TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BuleHora

በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ጉጂ ዞን ፤ ከቡሌ ሆራ ወጣ ብሎ በሚገኝ ማረሚያ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ከ400 በላይ እስረኞችን መልሶ ለመያዝ አሰሳ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው አስተዳደር ማሳወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጥቃቱ ከአንድ ሳምንት በፊት የተፈፀመ ሲሆን ጥቃት አድራሾቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነ ቡድን የተፈረጀው " ሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን)  መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸው ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ተኩስ ከፍተው አምስት (5) የፖሊስ አባላትን ከገደሉ በኋላ እስከ 480 የሚደርሱ እስረኞችን አስመልጠው እንደነበር በዘገባው ላይ ተገልጿል።

የቡሌ ሆራ ምክትል ከንቲባ አቶ ጊርጃ ኡራጎ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦

" ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እስረኞችን መልሶ ለመያዝ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል አሰሳ እያካሄደ በማሳደድ ላይ ነው።

ከእስር እንዲያመልጡ የተደረጉት የሕግ ታራሚዎች በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለው የቅጣት ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ የነበሩ ናቸው።

ሁሉም ታራሚዎች ናቸው የወጡት። እስከ 480 እስረኞች ይሆናሉ ብለን እንገምታለን።

አሁን ላይ በዚያ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስሮ የሚገኝ ትክክለኛ የታራሚ ቁጥር የለንም። ነገር ግን ያመለጡት ከ400 በላይ ይሆናሉ።

ካመለጡት መካከል የሸኔ ቡድን አባላት ይገኙበታል።

ታጣቂዎቹ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ አምስት የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት እና አንድ የአካባቢው ነዋሪን ገድለዋ ፤ ሁለት ሰዎችን አቁስለዋል። "

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia