TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ " የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና/ቻን " እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ ዝግጅት ዛሬ ሞሮኮ ካዛብላንካ በሰላም መድረሱን የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል። ቡድኑ ወደ ሞሮኮ ከመሄዱ በፊት በሀገር ውስጥ ልምምድ ሲያደርግ ቆይቷል። በሞሮከ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ…
#Update

የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና / CHAN AFRICA እየተባለ በሚጠራው የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ብሄራዊ ቡድኑ #ከሞዛምቢክ#አልጄሪያ እና #ሊቢያ ጋር በአንድ ምድብ ነበር የተደለደለው። ከሞዛምቢክ 0 ለ 0 ሲለያይ በአልጄሪያ 1 ለ 0 ተሸንፎ ነበር።

በምድብ የመጨረሻው ጨዋታ #ከሊብያ ጋር የገጠመው ብሔራዊ ቡድናችን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከወዲሁ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

ቡድኑ በውድድሩ ላይ በአጠቃላይ 4 ጎሎች ሲቆጠሩበት ማስቆጠር የቻለው አንድ ጎል ብቻ ነው።

በተመሳሳይ ምድብ ውስጥ የነበሩት አልጄሪያ እና ሞዛምቢክ ከምድቡ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮና እየተካሄደ የሚገኘው በአልጄሪያ ነው።

ተጨማሪ : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x    

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ባንካችን አቢሲንያ ከሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት መሥራት ጀመረ፡፡

የባንካችን ደንበኞች የሳፋሪኮም አየር ሰዓት በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ወይም አቅራቢያዎ በሚገኙት የባንካችን ቅርንጫፎች መሙላት ይችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #MobileBanking #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Triple_E_Hotel በመዲናችን አ/አ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03፣ 22 በተለምዶ ዳውን ታውን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ባለቤትነቱ የአቶ  መስፍን ውብሸት በሆነው ኤሉዛይ ሆቴል እና ቱሪዝም ካምፓኒ የተገነባው ትሪፕል-ኢ ሆቴል እና ስፓ ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት ይኸው ሆቴል በ4 ዓመት ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ስራውን…
#Triple_E_Hotel

በመዲናችን ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03፣ 22 በተለምዶ ዳውን ታውን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ500 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈው ትሪፕል-ኢ ሆቴል እና ስፓ በትላንትናው ዕለት ተመርቋል።

ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተነገረለት ይኸው ሆቴል በ4 ዓመት ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ስራውን የጀመረው በሐምሌ ወር ነበር።

ሆቴሉን በምስል ለመጎብኘት 👉 https://telegra.ph/Triple-e-Hotel--Spa-01-20
#ETHIOPIA #USA

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊነከን ጋር በስልክ መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት አሳውቋል።

ውይይታቸው ትኩረቱን ያደረገው የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀም በተመለከተ እንደነበር ተመላክቷል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ይፋ ባደረገው መረጃ፤ የኤርትራ ወታደሮች ከሰሜን ኢትዮጵያ እየወጡ መሆኑን በማመልከት በዚህም ጉዳይ ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ መነጋገራቸውን ገልጿል።

ብሊንከን ፤ የታየውን መሻሻል (የኤርትራ ሰራዊት መውጣት መጀመር) በደስታ መቀበላቸው፤ ይህም በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቆጣጣሪዎች ወደየአካባቢዎቹ እንዲደርሱ አሳስበዋል።

ብሊንከን ፤ ሀገራቸው አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ላለው የሰላም ሂደት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪ፤ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና ብሊንከን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን አለመረጋጋት እንዲያበቃ በማድረግ አስፈላጊነት ላይም መመካከራቸው ተገልጿል።

ይህንን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን /ከጠ/ሚ ፅ/ቤት/ ከራሳቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።

የኤርትራ ወታደሮችን ከሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ከትግራይ ክልል መውጣትን በተመለከተ ከሰሞኑን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርገው ዘገባ እያቀረቡ ይገኛሉ ነገር ግን  ወታደሮቹ እየወጡ ስለመሆኑ ከአፍሪካ ህብረት/ ከኢትዮጵያ መንግሥት/ከትግራይ ክልል አመራሮች በኩል እስካሁን ምንም ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባከተማ #ሸገርከተማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሸገር ከተማ አስተዳደር የሰነድ ርክክብ መፈጸማቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ወደ አዲስ አበባ የተካለሉ በቀድሞ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የነበሩና በአዲሱ የአስተዳደር ወሰን መሠረት ወደ አ/አ እንዲካለሉ የተደረጉ አካባቢዎችን የተመለከቱ መረጃዎችና ሰነዶችን፣ አጎራባች ለሆኑ የአዲስ አበባ ክፍላተ ከተሞች ማስረከቡን የሸገር ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በተመሳሳይ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ሥር ሲተዳደሩ የነበሩና በተካለለው የአስተዳደር ወሰን መሠረት በቅርቡ ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወይም ወደ ሸገር ከተማ እንዲካለሉ የተደረጉ አካባቢዎችን የተመለከቱ ሰነዶችንም፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ማስረከቡ ተነግሯል።

"የባለቤትነት መብት የተፈጠረላቸው ላይ የሚቀየር ነገር የለም" ያለው አስተዳደሩ ወደ ኦሮሚያ የመጡት ፋይላቸው ዞሮ ርክክብ መፈጸሙን አሳውቋል።

በዚህ መሠረት ግንባታቸው ተጠናቆ ዕጣ የወጣባቸው የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ቤቶች የተገነቡት በአዲስ አበባ አስተዳደር ሲሆን፣ የቤቶቹ ባለቤቶች የተመዘገቡ ቆጣቢዎች በመሆናቸው ቤቶቹ ለቆጣቢዎች መተላለፋቸውን ገልጿል።

የሸገር ከተማ በቤቶቹ ላይ የሚፈጥረው አዲስ ባለቤትነት አይኖረውም የተባለ ሲሆን ወደ ሸገር አስተዳደር ሲተላለፉ የባለቤትነት መብት ተፈጥሮላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

የሸገር ከተማ ኃላፊነት ከዚህ በኋላ ያለውን ሁኔታ ማስተዳደር ብቻ እንደሚሆን ተገልጿል።

" የቤቶቹ ባለቤቶች መብታቸውን ይዘው በሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር ይተዳደራሉ " ያለው አስተዳደሩ፤ "የመሸጥ፣ የመለወጥና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው በሸገር አስተዳደር የሚከናወን ይሆናል" ብሏል።

👉 ተጨማሪ ያንብቡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#BerhanBank

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!
#ብርሃን_ባንክ
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን)

በ " ወሊሶ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን " ከፍተኛ የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት በተፈፀመበት ሁኔታ ቤተክርስቲያን ሕገወጥ ነው ያለችው የ " ጳጳሳት " ሹመት መከናወኑን ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህንን ክስተት ተከትሎ  ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ አስቸኳይ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው በመግለጫቸው ዝርዝር ጉዳዮችን ባያነሱም ዛሬ ማለዳ የተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" መሆኑን እና ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ፦

1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ  በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

3.  ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ  ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን) በ " ወሊሶ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን " ከፍተኛ የዶግማ እና ቀኖና ጥሰት በተፈፀመበት ሁኔታ ቤተክርስቲያን ሕገወጥ ነው ያለችው የ " ጳጳሳት " ሹመት መከናወኑን ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ይህንን ክስተት ተከትሎ  ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ አስቸኳይ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን…
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦

" በፈተና የሚያጸናው ሁል ጊዜ ፈተናዎችን እያሳለፈ ለዘመናት ሲጠብቃት የነበረ እግዚአብሔር ዛሬም ጥበቃውና መግቦቱ እንደማይለያት ሙሉ እምነት አለን ፣ በደረሰው ክስተትም እጅግ አዝነናል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ታዝናለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ3ሺ ዘመን በላይ የራሷን አንድነት ከማስጠበቅ አልፋ የሀገርን አንድነት ስታስጠብቅ ለሰው ልጆች አንድነት ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ስትሠራ የኖረች አሁንም ያለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነች።

ይህንን አንድነቷን የሚንድ ሕጋዊ ሰውነቷን የሚጥስ አላስፈላጊ ክስተት ተፈፅሟል።

በዚህም ቅዱስ ፓትርያርኩ በአስተላለፉት ጥሪ መሠረት ከሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከነገው ዕለት ጀምሮ የቅዱስነታቸውን ጥሪ በመቀበል እንድትገኙ።

የተፈጠረው ችግር በዝርዝርና በጥናት ቅዱስ ሲኖዶስ አይቶ የመጨረሻውን ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ ምእመናንና አገልጋዮች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሁላችሁም በየአላችሁበት ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ።

ተመሳስለውና የሌለ ሐሳብ እያቀረቡ ሕዝብን ከሚለያዩ ሠዎች እንድትጠበቁና እንድትጠብቁ በጽናት፣ በትእግስትና በፍቅር ሕጋዊ በሆነ ነገር ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን እንድትጠብቋት በአንድነቷ የተረከብናትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ለነገው ትውልድ ለማስረከብ የእያንዳንዳችንን ድርሻ እንድንወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "

(ከአ/አ ሀገረስብከት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ? ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦ " በፈተና የሚያጸናው ሁል ጊዜ ፈተናዎችን እያሳለፈ ለዘመናት ሲጠብቃት የነበረ እግዚአብሔር ዛሬም ጥበቃውና መግቦቱ እንደማይለያት ሙሉ እምነት አለን ፣ በደረሰው ክስተትም እጅግ አዝነናል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ታዝናለች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ…
" ክሰቱት በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት በመመልከት መንግስት ሕጋዊ ኃላፊነቱን ይወጣ " - የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ከፍተኛ የዶግማና ቀኖና ጥሰት በመፈፀም ተፈፅሟል ካለችው ህገወጥ የ " ጳጳሳት " ሹመት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግስት የቤተክርስቲያኗን ህጋዊ ሰውነት በማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አስቸኳይ ጥሪ አቅርባለች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " ሕጋዊ ሰውነቷ የተረጋገጠ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሕጋዊ ሰውነቷ የመጠበቅ የማስጠበቅ ኃላፊነቱ የመንግሥት ነው " ብለዋል።

የተፈጸመው ድርጊት " ግፍ ነው " ሲሉ የገለፁት ብፁዕነታቸው " መንግሥት ይሄንን ተመልክቶ የቤተ ክርስቲያኗን ሉዓላዊነት #በመጠበቅ እና #በማስጠበቅ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስተቱ #በሀገር ላይ ጭምር ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን በመጠቆም መንግስት በጉዳዩ ላይ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ባንካችን አቢሲንያ ከሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት መሥራት ጀመረ፡፡

የባንካችን ደንበኞች የሳፋሪኮም አየር ሰዓት በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ወይም አቅራቢያዎ በሚገኙት የባንካችን ቅርንጫፎች መሙላት ይችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #MobileBanking #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
STEMpower እና Visa ከTikvah-Ethiopia ጋር በመሆን የሚያዘጋጁት የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና በሰባተኛ ዙር ተመልሶ መቷል።

ባለፉት ዙሮች ወደ 1500 የሚጠጉ ሰልጣኞች መሳተፍ ችለዋል። በዚህ 7ተኛ ዙር ደግሞ ተጨማሪ 300 ሰልጣኞችን ለማሳተፍ ዝግጅት ተደርጓል። እርስዎም ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተመዝግበው የስልጠና እድሉን መጠቀም ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያካትተው፦

* የ6 ቀን መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ትምህርት እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና

* በተጨማሪ የ3 ወር የንግድ ማማከር እና ድጋፍ

* 9 ወር የማማከር ድጋፎች፣ የኔትዎርኪንግ እና የተለያዩ ክትትሎች በተጨማሪም ቢዝነ  ፕሮቶታይፕ (prototype) የሚያስፈልገው ከሆነ ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን በመጨረስ ላይ እንገኛለን።

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

- የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

- በግብርና፣ ጤና፣ አገልግሎት፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ እና ሌሎችም ዘርፎች የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

- ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ  ሰኞ ጥር 29፣ 2015 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.office.com/r/6jrgpFiwtt

@tikvahethiopia