TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#RWANDA

ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ስማርት ስልክ ማምረቻ ከፈተች። ፋብሪካው በዋና ከተማዋ ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በምረቃው ላይ ፕሬዚደንት ፓል ካጋሜ ተገኝተዋል። በማራ ግሩፕ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ማራ ኤክስና ማራ ዜድ ስማርት ስልኮችን የሚያመረተው ይህ ፋብሪካ ስልኮቹ የጎግልን አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደሚጠቀሙ ተናግሯል። ስልኮቹ 5500 ብርና 3700 ብር አካባቢ ዋጋ ተተምኖላቸዋል።

ሰኞ ዕለት ፋብሪካውን ጋዜጠኞች ተዟዙረው እንዲጎበኙ ከተደረገ በኋላ "ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ነው" ብለዋል የማራ ግሩፕ የበላይ ኃላፊ አሺሽ ታካር ለሮይተርስ። ታካር አክለውም ፋብሪካው ዒላማው ያደረገው ጥራት ላይ መሠረት አድርገው ለመክፈል የተዘጋጁ ግለሰቦችን ነው። በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተለያዩ መለዋወጫዎችን ከቻይና በማስመጣት የሚገጣጠሙ ስማርት ስልኮች እንዳሉ ሚስተር ታከር ይናገራሉ።

"እኛ በማምረት ደረጃ የመጀመሪያዎቹ ነን። ማዘር ቦርዱን፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ንዑሳን ክፍሎቹን የምናመርተው እዚሁ ነው። በእያንዳንዱ ስልክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ነገሮች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። በቀን 1200 ስልኮችን ያመርታል የተባለው ይህ ፋብሪካን ለማቋቋም 24 ሚሊየን ዶላር እንደወጣበት ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ካጋሜ ፋብሪካው የሩዋንዳውያንን ስማርት ስልክ ተጠቃሚነት እንደሚጨምር ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት በሩዋንዳ ከሚገኙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች 15 በመቶው ብቻ ስማርት ስልክ ይጠቀማሉ።

Via BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RWANDA

ሩዋንዳ ዛሬ አንድ (1) ተጨማሪ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሪፖርት አድርጋለች። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከዚህ ቀደም ቫይረሱ ከተገኘበት ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበረው ነው። አጠቃላይ በሩዋንዳ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል። 4 ሰዎች አገግመው ከህክምና ማዕከል መውጣታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RWANDA

በሩዋንዳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 110 ደርሷል!

ባለፉት 24 ሰዓት በሩዋንዳ 772 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አምስት (5) ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ተረጋግጧል። ከአምስቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል አራቱ (4) ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RWANDA

በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 1,160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 126 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት (7) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 25 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SOMALIA #RWANDA #SUDAN

- በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 923 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቅላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 136 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 5 ተጨማሪ ሰዎች አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 54 ደርሰዋል።

- ዛሬ በሱማሊያ 3 ሰዎች በመሞታቸው አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል። በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥርም 60 ደርሷል፤ ከእነዚህም ውስጥ የ20 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ነው።

- በሱዳን ዛሬ አዲስ ኬዝ አልተመዘገበም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SOMALIA #SUDAN #RWANDA

- በሱማሊያ APRIL 16 በተደረገ 47 የላብራቶሪ ምርመራ 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል።

- በሱዳን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 66 ደርሰዋል። የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት 33 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 66 ደርሰዋል። በተጨማሪ 4 ተጨማሪ ሰዎች በመሞታቸው የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል።

- በሩዋንዳ APRIL 16 በተደረገ 760 የላብራቶሪ ምርመራ 5 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 143 ደርሷል። እንዲሁም 5 ተጨማሪ ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 65 ደርሰዋል።

- በዩጋንዳ አዲስ ኬዝ አልተመዘገበም፤ 55 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#RWANDA

ሩዋንዳ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ለአስፈላጊ ነገሮች ከቤቱ የሚወጣ ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የማጥለቅ ግዴታን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሯን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RWANDA

በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 1,299 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 147 ነው።

በሌላ በኩል አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በማገገማቸው አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 80 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Rwanda #UK

ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።

የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?

" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።

አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።


በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።

በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA

@tikvahethiopia
#Rwanda

በሩዋንዳ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖል ካጋሜ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ያልተጠናቀቀ ቆጠራ አሳይቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በበርካታ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ባካሄደው ቆጠራ (79% ቆጠራ) ካጋሜ 99.15 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል።

24 ዓመታትን ሩዋንዳን በፕሬዜዳንትነት የመሩት ፖል ካጋሜ ውጤቱ ለተጨማሪ 5 ዓመታት በስልጣን እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል።

ሶስት ብርቱ ናቸው የተባሉ ተቀናቃኞቻቸው ከምርጫ ፉክክሩ ውጭ በሆኑበት ነው ምርጫው የተካሄደው።

በምርጫው የተሳተፉት የአየር ንብረት ጥበቃ ተሟጋች ፍራንክ ሃቢኔዝ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ፊሊፕ ምፓይማና ከ1 በመቶ ያነሰ መራጭ ነው ያገኙት።

ከዚህ በፊት በነበረው የአውሮፓውያኑ 2017 ምርጫ ካጋሜ በ98.8 ድምጽ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ፖል ካጋሜ እኤአ 1994 የሩዋንዳ የዘር ፍጅት በኋላ በመሪነት ስፍራ የተቀመጡ ሲሆን ከ2000 በኋላም በፕሬዚዳንትነት ቀጥለዋል።

#BBC #AlJazeera

@tikvahethiopia