TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

• የሞቱ እስራኤላውያን ከ700 በላይ ሆነዋል። ከ350 በላይ ፍልሥጤማውያንም ህይወታቸው ጠፍቷል።

#ኢራን ፍልስጤምን ደግፋ ስትቆም ፤ #አሜሪካ ከእስራኤል ጎን መሆኗን አረጋግጣ ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ እንደምትጀምር አሳውቃለች።

በእስራኤል ጦርና በፍልስጤሙ ሃማስ መካከል ጦርነቱ ዛሬም ተባብሶ መቀጠሉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በተለይም እስራኤል ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ብርቱ ውጊያ እየተካሄደ ነው ተብሏል።

በጦርነቱ እስራኤል ውስጥ ከ700 በላይ #እስራኤላውያን መገደላቸው ተሰምቷል።

እስራኤል ተከፍቶብኛል ላለችው ጦርነት እየወሰደች ባለችው የአፀፋ እርምጃ በጋዛ ሰርጥ ከ350 በላይ #ፍልጤማውያን ተገድለዋል።

በአጠቃላይ ባለፉት ሰዓታት ብቻ እስካሁን ይፋ በተደረገው ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተጎድተዋል።

ጋዛ ውስጥ መሰረተልማቶች ፣ ህንፃዎች እንዳልነበሩ ሆነዋል፣ የኤሌክትሪክ ፣ የነዳጅና የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት ተቋርጧል ፤ ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል። ሰብዓዊ እርዳታ የሚገባበት መንገድ እንኳን የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል የሊባኖሱ ሂዝቦላህ ከፍቶብኛል ላለችው ተኩስ በሊባኖስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈፅማለች።

ሂዝቦላም እስራኤል ላይ ተኩስ ስለመክፈቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።

ተኩሱ የተከፈተው እስራኤል፣ ሊባኖስ እና ሶሪያ በሚወዛገቡበት ግዛት እና ሶስቱንም ሃገራት በሚያገናኛቸው የዶቭ ተራራ አካባቢ ነው።

እስራኤል የሊባኖስ ታጣቂ ሂዝቦላህ በውጊያው ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቃለች።

ሃማስ ፤ እስራኤል በወረራ ከያዘቻቸው ግዛቶች ለመጠራረግ ፍልስጥኤማውያን እንዲሁም ሌሎች አረቦች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

እስራኤል ያለጥርጥር በበርካታ ግንባሮች ሊከፈት የሚችል ጦርነት ሊኖር እንደሚችል ነው እየታያት ያለው ተብሏል።

ምናልባትም ጦርነቱ የከፋ የሚሆነው ከፍተኛ ኃይል ያለውን የሊባኖሱን ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ መሳብ ከቻለ እንደሆነ ተነግሯል።

በእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት ሀገራት የተለያዩ አቋማቸውን እያንፀባረቁ ሲሆን ኢራን የሃማስን ጥቃት ደግፋ ቆማለች።

ኢራን " የፍልስጤምን ሕጋዊ የመከላከል መብት እደግፋለሁ " ብላለች።

አሜሪካ በበኩሏ ከእስራኤል ጎን እንደሆነች በተደጋጋሚ እያረጋገጠች ነው ፤ ወታደራዊ ድጋፍም ለማድረግ እየተዘጋጀች መሆኑ ተሰምቷል። የአሜሪካ መከላከያ ድጋፉን ከዛሬ ጀምሮ የሚልክ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ይደርሳል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ወታደሮቹን እያሰማራ ሲሆን በጋዛ ላይ ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ከማድረግ በተጨማሪ የምድር ላይ ዘመቻ ለማድረግ ማቀዱን ተሰምቷል።

መረጃው ከቢቢሲ እና አልጀዚራን ጨምሮ ከሌሎች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተገኘ ነው።

More - @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia