TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና⬆️

2ኛው ቀኑን የያዘው የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች #ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው ዕለት:-

* ለህዝብ ቅርብ መሆንና በሚረዳው ቋንቅ ማናገር (How to be closer to the people and address them effectively in their setting?)

* ልህቀትን የሚያመጣ የአመራር ክህሎት (Leadership for Excellence)

* ፕሮቶኮል፣ የጊዜ አጠቃቀም እና ተያያዥ ጉዳዮች (Protocol, Etiquette and Time management)

* ውጤታማ የንግግር ክህሎት (Effective Public Speaking) በሚሉ ርዕሶች በአገር ውስጥ እና በውጭ -ባለሙያዎች ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ስልጠናውና ውይይቱ በዛሬው ዕለት #እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ጠ/ሚ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዳሴው ግድብ‼️

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በማስተካከል
በፈረንጆቹ 2022 #እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ #ውይይት እየተካሄደ ነው።

ጥልቅ ጥናትና ምርምር ስራ ሳይከናወንለት ግንባታው በመጀመሩ ምክንያት ግንባታ ጊዜው ሊጓተት እንደቻለ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስከተለው ጉዳት ሀገሪቷ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣ አድርጓታል ተብሏል።

የግንባታው ስራው በአሁን ወቅት የሚገኝበት ደራጀም በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ወቅት ይፋ ሆኗል።

በዚህም በሳሊኒ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ምህንድስናው ስራው 82 በመቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው ደግሞ 25 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል በውይይቱ ወቅት።

በአጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 65 በመቶ መጠነቀቁ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ የግንባታው ፅህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልና ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር የግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።

የህዝባዊ ተሳትፎን ፣ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው የሶስትዮሽ ግንኙነት እና የኃይል ሽያጭ ትስስር ላይ ትኩረት ባደረጉ አራት ጉዳዮች ላይ ውይይቱ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀምሌ 13/2010 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ የገባው የምህረት አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጊዜ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2011 #እንደሚጠናቀቅ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡ እስካሁን ድረስ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዕድሉ ተጠቃሚ መሆናቸው መገለፁም ይታወሳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ እስካሁን ባለው አፈፃፀም ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳልገጠመና አብዛኛው / ከ90 በመቶ በላይ ተፈታኝ ተማሪ / ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቱን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን የተነገሩት ትላንትና ምሽት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተፈታኝ ተማሪዎችን እና እየቀረበላቸው ያለውን መስተንግዶ በአካል ተገኝተው በተመለከቱበት ወቅት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃላቸው ነው።

ከ90 በመቶ በላይ ተማሪ ወደ መፈተኛ ተቋሙ መግባቱን የተገለፁት ሚኒስትሩ ሙስሊሞች እና የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አማኞች #ዛሬ እሁድ ጥዋት እንደሚገቡ ፤ ከዚህ በኃላ ሁሉም ተማሪ ገብቶ #እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል፤ ነገ ሰኞ ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት። " ያሉ ሲሆን " ይህ የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ። " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል። ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው። " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተማሪዎች የተሰጣቸውን መመሪያ አክብረው ፤ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲሰሩ እንዲሁም በምንም ነገር እንዳይሸበሩ አደራ ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ለተፈታኞቹ " የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ " ሲሉ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።

@tikvahethiopia