TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" በምጥ የተያዘችን እናት ሊያመጣ ሲሄድ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል " - የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር   የአምቡላንስ ሼፌሩ በተተኮሰበት ጥይት #ተገደለ። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይዎት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ሰዓት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት…
#UPDATE 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያወጣውን የሃዘን መገለጫ ዋቢ በማድረግ ጥር 3 /2016 በትግራይ ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይወት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉ መዘገባችን ይታወሳል።

የቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌሩ እንዴት ለህልፈት እንደበቃ የሚያትት ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ እንዳባፃሕማ ወረዳ፤ ዕዳጋ ዓርቢ ከተማ ፓሊስ የደረሰን የምርምራ ወጤት እንደሚከተለው አቅርበናል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በእምባስነይቲ እንዴት ተመታች ? ሹፌሩስ እንዴት ለህልፈት ተዳረገ ? 

ፖሊስ ፤ አከባቢው ህጋዊ ያልሆነ ትጥቅ በተምቤን ትግራይ ክልል አድርጎ ወደ ሰቆጣ አማራ ክልል የሚተላለፍበት እንደሆነ በጥናትና ክትትል ቀደም ብሎ እንደደረሰበት ይገልጻል።

ስለሆነም ጥር 2/2016 ቀን ላይ በአምባስነይቲ ነበለት በተምቤን ወደ ሰቆጣ 80 መሳሪያ ከነተተኳሹ በሌሊት እንዲተላለፍ እየተደሎተ መሆኑ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል።

ገዢና ሻጮች ወደ እምባስነይቲ ዕዳጋ ዓርቢ ነበለትና አከባቢው መግባታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ፓሊስ በአከባቢው ከሚገኙ ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች በመቀናጀት መሳሪያው ከገዢና ሻጭ እንዲሁም አሻሻጭ ደላሎች እጅ በፈንጅ ለመያዝ በተጠንቀቅ ቆመ። 

ፓሊስ ቀን ላይ ገዢና ሻጭ እንዲሁም አሻሻጭ ደላሎች ያረፉበት ሆቴል የሚዘዋወሩባቸው ቤቶችና ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲከታተለ ውሎ አመሸ። 

ፓሊስ ከአከባቢው ተገዝቶ የሚጓጓዘው መሳሪያ ከነተተኳሹ በመኪና እንደሚጓጓዝ መረጃው ቢደርሰውም፤ መኪናዋን የሚያሽከረክራት ሹፌርና የመኪናዋ ዓይነት አልለየም ነበር።

ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር  አምቡላንስ በወሊድ ምጥ የተያዘች እናትን ከአከባቢው የተሻለ ህክምና ወዳለበት ከተማ ለመውሰድ በእምባስነይቲ ነበለት ዓዲ ፌላ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ተገኘች። 

ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ፓሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ህጋዊ ያልሆነ ትጥቅ ከትግራይ ወደ አማራ ክልል ለማሸጋገር የምትበረው መኪና ከነግብረአበሮችዋ ለመያዝ በተጠንቀቅ እያሉ አምቡላንስዋ ተከሰተች።

አቶ ወልዱ አረጋዊ የሚነዳት አምቡላንስ የወላጅ እናት ህይወት ለመታደግ በጉዞ ሳለች በድቅድቅ ጨለማ በአሳቻ ቦታ " ቁም ! " የሚል የፀጥታ አካላት ትእዛዝ እንደተሰጣት ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ፤ ሟች " ቁም " የሚለውን ወታደራዊ ትእዛዝ ሳይቀበል በመቅረት አምቡላንስዋን መንዳቱን ቀጠለ ይላል።

" ቁም !ቁም !ቁም " የሚለው ድምፁ እንጂ መልኩ የማይታየው ከድብቅ ቦታ የሚሰማው ማስጠንቀቅያ ትእዛዝ ቀጠለ። ሟች አምቡላንስዋ አላቆማትም ። አንደኛ ኬላ አልፎ ሁለተኛ ኬላ ደርሶ ለማለፍ ሲሞክር አምቡላንስዋ ተተኮሰባት ሟችም ተተኮሰበት። መኪናዋ ቆመች ፤ የወልዱ ህይወትም በዚህ መንገድ ተቀጠፈ።

ይህ አደጋ ካጋጠመ በኃላ ቀን ሙሉ በድብቅ የፓሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ክትትል የዋለችው ህጋዊ ያልሆነ መሳሪያ የጫነችው መኪና ተከትላ እንደመጣች ፖሊስ ገልጿል።

መኪናዋ ከተወሰኑት ግብረ አበሮች ከጫነችው ህጋዊ ያልሆነ መሳሪያና ተተኳሽ ጭምር በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ዋለች። 

በአምቡላንስዋ የነበሩና ከአደጋው የተረፉ ሃኪሞች ሟች ቁም ሲባል ለምን እንዳልቆም አስመልክቶ ከፓሊስ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ቃል፤ እንዲቆም የተጠየቀበት ቦታ ከከተማ ውጪ እንዲሁም ጨለማ ስለነበር #ዘራፊዎች መስለውት ለማምለጥ እሰቦ ነው ብለዋል።

አቶ ወልዱ አረጋዊ ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት ነበር።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

" በችግር ላይ ሌላ ችግር  በህዝቡ ላይ የመጫን ፍላጎት የለንም ፤ አሁን የገጠመን ፈተና እናልፈዋለን። አባቶች በፀሎትና ምክር አግዙን !! " - ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከአበው ጳጳሳት እና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በኣክሱም ከተማ መወያየታቸውን የሚገልጽና አንድ ንግግር ሲያደርጉ የሚታይበት ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ቪድዮው በትግራይ ፐብሊክ ሚዲያ (TPM) የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ነው የተሰራጨው።

ሊቀመንበሩ የ5 ደቂቃ ርዝማኔ ባለው ንግግራቸው  ፥ " እኔ ለድርጅትና ለህዝብ ደህንነት ስል ብዙ ታግሻለሁ ፤ ትዕግስትና ዝምታዬ ግን መልካም ነገር ሳይሆን አደጋ ነው ያስከተለው ፤ ስለሆነም ከአሁን በኋላ መታገስ ሳይሆን ተመጣጣኝ ሰላማዊ ትግል ነው የሚያዋጣው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ የውጭ ጠላት አለብን የውስጥ ጉዳይ አናቆየው በማለታችን በውስጣችን ብዙ ችግሮች እንዲፈጠሩ ሆኗል " ያሉት ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ " ከአሁን በኋላ የጎራ መደበላለቅ አይኖርም አቋማችን በግልፅ በማንፀባረቅ ሰላማዊ ትግል ማካሄዳችን እንቀጥላለን " ብለዋል።

" በሃይል ፍላጎቴን አሳካለሁ የሚል አካል ሃይ ሊባል ይገባዋል ፥ በትግራይ በጉልበት እሰራለሁ ማለት አያዋጣም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከአሁን በኋላ ከህዝብ የሚደበቅ ሚስጥር አይኖርም " በማለትም ተናግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ " የተፈጠረውን ልዩነት በሰላም እንጨርሰው ፤ የማይሳካ ከሆነ ግን ሉአላዊነታችንን አሳልፈን አንሰጥም ፤ አቋማችን ግልፅ በማድረግ እንታገላለን " ብለዋል።

" አንድ በማያደርገን አንድ ሁኑ አትበሉን  በፓለቲካ አንድ በማያደርግህ አቋም አንድ መሆን አይቻልም ፤ ተከባብሮ በሰላም መስራት ግን ይቻላል ፤ ትግራይ ለሁሉም በቂ ናት " ሲሉም ደብረጽዮን (ዶ/ር) አክለዋል።

ህዝቡ ላይ በችግር ላይ ሌላ ችግር መጫን  እንደማይፈልጉ የተናገሩት ሊቀመንበሩ ፥ የተፈጠረው ሁኔታ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንዳልሆነና በሰላማዊ አግባብ እንደሚፈታ በማመላከት የሃይማኖት አባቶች በፀሎትና በምክር እንዲረዱዋቸው ጠይቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያመቐለ #TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia