TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጉዞ_ዓድዋ_6

በፈጣሪ ፍቃድ ከሐረር 61 ቀናት ከአዲስ አበባ ደግሞ 47 ቀናት ፈጅተን ከባዱን የእግር ጉዞ በድል ፈጽመን ማርያም ሸዊቶ #ሶሎዳ_ተራራ ግርጌ ዓድዋ ደርሰናል።

ፍቅር ለሆነው ህዝባችን ያለ አንዳች ችግር አብልቶ አጠጥቶ እዚህ ላደረሰን ደጉ ደራገሩ የገጠሩና የከተማው ወገናችን ቸር አምላክ ብድሩን ይክፈልልን።

ከሐረር እስከ አዲስ አበባ፣ ከለገጣፎ እስከ ሸኖ፣ ከደብረ ብርሐን እስከ ቆቦ ከአላማጣ እስከ ዓድዋ፤ ፍቅርን ለመገባችሁን፣ በኢትዮጵያዊነታችን ዳግም እንድንኮራፕ ላደረጋችሁን ብሩካን እናቶችና አባቶቻችን እህቶችና ወድሞቻችን ክብር ይግባችሁ።

"እምዬ አዝምቶ አንስቶ ጋሻ
ድል ባያመጣ አትኖር እንዳሻህ
በእቴጌ ብልሐል ጦር ባይፈታ
ሐገር የለችም የዚያኔው ሞታ
ሚካኤል ብጡል መንገሻ አሉላ
ሐገር የላቸው ከኢትዮጵያ ሌላ"
ፈለግ ተከትለን!!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ።
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via ያሬድ ሹመቴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia