TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ሐሺ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ!

#የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት #ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የተጠባባቂና የምክትል ከንቲባ ሹመት አፀደቀ። ምክር ቤቱ  አቶ አብዲፈታህ ኢብራሂምን ተጠባባቂ ከንቲባ፣ አቶ ሐሺ አብዱላሂ ደግሞ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟቸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 957 ላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 123 ደርሷል።

የታማሚው ዝርዝር ሁኔታ ፦

- የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ #የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪ፤ ከፑንትላንድ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል። " ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ…
#Update

" በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች " - የሶማሌ ክልል መንግስት

የሶማሌ ክልል መንግስት ጅግጅጋ " ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት " የተከሰተውን ድርጊትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዛሬው እለት ከቀኑ 9:00 ላይ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ በጥበቃ ላይ የነበረ " የፌደራል ፖሊስ " አባል በከፈተው ተኩስ የ1 ሰው ህይወት ማለፉንና በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አሳውቋል።

" አባሉ በከፈተው ተኩስ የክልሉ ም/ቤት አባልና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም #ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች 4 ዜጎች በህክምና ተቋማት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል " ሲል ክልሉ አመልክቷል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ #በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከድረጊቱ በኋላ በኤርፖርት የተፈጠረውን ክስተት ወዳያኑ በቁጥጥር ስር በመዋሉ ኤርፖርቱ ወደ መደበኛው ስራ ተመልሷል ሲል ክልሉ በመግለጫው አሳውቋል።

በአሁኑ ሰዓት ክልሉ በተለይ #የጅግጅጋ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ እንደምትግኘ የገለፀው የሶማሌ ክልል መንግስት " ጉዳዩ ተመርምሮ ወደፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል " ብሏል።

@tikvahethiopia