆነ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

" ዘጠኝ ሺህ የተሸጠው business class ነው " ያሉት አቶ መስፍን " የeconomy class ትኬት ቀድመው የገዙ ሶስት ሺህ ብር ገደማ ነበር፣ በአለም አቀፍ አሰራር መሰረት ትንሽ ዘግይቶ የሚገዛ ደግሞ ወደድ ይላል፣ አራት ሺህ ገደማ ገብቷል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለበረራ የሚጠቀምበት አውሮፕላን 138 ሰው የሚጭን ቦይንግ 737 መሆኑን ጠቁመዋል።

" ወደፊት ፍላጎቶችን እያየን ከዛም በላይ የመጫን አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖችን መጠቀም እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

#ኤልያስመሰረት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ትላንት ለአሀዱ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት " ለአንድ ዓመት " በሚል የተገለፀው ስህተት እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀው እንዲታረም ብለዋል።

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) የሚሰጠው ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ለአራት ወራት እንደሆነ አመልክተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ እንደሚወስዱ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ #አራት_ወር ተወስዶ ተማሪዎቹ አቅማቸውን የሚሞላ ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ ይደረጋል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነድ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#AxumUniversity

አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤  ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦

- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።

- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።

- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።

- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን  ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።

- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል። 

- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።

የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013  ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Credit : www.ethiopianInsider.com

@tikvahethiopia
" ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር ነው የሚገኙት " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ 7 ታዳጊዎች #እንደጠፉ እና #እንደታገቱ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ነው አለ።

ፖሊስ መረጃው እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ስለመሆኑ #አረጋግጥላችኃለሁ ብሏል።

ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ፖሊስ ምን አለ ?

- #አራት ወንድ እና #ሦስት ታዳጊ ሴቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 " መካኒሳ ቆሬ " አካባቢ ከሚገኘው የወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት እንደጠፉ እና ታግተዋል በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም።

- ታዳጊዎቹ ለመጥፋት በማሰብ ከወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት ልብሶቻቸውን ይዘው እንደወጡ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው መኖር እንደሚፈልጉ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

- በልመና ተግባር ላይ ተሰማርተውም ባገኙት ገንዘብ የተወሰኑ የቤት ቁሳቁስ በማሟላት ሰባቱም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው " ቡልቡላ " አካባቢ በ1 ሺ 800 ብር መኖሪያ ቤት ተከራይተው #ሦስቱ ወንዶችና #ሦስቱ ሴቶች #የፍቅር_ግንኙነት በመመስረት በጋራ እየኖሩ እንደሚገኙ እራሳቸው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

- የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ከተለያዩ ቦታዎች መረጃ በማሰባሰብ በተደረገው ክትትል ያሉበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ ተችሏል።

- ታዳጊዎቹ የስነ-አእምሮና ተያያዥ የጤና ምርመራ እንዲያገኙ እንዲሁም ማህበራዊ ችግራቸው ሊፈታ በሚችልበት ሁኔታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው።

- አንዳንድ መገናኛ ብዙኃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃን ስላገኙ ብቻ  የሚያስከትለውን አሉታዊ ጫና ታሳቢ ሳያደርጉ ዜናውን ማሰራጨታቸው በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያስከትል መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው ሊገነዘቡ ይገባል።

- ወንጀልን በማጣራት እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ስራ ጊዜን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን !

አንድ ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ፦

- በተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ)

- የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣

- ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም ClF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

#ተገጣጥመው_ወደ_ሀገር_ውስጥ_የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 13ዐዐ ከሆነ 75.67% ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ18ዐዐ በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው #ያገለገሉ (USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የተሽከርካሪው ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡

እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ #አራት_ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት #የዊዝሆልዲንግ_ታክስ ይሰበሰባል፡፡

የቀረጥ እና የታክስ ማስከፈያ መሠረት (Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ (CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን ፦
* የጉምሩክ ቀረጥ፣
* ኤክሳይዝ ታክስ፣
* የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣
* ሱር ታክስ ድምር ይሆናል፡፡

የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት ተደርጎ እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 4ዐዐ,ዐዐዐ፣ የሲሊንደር አቅሙ 13ዐዐ የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ ፦

🚘 በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 × 3ዐ%(ከፍተኛው መጣኔ) = 12ዐ,ዐዐዐ ይሆናል፡፡

🚘 ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡

🚘 በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት thn (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,9ዐዐ ብር ይሆናል፡፡

🚘 በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900) 10% = 86,190 ብር ይሆናል፡፡

🚘 ተሽከርካሪው በመደበኛ አስመጪ (ከአምራች ድርጅት ውጪ...) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 4ዐዐ, 000 × 3%= 12,ዐዐዐ ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት 120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12, 000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡

#ማሳስቢያ ፦ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸዋል።

ይህ መረጃ የገቢዎች ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia