TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሀላፊነት ይህን ድምፅ ስጡልኝ። ለቀጣይ ሀገራዊ መልካም ስራዎች ለመስራት በቻናላችን ቤተሰብ ውስጥ ምን ያህል #ሴቶች እንዳሉ ለማወቅ በማስፈለጉ በኃላፊነ ይህንምልክት በመጫን አብሮነታችሁን ግለፁ።

ሴቶች ብቻ በኃላፊነት ድምፅ ስጡ። በአዲሱ አመት ከሴቶች መብት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ስላሉ ቁጥሩን ማወቅ ማስፈለጉ ነው።

አመሰግናለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ጾታዊ ተዋፅዖውን የጠበቀ ካቢኔ ካዋቀረች ከሁለት ቀናት በኋላ #ሩዋንዳም የአዲስ አበባን ፈለግ በመከተል ግማሹን የካቢኔ አባላቷን ሴቶች ማድረጓ ተሰምቷል፡፡ ከ26ቱ አዲስ ተመራጭ የሀገሪቱ ካቢኔ አባላት መካከል 13ቱ #ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። ከሀገሪቱ የፓርላማ አባላት መካከልም 61 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ በዘገባው አስነብቦናል፡፡

@tseabwolde @tikvahethiopia
#update አምባሳደር #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአሜሪካ ኢምባሲ የደስታ መግለጫ አስተላለፈ፡፡ ያለ #ሴቶች ተሳትፎ አንድ ማህበረሰብ #ውጤታማ እንደማይሆን የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን ወደ ሃላፊነት ማምጣቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብሏል የአሜሪካ ኢምባሲ በመግለጫው፡፡ መንግስት ሴቶችን ያቀፈ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰዱ ኢምባሲው #አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል‼️

የትግራይ ክልል ለ3 ሺህ 231 ታራሚዎች #ይቅርታ አደረገ። የክልሉ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 72ቱ #ሴቶች ናቸው።

ታራሚዎቹ የይቅርታ ህግን ያሟሉ መሆናቸውን ተከትሎ ነው በይቅርታ እንዲለቀቁ መደረጉን የቢሮው ሀላፊ አቶ #ተኪኡ_ምትኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ታራሚዎቹ ከህዳር 20 ቀን 2011 ጀምሮም ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተመልክቷል።

የክልል መንግስት ባለፈው ዓመት የግንቦት 20 በዓልን ምክንያት ለ2 ሺህ 206 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጎ አንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር አብይ አህመድ ተሸለሙ!
.
.
ዶክተር #ዐብይ_አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል፡፡ ሽልማቱ በስርዓተ ጾታ እኩልነት ዙሪያ ጥሩ ተግባራትን ለፈጸሙ ግለሰቦች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍናቸው ወራት ውስጥ በአመራር ስፍራዎች ላይ #የሴቶችን_ተሳትፎ አሳድገዋል፡፡ ለአብነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግማሽ አባላት ሴቶች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሴት ፕሬዝደንት፣ መከላከያ ሚንስትር፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መሾማቸው ተነስቷል፡፡

#ሴቶች በሙስና ወንጀሎች የመሳተፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን እና በስራቸው ውጤታማ መሆናቸውን በተደጋጋሚ እንደተናገሩ ተገልጿል፡፡ በስርዓተ ጾታ አቀንቃኞች ዘንድ ዶክተር ዐብይ እንደሚወደሱም ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያገኙት ሽልማት በአፍሪካ ህብረት እና በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም...

"በ846 ወረዳዎች ለሚገኙ የቴሌኮም አገልግሎት የመግዛት አቅም ለሌላቸው #ሴቶች 70,000 የሞባይል ቀፎዎችን ከሲም ካርድ ጋር በስጦታ ለማበርከት ዝግጅታችንን #አጠናቀናል።"

#Ethiopia #Women
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ተስፋዎች🔝

#የTikvah_Ethiopia ሴት አባላት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አጭር ገለፃ ተደርጎላቸዋል:: ለበርካታ ወጣት #ሴቶች አርአያ ለመሆን እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በቀጣይ ሊሰሯቸው ባሰቧቸው ስራዎች ዙሪያም በመጪው ሳምንት #ምክክር ያደርጋሉ:: በዛሬው ውይይት ላይ የተካፈሉት #አብዛኞቹ #የStopHateSpeech አስተባባሪዎች ናቸው::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ችግሮች መፍታት የሚቻል ከሆነ በፍጥነት ቢፈቱ እና ህዝቡ ወደ ቀድሞው ኑሮው እንዲመለስ ቢደረግ መልካም " - የቲክቫህ አባላት

ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በክልሉ ላለው ችግር እካሁን ይሄ የሚባል መፍትሄ ባለመምጣቱ ህዝቡ ስቃዩ እየተራዘመ ነው ብለዋል።

በቅርብ ሳምንት የታዩት በጎ ነገሮች መልካም ቢሆንም በፍጥነት ወደ ታች ወርዶ በችግር ላይ ያለውን ህዝብ መታደግ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

ነዋሪዎች ባለፉት በርካታ ወራት ፦
👉 ያለ ባንክ፣
👉 ያለ ስልክ፣
👉 ያለ ትራንስፖርት ፣
👉 ያለ የንግድ ልውውጥ፣
👉 ያለ ስራ፣
👉 ያለ ትምህርት
👉 ከምንም በላይ ደግሞ ያለ በቂ ህክምና ላይ ነው የሚገኙት ይህን ለአንድ ቀን እንኳን ለማሰብ የሚከብድ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ያሉት ችግሮች የሚፈቱበት አግባብ ቢፋጠን ፤ ዜጎችም ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ቢደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

ለበርካታ ወራት ባለው ሁኔታ ምንም ፖለቲካ የማያውቁ ፣ ስላለው ሁኔታ በቅጡ የማይረዱ እጅግ ብዙ ሰዎች አብረው የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል፤ ሌላው ቢቀር ለትንንሽ ህፃናት፣ ሴቶች እና አረጋዊያን ተብሎ ፈጣን መፍትሄ ቢፈግ ሲሉም ተማፅነዋል።

በተለይም ፤ ከባንክ አለመኖር ጋር በተያያዘ ብዙ ችግር መከሰት ከጀመረ ወራት መቆጠሩንና ይህም ችግር ለማንም ግልፅ እንደሆነ አንስተዋል።

መልዕክታቸውን ከላኩ ቤተሰቦቻችን አንዱ " ቤተሰቦቼ የሚኖሩት ትግራይ ክልል ነው። ታድያ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ላይ ባንኮች አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ምክንያት ህዝቡ በብዙ ችግሮች ውስጥ እየኖር ነው " ብሏል።

አክሎም ፤ " ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በአቋራጭ መበልፅግ የሚፈልጉ እራስ ወዳዶች ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቤተሰቦቹ ብር መላክ ከሚፈልግ ሰው አላማጣ ላይ ባሉት ሰዎቻቸው ሆነው አዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ መቀመጫቸውን ካደረጉ ግለሰቦች እስከ 50 በመቶ ማስላክያ ክፍያ በመቁረጥ ከሚልከውና ከሚቀበለው ህዝብ እየዘረፉ ይገኛል " ሲል አስረድቷል።

በዚህ ላይ አስፈላጊውን እርምት ሊወሰድ እንደሚገባና በአፋጣኝ በትግራይ የባንክ አገልግሎት እንዲጀመር ሊደረግ ይገባል ሲል ጠይቋል።

በትግራይ ፤ በብር እጦት ምክንያት ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ ምንም የማያውቁ ንፁሃን እየሞቱ እና እየተንገላቱ ነውና ፈጣን መፍትሄ ያስፈልጋል ብሏል።

ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን አባላት ፤ በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታ በተደጋጋሚ መግለፃቸው እና በተለይ በተለይ ለ #ህፃናት#ሴቶች እንዲሁም #አረጋዊያን ካለው ችግር እንዲወጡ ፈጣን መፍትሄ እንዲፈለግ መማፀናቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ወገኖች ችግር ላይ ናቸው ! በምዕራብ ወለጋ ዞን በጊምቢ ወረዳ ፣ ቶሌ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ከሰኔ 11ዱ ጥቃት የተረፉ ነዋሪዎች አስፈላጊውን የምግብ እርዳታ ስላላገኙ ችግር ላይ ይገኛሉ። ነዋሪዎቹ ቤት ንብረታቸው ከመውደሙ ባሻገር ንግዳቸው እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸው ስለተዘረፉ የምግብ ችግር እንደገጠማቸው እየተናገሩ ነው። ቤት ንብረታቸው የወደመባቸው ሰዎች ዘመዶቻቸው…
#UN

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን አሰቃቂ የጅምላ ግድያ ላይ ባለሥልጣናት ፈጣን፣ ገለልተኛ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠየቀ።

የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ኃላፊ ሚሼል ባችሌት " በቶሌ መንደር የተፈጸመው የጭካኔ ግድያ እና የነዋሪዎች በጥቃቱ ምክንያት ተገድዶ መፈናቀል ዘግንኖኛል " ብለዋል።

ቅዳሜ ዕለት ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት እማኝን ባልደረባቸው እንዳነጋገሩ እና ወደ መንደሩ የገቡት ታጣቂዎች በነሲብ ተኩስ ከፍተው ብዙዎችን እንደገደሉ መረዳታቸውን ገልጸዋል።

ከሟቾቹ አብዛኞቹ #ሴቶች እና #ሕጻናት መሆናቸውን እንዲሁም ቢያንስ 2 ሺ ሰዎች ከአካባቢው ለመሸሽ መገደዳቸውን አመልክተዋል።

4 ሰዓት በፈጀው ጥቃት ታጣቂዎቹ በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸውንም ገልፀዋል።

በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን አስከሬን አሁንም በመንገዶች ላይ ወድቀው ሊገኙ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ባችሌትም ባለሥልጣናት " ጥቃቱ በአፋጣኝ መጣራቱን፤ ሰለባዎች እና ቤተሰቦቻቸው እውነት፣ ፍትህ እና ካሣ የማግኘት መብታቸውን እንዲሁም አጥፊዎችን በተጠያቂነት መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ " ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በጥቃቱ ወቅት መታገታቸውን እና ያሉበት እንደማይታወቅም አጽንኦት በመስጠት ባለሥልጣናት የታገቱት ነጻነታቸውን እንዲያገኙ አስፈላጊ እና ሕጋዊ ርምጃዎችን እንዲወስዱም ማሳሰባቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ከተቀሰቀሰ በኃላ እስካሁን ምን ሆነ (እጅግ በጥቂቱ) ?

- ህወሓት ቆቦና የአካባቢው ቦታዎችን መቆጣጠሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ሰላም እና ደህንነት ፍለጋ ወደ አጎራባች ከተሞች እንዲፈናቀል ምክንያት ሆኗል።

- እንደ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በመቐለ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 4 ሰዎች ተገድለዋል ፤ 2ቱ ህፃናት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ንፁሃንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እንደማይፈፅም በመግለፅ የወጡ ክሶችን አስተባብሎ ነበር።

- ህወሓት በአፋር ክልል " ያሎ " በኩል በሰነዘረው የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዱብቲ ጠቅለላ ሆስፒታል የገለፀ ሲሆን በጥቃቱ ህፃናት ተገድለዋል። አንዲት እናት ሁለት ህፃናት ልጆቿ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ተገድለውባታል። የቆሰሉም በርከት ያሉ ናቸው።

- የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር እንደገለፀው " ወለህ " አካባቢ ህወሓት 10 ሰላማዊ ሰዎችን በግፍ መግደሉን፣ ከሟቾች መካከል አንዲት እናት ከነ ልጆቿ እንደምትገኝበት ገልጿል። በተጨማሪ ቡድኑ ወደ ወለህ መጠለያ ጣቢያ በመግባት 25 ሰዎችን መግደሉን አስተዳደሩ ገልጿል።

- ህወሓት በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑ በገለፀ በሰዓታት ውስጥ ይዟቸው በሚገኙ የራያ ቆቦ ወረዳዎች በንፁሃን ላይ ጥቃት መዘንዘሩን ነዋሪዎች መግለፃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። ህወሓቶች በቀበሌ 02 ሰው መግደላቸው፣ ማቁሰላቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከጥቂት ቀናት በፊትም አራዱም ላይ ሰላማዊ ሰው መግደላቸውን ገልፀዋል። ባለፉት 18 ቀናት ሌሎች ያልታጠቁ ንፀሃን ሰዎችን መግደላቸውና በተጨማሪ ዝርፊያ እንደፈፀሙ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

- የመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል እንደገለፀው 2 ጊዜ በተፈፀመ የአየር ጥቃት 10 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ የመጀመሪያዎቹን ተጎጂዎች ለመርዳት በተሰበሰቡበት ወቅት በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉ ናቸው ብሏል። (ይህ የሆነው ትላንት ነው)

- UN OCHA በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ዳግም ባገረሸ ግጭት በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።

እንደ UN OCHA መረጃ ፦

👉 በአማራ ፣ አፋር፣ እና ትግራይ ክልሎች በ10 ሺዎች መፈናቀለቸውን ገልጿል።

👉 የሰብዓዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ መግባት እንዳቆሙ፣ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በረራ እንደተቋረጠ መሆኑን ገልጿል።

👉 በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ለመገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

👉 በመርሳ ከተማ በ5 ት/ቤቶች አብዛኞቹ #ህፃናት እና #ሴቶች ከቆቦ እና አካባቢው ተፈናቅለው ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ለእነሱ ምግብ እና ምግብ ያልሆኑ ድጋፎችን ማሰራጨት ጀምራለሁ ብሏል።

- የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል በዞኑ የተፈናቃዮች ቁጥር እጅግ እየጨመረ መሆኑን ገልጾ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጿል። መርሳ በሚገኙ ት/ቤቶቹ ውስጥ ያሉት ሴቶች እና ህፃናት ሲሆኑ ወንዶች ወጣቶች እንዲገቡ አልተደረገም። በአጠቃላይ ወልድያ እና መርሳ ከተሞች ላይ 92,400 ተፈናቃይ አለ።

- ጦርነቱ ዳግም ካገረሸ ወዲህ በርካታ ንብረቶች ወድመዋል።

- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ወደ ባህርዳር ቢሮው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መልዕክቶች እየመጡለት ሲሆን አካባቢዎቹ ላይ ምቹ ሆኔታ ሲፈጠር ምርመራ አድርጎ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

NB. የተዘረዘሩት ክስተቶች ግጭት ዳግም ካገረሸ ወዲህ #በተለያዩ_ጊዜያቶች የተሰሙ ናቸው።

የሰላም ሂደቱ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ ነው ?

የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ለሰላማዊ ንግግር ዝግጁ መሆኑን ከሳምንታት በፊት ገልጾ ነበር።

ህወሓት በአፍሪካ ህብረት (AU) አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦባሳንጆ ላይ እምነት እንደሌለውና በሂደቱ መተማመን እንደሌለው ሲገልፅ ከቆየ በኃላ ከቀናት በፊት በህብረቱ መሪነት ለሚደረግ የሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ይህንን የህወሓት የሰላም ሂደት መቀበል እና ግጭት ለማቆም ዝግጅቱነት እንዳለው መግለፁን በተመለከተ በርካታ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ውሳኔውን በማድነቅ የሰላም ሂደቱ እንዲፋጠን ጥሪ አቅርበዋል።

ዳግም ያገረሸው ጦርነት ግን አሁንም አልቆመም።

የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ህወሓት ላወጣው መግለጫ በግልፅ ቀጥተኛ ምላሽ ባይሰጥም ትላንት ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር በተወያዩበት ወቅት መንግስት ለአፍሪካ ህብረት የሰላም ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ቁርጠኛ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ እንዲያገኝ መንግስት ዝግጁነት እንደነበረው ነገር ግን ህወሓት በቅርቡ ወረራ መፈፀሙን ኤምባሲው ዛሬ አመልክቷል።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቱ እንዲፈታ የሚያምንበት ብቸኛ አማራች ሰለማዊ መፍትሄ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ አልጀዚራ ላይ ባወጡት ፅሁፍ መንግስት በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ለሰላም ውይይት ዝግጁ እንደሆነ አስታውሰው ህወሓት የሰላም ጥሪ ገፍቶ ጦርነት ከፍቷል ብለዋል።

ህወሓት የጀመረውን ጥቃት በማቆምም ወደ ሰላም ድርድር እንዲመለስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል።

በአፍሪካ ህብረት ስር ለሚደረገው ድርድር ፍላጎቱን ማሳየቱን ተከትሎ በቃሉ እንዲፀና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከዝምታው በመውጣት የመንግስትን የሰላም አማራጭ በመደገፍ ህወሓት ታጣቂዎቹን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ድርድር እንዲገባ ጫና ማድረግ አለበት ሲሉም አሳውቀዋል።

ህወሓት ወደሰላም እንዲመለስና ሰላምን ለማረጋገጥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ማድረግ ያለበት አሁን ነው ያሉት አምባሳደሩ ይህ ካልሆነ መንግስት ህዝብን የመጠበቅ ግዴታ ስላለበት ግዴታውን ይወጣል ብለዋል።

ከቀናት በፊት " ህወሓት " ፤ በአፍሪካ ኅብረት (AU) የሚመራ ተዓማኒ የሰላም ሒደት እንደሚጠብቅ ፤ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ፤ ለድርድሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፣ ለአፋጣኝ እና በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ተግባራዊ ለሚደረግ የተኩስ አቁም ዝግጁ መሆኑን መግለፁ እንዲሁም ለግጭት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት የሚቻለድ በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እግጠኛ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#የምርመራ_ሪፖርት

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ፤ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " አኖ ከተማ በጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋናነት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ይህ በተመለከተ #ኢሰመኮ ምርመራ አድርጓል።

ምርመራውን በተመለከተ ከላከልን መግለጫ ፦

- ጥር 25/ 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የወታደር ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) መሆናቸው በነዋሪዎች የተገለጹ ታጣቂዎች በ3 አቅጣጫ ወደ " አኖ ከተማ " መግባታቸውን፤ በመቀጠል በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የሆነ የተኩስ ድምፅ መሰማት መጀመሩን እና የሲቪል ሰዎች ግድያና የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት መድረሱ ታውቋል።

- በጥቃቱ ዋና ኢላማ የተደረጉት ከ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው።

- በታጣቂ ቡድኑ በተፈጸመ ጥቃት አንድ የክልል የሥራ ኃላፊ ከነሾፌሩ፣ የከተማ ፖሊስ እና የቀበሌ ሚሊሻ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ ሃምሳ (50) ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚም መካከል 42 ተጎጂዎች በተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡

- ከሟቾች መካከል አራት #ሴቶች እና ሦስት #ሕፃናት ናቸው፡፡

- ታጣቂዎቹ ‘ሰኞ ገበያ’ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤት ለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል፡፡

- በከተማዋ ውስጥ የሚገኝ እና ቀደም ሲል የቀበሌ አስተዳደር ንብረት የነበረና ወደ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት ተፈናቃዮች መጠለያነት ተቀይሮ በማገልገል ላይ ይገኝ የነበረ ግቢ ውስጥ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት፤ በግቢው ውስጥ የነበሩ ማምለጥ ያልቻሉ ወንድ ተፈናቃዮችን መርጠው ገድለዋል። ከእነዚህም መካከል ከተገደሉ በኋላ #ሬሳቸው_በእሳት የተቃጠለ ሰዎች አሉ፡፡ በጥቃቱ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ሲሆን መጠለያውም በጊዜያዊነት ተዘግቶ ነበር፡፡

- የሟቾችን አስከሬን ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት እና በማግስቱ የአካባቢው ማኅበረሰብ መቅበሩን የተጎጂዎች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

- 8 ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

- በተፈጸመው ጥቃት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግለሰቦች የንግድ መደብሮች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አኖ ቅርንጫፍ እና ሌሎች ተቋማት መጠነ ሰፊ ዘረፋ እና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ 

ሙሉ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/c/1370522004/23484

@tikvahethiopia
#Budapest 🇪🇹

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውድድር ደማቅ ታሪክ ከምትፅፍባቸው ውድድር አንዱ የሆነው የ " ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና " በቡዳፔስት፤ ሀንጋሪ ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።

🥇በውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ከምሽቱ 3:55 ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተጠባቂው የ10,000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ሩጫ ውድድር ላይ ትሳተፋለች።

የ10,000 ሜትር #ሴቶች ሀገራችን በማን ትወከላለች ?

1. ለተሰንበት ግደይ
2. ጉዳፍ ፀጋይ
3. እጅጋየሁ ታዬ
4. ለምለም ሀይሉ
5. ሚዛን አለም (ተጠባባቂ )

የቲክቫህ ስፖርት ገፅ @tikvahethsport አባል ከቡድኑ ጋር ወደ ሀንጋሪ ያቀና ሲሆን ተከታታይ መረጃዎችን እና ፎቶዎችን ከስፍራው ለቲክቫህ ቤተሰብ የሚያደርስ ይሆናል።

(ዝርዝር ፕሮግራሙን ከላይ ይመልከቱ)

ድል ለኢትዮጵያ !
ድል ለሀገራችን ልጆች !

More : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
የበርካታ ስደተኞች ደብዛቸው ጠፋ።

ከቀይ ባሕር ዳርቻ ስደተኞች የጫነች ጀልባ ሰጥማ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሆኑ ስደተኞች ደብዛቸው መጥፋቱን የየመን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጀልባዋ 75 ስደተኞች እንደጫነች ትላንት እሁድ መስጠሟን የየመን የባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል አሳውቋል።

ከስደተኞቹ መካከል 26 ሲተርፉ የቀሩት 49 ሰዎች የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

የጠፉትን ስደተኞች ለማግኘት ዛሬ ሰኞ ፍለጋ እየተካሔደ ነው ተብሏል።

የየመን መንግሥት የሚቆጣጠረው " ሳባ " የዜና ወኪል ጀልባዋ በኃይለኛ ንፋስ ሳቢያ ስትሰምጥ #ሴቶች እና #ሕጻትን ጨምሮ የጫነቻቸው ስደተኞች ወደ ባሕር መውደቃቸውን ስማቸው ያልተጠቀሰ የየመን ባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል ባለሥልጣን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የተሻለ ገቢ እና የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ባሕረ ሰላጤው ሀገራት ለማምራት የሚሞክሩ የአፍሪካ ቀንድ ሰዎች የጫነ ጀልባ በቀይ ባሕር ዳርቻዎች የመስጠም አደጋ ሲገጥመው የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየዓመቱ ከኢትዮጵያ፣ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ በየመን በኩል አድርገው ሳዑዲ አረቢያን ወደመሳሰሉ ሀገራት ለመጓዝ ጥረት ያደርጋሉ።

መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ / አሶሼትድ ፕሬስ / ሳባ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#ትግራይ - ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች !

" መቐለ ወደ #ስድስት_ቦታዎች አሁን ራሱ ያልመከኑ ቦንቦች አሉብን። … እስካሁን ድረስ ሞትና አደጋ 1,038 ነው በቢሯችን የያዝነው " - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

ባለፉት 2 አመታት የነበረው ከፍተኛ ጦርነት በግንባር ብቻ ሳይሆን በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይም ስለተካሄደ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህፃናትና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ሞትና የአካል ጉዳት አደጋዎች እየደረሱባቸው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሰምቷል።

የትግራይ ጤና ቢሮ ፤ የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤንዘር እፀድንግል (ዶ/ር) ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ፣ " በትምህርት ቤቶች፣ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ መቀሌ ወደ ስድስት ቦታዎች አሁን ራሱ ያልፈነዱ ቦንቦች አሉብን፣ ያልተነሱ ማለት ነው " ያሉ ሲሆን፣ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረቡላቸው የተለያዩ ጥያቄዎችም ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።

ያልመከኑት የጦር መሣሪያዎች #መቐለ የት የት ቦታዎች ይገኛሉ ?

- አንደኛው #ከፕላኔት_ጀርባ አካባቢ ነው።

- ሁለተኛው ቦታ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ የተመታበት #የአፄ_ዮሐንስ_ቤተመንግሥት_ጀርባ በኩል ነው።

- ሦስተኛው #05 አካባቢ ነው።

- ሌሎቹ ደግሞ መቐለ ውስጥ ሆነው ግን #እርሻ ቦታ ላይ ነው ያሉት።

በርግጥ በኅብረተሰቡ ላይ #አደጋን_እንደሚያደርሱ የሚገልፅ ምልክት (አጥር) ተደርጓል ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ እና በባለሙያ መነሳት አለባቸው " ብለዋል።

ባልመከኑ የጦር መሣሪያዎች ምን ያህል ሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ደረሰ ?

" ሁሉንም ወደ ጤና ተቋማት አምጥተን ለማከም ሁኔታው አልተመቸም ነበር። ስለዚህ ሙሉ ዳታ የለንም።

ሙሉ ዳታ አባባሌ አንዳንዶቹ አደጋ ደርሶባቸው የሞቱ አሉ፣ ሌሎች መምጣት ያልቻሉ ብዙ ሰዎችም እንዳሉ ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። ባልፈነዱ የጦር መሣሪያዎች ፣ በተጣሉ ተተኳሽ እና የተቀበሩ ቦንቦች አደጋ የደረሰባቸው ባለን ዳታ መሠረት ፦

- እስካሁን ሞትና አደጋ በአጠቃላይ 1,038 ነው ያለን በእኛ በቢሯችን የያዝነው። #163 ሞት፣ 875 ደግሞ ከባድ ጉዳት ማለት ነው።

- ከ163ቱ መካከል 84ቱ ዕድሜአቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት፣ 79ኙ ደግሞ ዕድሜአቸው ከ18 በላይ የሆኑ አዋቂዎች ናቸው።

- ከ84 #ህፃናት ውስጥ 75ቱ ወንዶች፣ 9ኙ ደግሞ #ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው ? አሁንም የሚመጡ አሉ ?

- አዎ አሁንም ድረስ ይመጣሉ። በተለይ ክረምት ላይ በእርሻ ሥራ መቀሳቀስ ስለሚኖር፣ በመነካካትም ሳያውቁ እያረሱ እያለ መፈዳት ያጋጥማቸው ስለነበሩ ቁጥሩ እየቀነሰ ቢሄድም አልፎ አልፎ እየመጡ ነው። ምክንያቱም በተጠናከረ ደረጃ አልተጠረገም። 

- ፈንጅ ነገሮችን የማጥራት ሥራ ካልሰራን ትልቅ ችግር ነው ያለው። የመንግሥት ተዋጊ አካሎች ትምህርት ቤቶችን እንደ አውደ ማቆያ ሲጠቀሙባቸው ስለነበር እዛ ላይ የተጣሉ ጦር መሳሪያዎች አሁን ትምህርት ሲጀምሩ #ህፃናት በተለያየ ጊዜ አደጋ ይደርስባቸዋል።

- በተለያዩ መንገዶች ሰው ተሸክሟቸው ፣ በጋሪ ፣ በፈረስ ፣ በበቅሎ ሕክምና ቦታ መድረስ የቻሉ ሰዎች እንኳ (በተለይ ደግሞ ሽረ አካባቢ የመጡ ብዙ ታካሚዎች) መድኃኒት በበቂ ሁኔታ ስላልነበረ የጤና ተቋማት በቂ ሕክምና ሊሰጧቸው ባለመቻላቸው ብዙ ያጣናቸው አሉ።

- አካል ጉዳተኞችም ሆነዋል ሕክምና ቢደረግላቸው መትረፍ እየቻሉ ግን የሰርጀሪ እቃዎች እጥረት ስለነበረ አካል ጉዳተኛ የሆኑት በርከት ያሉ ሰዎች ናቸው። በአጠቃላይ በነበረው ሁኔታ ከባድ ነበር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ በተቻለ መጠን ባለን አቅም አገልግሎት እየሰጠን ነው።

ከመድኃኒት እጥረቱ ጋር በተያያዘ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎችን በቁጥር ደረጃ መግለፅ እችላለን ?

- በቁጥር እንኳ ያስቸግራል፣ ግን እኔ የማስታውሳቸው ወደ ሦስት #ህፃናት በአንድ ወቅት ገብተው የሕክምና እቃዎችን ማግኘት ስላልተቻለ ለአካል ጉዳት ተጋልጠዋል። ይህ በአንድ ወቅት ብቻ ነው። በተጠና መልኩ ግን ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ በቁጥር ደረጃ አጋጣሚ አልያዝነውም።

ምን ተሻለ ?

- አንደኛ ከሁሉ በላይ በመጀመሪያ እንዲህ አይነት መሣሪያዎችን መነካካት እንደሌለባቸው ህፃናት፣ ማኅበረሰቡ ማወቅ እንዳለባቸው ትምህርት መሰጠት አለበት።

- የፈንጅ #አምካኝ ባለሙያዎች በስፋት በማሰማራት በእያንዳንዱ ቦታዎች ተሰብስበው ያልመከኑ የጦር መሣሪያዎች መወገድ አለባቸው ፤ በየአካባቢው በጣም በርከት ያሉ #ያልተነሱ ፈንጂዎች አሉብን።

- ከተነሱ ነው በዘላቂነት መፍትሄ የሚገኘው። ሕዝብ ባለበት ቦታ ምንም አይነት ጦርነት አለማካሄድ ላለማካሄድ የሚደነግጉ መርሆዎችም መከበር አለባቸው። የህዝብ መገልገያ ቦታዎች ለወታደራዊ አላማ አለማዋል እንሰ እሪኮመዴሽንም መወሰድ አለበት።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
የተሽከርካሪ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ቀጠፈ።

ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ተኩል አካባቢ በደቡብ ወሎ ዞን ፤ ደሴ ዙሪያ ወረዳ 013 ቀበሌ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ከደሴ ወደ አቀስታ ከተማ 20 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ " ኮድ3-46660 አማ " የሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለኛ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው የ14 ሰዎች ህይወት ያለፈው።

ከሟቾቹ መካከል የ12ቱ ሰዎች ህይወታቸው ወዲያውኑ ሲያልፍ አንዱ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ባለበት ወቅትና ሌላው ተሳፋሪ ደግሞ ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

ከአጠቃላይ ሟቾች ውስጥም ስድስቱ #ሴቶች ናቸው።

አሽከርካሪውን ጨምሮ ሌሎች በአደጋው ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 6 ሰዎች በደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

የሟቾች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል።

ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን ፅ/ቤቱ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ አደጋ ጋር በተያያዘ አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በላከችው መልዕክት ፤ ከሟቾቹ ሁለቱ የቅርብ ጓደኞቿ እንደሆኑ ተናግራለች።

ሌሎች ሁለቱ ደግሞ እህትማማቾች እንደሆኑ ገልጻለች።

" በጣም ከባድ ሀዘን ላይ ነን ፤ መላው የአቀስታ ህዝብም ከባድ ሃዘን ላይ ነው " ብላለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ደማቁ የዓድዋ የድል መታሰብያ በዓልን በእርስ በርስ ግጭት ማቆሸሽ አይገባም " - ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መልእክት አስተለልፈዋል። ከ3 ዓመት ተኩል በኃላ በትግራይ ታሪካዊትዋ የዓድዋ ከተማ በመገኘት በዓሉን ለማክበር በመቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል። ፕረዚደንትዋ #እንባ_እየተናነቃቸው ያለፈውን አስከፊ ጦርነት በማስታወስ ፣ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ…
#ትግራይ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 😢

" ጠላት ሊወረን ሲመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፣ በሃይማኖት ፣ በፆታ ሳይለያይ የመሪውን ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክን ጥሪ በመቀበል ተሰባስቦ በመዝመት በነዚህ ተራሮች እና ኮረብታዎች ታሪክ እንዳልሰራ ሁሉ ለራሱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ፤ ለአፍሪካ አህጉራችን እንዲሁም ለመላው የተጨቆነ ህዝብ ተስፋ የሰጠ ሳለ በዚህች መሬት፦
- ወንድም በወንድሙ ላይ ቃታ የሳበበት የተጋደለበት
- ንፁሃን የተገደሉበት
- ብዙዎች የተሰደዱበት
- በርካቶች በገዛ ሀገራቸው የተንከራተቱበት፣ የተፈናቀሉበት
- ንብረት የወደመበት
- #ሴቶች_የተደፈሩበት ሁኔታ ታሪክ ጅብዱ በተሰራበት ምድር እንዲያይ ያደረግነው። እነዚህ ተራራዎች ለዚህም እማኝ እንዲሆኑ ያደረግነው።

እነዚህ ተራሮች መናገር ቢችሉ እንዲነግሩን የምንፈልገው ግን የህዝባችንን ጀግንነት፣ ታሪክ ሰሪነት፣ አንድነት ነው፤ ምስክሮቻችን ናቸው።

በትግራይ ጦርነቱ እንደጀመረ ሰሞን መጥቼ ነበር። ከጦርነቱ ሁለት ወር በፊት እዚህ ነበርኩ። የጦርነት ደህና ገፅታ የለውም እጅግ አስከፊውን ግን አላየሁም ብዬ ነው የማስበው። "

#TikvahFamilyAdawa

@tikvahethiopia