TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኮሚሽነር ዘይኑ⬆️

በዛሬው ዕለት 240 የሚሆኑ የመብት ጥያቄ ያላቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከእነ ትጥቃቸው ወደ ቤተ መንግሥት በማምራታቸው ተፈጥሮ የነበረው መደናገጥ መረጋጋቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

ወታደሮቹ ከሃዋሳ የቡራዩን ጉዳይ ለማብረድ የተጠሩ መሆናቸውንና ግዳጃቸውን ጨርሰው ወደ ምደባ ቦታቸው በሚመለሱበት ጊዜ “ዶ/ር *አብይ ነው ችግራችንን የሚፈታው” በሚል ወደ ቤተመንግስቱ በቀጥታ ማምራታቸውን ኮሚሽነር ገልፀዋል።

በመጨረሻም #ትጥቃቸውን ፈተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር #ውይይት አድርገዋል ተበሏል። ወታደሮቹ ዓላማቸው ምን እንደሆነ እስኪታወቅ ድረስም ሌላ ኃይል ተጠርቶ አካባቢው በጥበቃ ስር እንደነበር ተናግረዋል።

ምንጭ፦ VOA(የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል‼️

#በአሶሳ_ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ “ታምሚያለሁ” በሚል ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዲሄድ በመፍቀድ በግለሰቡና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ ሶስት #የፖሊስ_አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማደር አኑር ሙስጣፋ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በከተማው የወረዳ ሁለት መደበኛ ፖሊስ አባላት የሆኑ ሶስት ግለሰቦች ማምሻውን #ትጥቃቸውን ፈትተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የፖሊስ አባላቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ላቀረበው የ”ታምሚያለሁ” ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከተው የወረዳው አካል ትዕዛዝ ሳያገኙ በራሳቸው ፈቃድ ግለሰቡን ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰዳቸው ነው፡፡

የጸጥታ ሃይሎቹ ተጠርጣሪውን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ሲገባቸው ወደ መኖሪያ ቤቱ መውሰድ እንዳልነበረባቸው ኮማንደር አኑር አስረድተዋል፡፡

ግለሰቡም ወደ መኖሪያ ቤቱ በተወሰደበት ወቅት ክላሽንኮብ በማውጣት በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በከተማው በተወሰኑ ቦታዎች አለመረጋጋት ታይቶ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ግን የከተማው ሁኔታ በጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ነበረበት እንደተመለሰ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FDRE_Defense_Force

" በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ከ3 ዓመታት በላይ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ1 ሺ በላይ አመራሮችና አባላት በጉሙዝ ብሔረሰብ ዕርቀ ሰላም ባህል "ማንገማ" መሠረት #ትጥቃቸውን_አስረክበው_እርቅ_አካሂደዋል

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ " በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " ብለዋል።

ለፈፀሙት ቃለ-መሃላም ሁሉም ተገዥ በመሆን ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ቁርጠኝነቱን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ ህገወጥ ታጣቂዎችም የአፍራሽ ኃይሎችን ተልዕኮ ከማስፈፀም ተቆጥበው ቅድሚያ #ለሰላም ዕድል መስጠት እንደሚገባቸው ጥሪ አስተላልፏል።

#FDRE_Defense_Force

@tikvahethiopia