TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬆️

የጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስትን በመምራት ላይ ሚገኘው የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ የማዕከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የጀመረው #ግምገማ ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ
ገልጸዋል፡፡

በግምገማው ላይ የተገኙት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የክልሉ ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር ጊዜውን በግል አጀንዳዎችና #ሽኩቻ ከማጥፋ ይልቅ ራሱን ከጎሰኝነትና ከጥላቻ በማጽዳት የክልሉን አመራር በማጠናከር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ክልሉ በርካታ ሙያተኞች በየዩኒቨርሲቲው፣ በፌዴራል፣ በክልሉም ሆነ በዳያስፖራ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን በማፈላለግ በየደረጃው ክልሉን ለማጠናከር #ቅድሚያ ሰጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮችም በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸው እና ህዝቡን ለመካስ በተመደቡበት የስራ መስክ ለመሰማራት መወሰናቸው መልካም መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር እና የክልሉ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑነት አቶ ጋትሉዋክ ቱት እና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ኃላፊነታቸው #መልቀቃቸውና ፓርቲው አቶ ኦሙድ ኡጁሉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አኙአያ ጃከን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ትናንት #መምረጡ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia