TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
86,660 ብር ደርሰናል!

ምዕራፍ አንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ሊጠናቀቅ ነው! 13,340 ብር ብቻ ይቅረናል(100,000 ብር)። የብሩን ማጠን ሳይሆን #አብሮነታችንን ማስመስከራችን ለቀጣይ ጉዟችን ትልቅ አቅም ይሆነናል። የዛሬው ህብረታችን ነገም ሌሎች ወገኖቻችን ለማገዝ ትልቅ አቅም ይፈጥርልናል።

#ኦሮሚያ #ሀረሪ #ደቡብ #ትግራይ #ሱማሌ #አፋር #ቤንሻንጉል #ጋምቤላ #አማራ #አዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር #ድሬዳዋ_ከተማ_አስተዳደር የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ትልቅ ክብር አለን!

Account number(CBE): 1000277462439

@tsegabwolde @tikvaethiopia
Alert‼️

#አፋር #ገዋኔ

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ እንዲሁም ከ ጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል። በተጨማሪም ወደ መቐለ የሚጒዙም የህዝብ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነገ ነሃሴ 20 እስከ መስከረም 30 በመላው ሀገሪቱ ይካሄዳል!!

ላለፉት አመታት በአብዛኛውን በከተሞች አካባቢ የሰራነውን ስራ #በማጠናከር ዘንድሮ ደግሞ ከከተማ ውጭ ወደሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትኩረታችንን እናደርጋለን።

ምን አይነት መፅሃፍት ነው ከቤተሰባችን አባላት የምናሰባስበው?

•ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ መፅሃፍትን/Text Book/ እንዲሁም አጋዥ መፅሃፍት ብቻ

•በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ትውልዱን ይጠቅማል፤ እውቀት ያስጨብጣል የምንላቸው መፅሃፍት።

•ትንሹ መስጠት የሚቻለው መፅሃፍ 1

•መፅሃፍቱ የሚገቡት ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ እና በአካል ሄደን ለምንለያቸው ቤተ መፅሃፍት

#እርሶ ምን ማድረግ ይችላሉ??

√ቢያንስ አንድ የመማሪያ መፅሃፍ ለሚወዷት ለኢትዮጵያ መለገስ ይችላሉ። እንዲሁም ከፍተኛ የመፅሃፍት ችግር ያሉባቸው ቦታዎችን በመለየት የማስተባበር ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

•TIKVAH-ETH በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ለምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ይህን ሀገራዊ ስራ እንድታግዙ ጥሪውን ያቀርብላችኃል።

•የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ከተማራቹባቸው እና ስትጠቀሟቸው ከነበሩት መፅሃፍ መካከል ቢያንስ አንዱን ለመጪው ትውልድ በስጦታ አበርክቱ።

•በStopHateSpeech ጉዞ ተሳታፊ የነበራችሁ የቤተሰባችን አባላት ይህን ለሀገርና ለትውልድ የሚሰራን ስራ በሙሉ አቅማችሁ እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

•በውጭ ሀገር የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቃሚ ናቸው የምትሏቸው መፅሃፍት በመላክ አልያም እዚህ ሀገር ባላችሁ ወዳጅና ዘመድ መፅሃፍት እንዲገዛ በማድረግ ይህን

#ኦሮሚያ
#አማራ
#ትግራይ
#ደቡብ
#ሱማሌ
#አፋር
#ሀረሪ
#ጋምቤላ
#ቤኒሻንጉል
#አ/አ ከተማ አስተዳደር
#ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

🏷በማኛውም አይነት ቋንቋ የተዘጋጀ የመማሪያ መፅሃፍ መለገስ ይቻላል!!
-------------------------------------------------------
በአሁን ሰዓት ልየታ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል፦

#ራያ_ቆቦ በራያ ቆቦና ዙሪያዋ የምትገኙ የቤተሰባችን አባላት መፅሃፍት ለመለገስ እና ይህን ስራ ለማስተባበር ከቤተሰባችን አባል #ሉላይ ጋር ይገናኙ፦ +251949256094

#ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ደግሞ ከቤተሰባችን አባል መሃሪ 0915034762/መሃሪ/ ጋር መገናኘት መፅሃፍ መለገስ ትችላላችሁ።

ሌሎች አካባቢዎች ላይ እኛም ለሀገራችን መስራት እንፈልጋለን የምትሉ እውቅና ያላችሁ ማህበራት ካላችሁ መልዕክት አስቀምጡልን @tsegabwolde 0919743630

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Amhara #Tigray #Afar

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ 🇪🇹 በግጭት በተጎዱ ክልሎች ላለው የጤና እና ሰብዓዊ ፍላጎቶች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አካላት ከ2 ቀን በፊት #በአማራ ክልል የወደሙ ሆስፒታሎችን በአካል የተመለከቱ ሲሆን የ2 ሚሊዮን ሰዎችን አስቸኳይ የጤና ፍላጎት ለማሟላት ወደ 100 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዳስረከቡ ድርጅቱ ገልጿል።

ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ #አፋር#ትግራይ እና ሌሎችም ክልሎች መላኩን ድርጅቱ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
የWFP ሪፖርት ምን ይላል?

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

#ትግራይ

በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ናቸው።

በትግራይ ክልል በተደረገው አስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዋስትና ግምገማ 83% የሚሆነው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ችግር አጋጥሞታል።

በዚህ ሳቢያ የተለያዩ ቤተሰቦች ያላቸውን ምግብ ሁሉ አሟጠው በመጨረሳቸው ጥራጥሬ ብቻ መመገብና የሚመገቡትን የምግብ መጠን ለመቀነስ ተገደዋል።

ከተመጣጣነ ምግብ አንጻር ግምገማው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች መካከል 13% እና ከነፍሰጡር ሴቶች ግማሽ ያህሉ እንዲሁም ጡት የሚያጠቡ እናቶች ለተለያዩ ችግሮች በሚያጋልጥ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ ችግር ገጥሟቸዋል።

#አማራ

በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ባለፉት 5 ወራት የረሃብ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል።

በዚህ ሳቢያ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 14%ና አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጣነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#አፋር

በአፋር ክልል በጦርነት በተከሰቱ መፈናቀሎች ምክንያት ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ ችግር መጠን ከፍ ብሏል።

በቅርቡ የተሰበሰበ መረጃ በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 28 በመቶው የተመጣጠነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።

#ሰሜንኢትዮጵያ- WFP በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ከ9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል።

በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲጓጓዝ እንዲፈቅዱ ጠይቋል፥።

ሙሉ ሪፖርት www.wfp.org/news/severe-hunger-tightens-grip-northern-ethiopia?s=09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቅልጥ ዓለቱ እንቅስቀሴ እስከቀጠለ ድረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ የመቀጠል እድል አለው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት አከባቢ በ 'አዋሽ ፈንታሌ' የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ንዝረቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል፡፡ ትናንት ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት መሰማቱ ይታወሳል። አሁንም ዳግም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ መከሰቱ ታውቋል። በአዲስ…
#አፋር

በአፋር ክልል ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

በቦታው የባለሙያ ቲም አዋቅሮ የላከው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው እንደተከሰተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጦ ለአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ በአጽንኦት አሳስቧል።

ህዝቡ ላይ የከፋ ከደጋ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊያደርጉት የሚገባው ርብርብ ምንድን ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ዩኒቨርሲቲው የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ኖራ ያኒሚኦ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

“ የአደጋው ምክንያት ምንነት አሁን ታውቋል። አደጋው የተፈጠረው የቀለጠ አለት በሚያደርገው እንስቃሴ ነው። 

ስለዚህ የከሰም ግድብ የሚባል ስኳር ፋብሪካ አካበቢ አለ። አደጋው እዛ አካባቢ ላይ የሚከሰት ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊያከተል ይችላል። ምክንያቱም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ እየተፈጠረ ነው።

አደጋው ካልቆመና የግድቡ አካል የሚነካ ከሆነ ከግድቡ ቁልቁለት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። 

ስለዚህ በተለይ የአዋሽ ፈንታሌ የወረዳ ካቢኔዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች ህብረተሰቡን ከቁልቁለታማው ቦታ የውሃ ፍስት ወደማይደርስበት ወደ ሌላ ቦታ ያውርዱ።

ተራራ ስር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ታዝበናልና እነዛ ሰዎች ወደ ሜዳ የሚመጡበት መንገድ ቢፈጠር ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል ”
ሲሉ አስገንዝበዋል።

የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ በበኩላቸው፣ ወደ ቦታው ባለሙዎችን እንደላኩ ገልጸው፣ “ በአካባቢው የግድብ ስራዎች አሉ። አደጋው ከጨመረ ቀፈን ቀበና ያለው ግድብ ትልቅ ፋክተር ተደርጎ ተፈርቷል ” ብለዋል።

“ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግለት ይገባል ግድቡ። አንዴ ጉዳት ከደረሰበት ህዝቡን ጠራርጎ ነው የሚወስደው። ከፍተኛ ቦታ ላይ ነው ያለው። በጣም ብዙ መሬትን ሊያካልል የሚችልም ነው ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አደጋው የሚጨምር ነው የሚቀንስ ? ምን እየተሰራ ነው ? አደጋው ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳትስ በምን ደረጃ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ተመራማሪና መምህር ኖራ በበኩላቸው ተከታዩ ማብራሪያ ችረዋል።

“ የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ነው። ከሦስት ሳምንታት ወዲህ የትላንት ስድስት ሰዓቱን ጨምሮ አደጋው ሦስት ጊዜ ተከስቷል።

መነሻው በክልሉ ሳቡሪ ቀበሌ ነው። ከዛ ተነስቶ ነው እስከ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ የሚሰማው።

በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አማካኝነት አንድ ቲም ተዋቅሮ ለሁለት ሳምንታት በቦታው ተገኝተን ምልከታዎችን እያደረግን ነው። ሙያዊ ሥራዎችን እየሰራን ነው። ለህዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠንም ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሚከሰትበትን ቦታ መለየት ይቻላል። በዚህ ሰዓት ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመት ግን አይደለም። አሁን ባለን ቴክኖሎጂና እውቀት ቦታዎቹን መለየት ብቻ ነው የሚቻለው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ዋናው ምክንያቱ ከሥር የቀለጠው አለት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ማግማው ወደላይ ሰንጥቆ መውጣት እስከሚያቆም ድረስ አደጋው ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል።

እስካሁን ድረስ እየተመዘገበ ያለው ከ4.5 እስከ 4.9 ሬክተር ስኬል አካባቢ ነው፤ ይሄም ያን ያክል ጉዳት የሚያደርስ አይደለም መካከለኛ ስኬል ነው። 7 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው አደጋው ከፍተኛ ሊሆን የሚችለው ”
ብለዋል።

በመጀመሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ቦታ ፍል ውሃ መፍለቁ፤ ነዋሪውም ውሃውን ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ይታወሳል፤ የተገኘ የምርምር ውጤት አለ እንዴ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ አሰስመንት ላይ ነን። ካጠናቀቅን በኋላ ሙሉ መረጃ እናጋራለን ” የሚል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Tigray " የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ? " የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። በሁለቱ ክልሎች…
#አፋር #ትግራይ

የትግራይ እና የዓፋር አጎራባች ዞኖች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት ለሁለተኛ ጊዜ በዓፋርዋ የአብዓላ ከተማ ተገናኝተዋል።

ለግማሽ ቀን በተካሄደው የሁለቱ ክልል አጎራባች ዞኖች አመራሮች ግንኙነት ፦
- የሁለቱም ክልል ህዝቦች የፊት ለፊት ግንኙነት እንዲጀመር፤
- የተከለከሉ መንገዶች ተከፈትው ነፃ የህዝቦች ግንኙነት እንዲቀጥል፤
- ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ክልል ህዝቦች የሰላም  እና የልማት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡
- ሁለቱም ክልሎች ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ፤
- ሁለቱም ክልሎች የሰላምና የፀጥታ እቅድ በማውጣት  በየወሩ እየገመገሙ እንዲጓዙ፤

ተወያይተው መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ግንኙነቱ በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላምና ልማት መሰረት እንዲይዝ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የላቀ ዝግጁነት አለው " ብሏል።  

በያዝነው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ዓፋር ሰመራ ድረስ በመጓዝ ከርእሰ መስተዳደር ሃጂ ኣወል ኣርባ ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Tigrai Television

@tikvahethiopia