TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ናይሮቢ🔝

ዛሬ በናይሮቢ መድኃኒያለም ቤተ ክርስትያን፤ ባለፈው ሳምንት መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ኢቲ 302፤ ሕይወታቸውን ላጡ 157 መንገደኞች የመታሰቢያ ፀሎት ተደርጓል።

በፀሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መለስ ዓለም፣ የፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን መልዕክት ያስተላለፉት አምባሳደር ማቻሪያ ካማዎ፣ በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር አቶ በየነ ርዕሶም እንዲሁም የኢትዮጵያውያንም የኬንያውያንም ሟች ቤተስቦችና ተወካዮቻቸው ተገኝተው ነበር። የሩስያና የታይላንድ የኤምባሲ ተወካዮችም እንዲሁም ሌሎች ዲፕሎማቶች በፀሎት ሥነ ሥርዓቱ ተገኝተዋል።

በፀሎት ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉትና የአውሮፕላኑ አደጋ በደረሰበት ዕለት ወደ ናይሮቢ የመጡት አቶ መለስ ዓለም በተከሰከሰው አውሮፕላን #ሊሳፈሩ እንደነበርም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምባሳደር መለስ አለም...

ዛሬ #በናይሮቢ መድኃኒያለም ቤተ ክርስትያን ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ #ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦንግ 737 ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች የመታሰቢያ ፀሎት ስነ ስርዓት ላይ አምባሳደር #መለስ_አለም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በፀሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር #መለስ የአውሮፕላኑ አደጋ በደረሰበት ዕለት ወደ ናይሮቢ እንደመጡና #በተከሰከሰው አውሮፕላን #ሊሳፈሩ እንደነበርም ተናግረዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia