TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኦዲት

#ለተከታታይ_ዓመታት ለተገኘበት በርከት ያለ የኦዲት ክፍተት ማስተካከያ ማድረግ እንደተሳነው የተገለፀው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአመራር መቀያየር ባለፈ ጥብቅ ሪፎርም እንደሚስፈልገው የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።

ይህንን ያስታወቀው፤ የሕ/ተ/ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2014 / 15 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ላይ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ሲደረግ ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ ምን አለ ?

ኮሚሽኑ ፦
📄ለሚፈጽማቸው ክፈያዎች ደረሰኝ ባለማቅረብ፣
📄ኮፒ ደረሰኝ መጠቀም፣
📃በኮፒ ደረሰኝ ሂሳብ ማወራረድ፣
📄ያልተፈቀደ ክፈያ በመፈጸም፣
📄ለተከፈለ ገንዘብ ማስረጃ ባለማቅረብ፣ እንዲሁም #በቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ተከፋይ እና ተሰብሳቢ ውዝፍ የኦዲት ሪፖርት ተገኝቷል።

- ከሳዑዲ ከስደት ለተመለሱ 102 ሺህ ኢትዮጵያውያን ለኪስ አበል እንዲሁም ለቤት ኪራይ 5.2 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ሳይቀርብ ተከፍሏል። ተከፈለ ለተባለው ለዚህ ገንዘብ ሰነድ ማግኘት ባለመቻሉ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልታቻለም።

- ለምግብ ዝግጅት ድርጅት ተብሎ የተከፈለና በወጪ የተመዘገበ 2.9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ዋጋው ከ65.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 14 ሺህ ኩንታል ዱቄት " ናህሊ ዱቄት ፋብሪካ " ለተስኘ ድርጅት የተከፈለ ተብሎ የቀረበ ቢሆንም የቀረበው ደረሰኝ ግን ኮፒ ነው።

- በወጪ ሒሳብ ለተመዘገበ 79 ሚሊዮን ብር ለኦዲት ሥራ የሚፈለጉ የወጪ ማስመስከሪያዎች (ቫውቸሮች) ከደጋፊ ሰነዶች ጋር እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም።

- ያልተወራረደ 881.5 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩ በኦዲት ሪፖርት ቢረጋገጥም፣ ከኦዲት ግኝት በኋላ የተወሰደ ማስተካከያ የለም።

➡️ በወቅቱ ያልተወራረደ 39.7 ሚሊዮን ብር ተከፋይ ሒሳብና ያልተከፈለ ሲሆን ከኮሚሽኑ መደበኛ በጀት 37.6 ሚሊዮን ብር በሥራ ላይ አልዋለም።

በተጨማሪም ፦

* ውኃ የሚያስገቡ እና ጣሪያቸው የሚያፈሱ መጋዘኖች ተገኝተዋል።

* በቆይታ ብዛት የተበላሸ ብስኩት ሳይወገድ በግምጃ ቤት ተገኝቷል።

* የቆይታ ጊዜያቸው የማይታወቅና በውስጣቸው ምን እንዳለ የማይታወቅ የታሸጉ 9 ኮንቴነሮች በመጋዘን ግቢ ውስጥ ተገኝቷል።

* የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ፦
🔹ሴሪላክ የዱቄት ወተት፣
🔹የወይራ ዘይት፣
🔹የምግብ ዘይት፣
🔹ብዛት ያላቸውና ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቴምሮች፣
🔹የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ተገኝቷል።

* በእህል መጋዘኖች ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያልፍ #ሁለት እና #ሦስት ወራት የቀራቸው አልሚ ምግቦች፣ ሳሙናዎችና እህሎች ተገኝቷል።

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም የኦዲት ሪፖርት ላይ ለመምክር በተጠራው ውይይት አለመገኘታቸው ቋሚ ኮሚቴውን አስቆጥቷል።

በወቅቱ ውይይቱ ላይ የተገኙት ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ኮሚሸነሩ የቀሩት ሌላ ተልዕኮ ስለነበራቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ምን አሉ ?

° ኮሚሽኑ ኃላፊዎችን #ከመቀያየር ባለፈ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገዋል።

° በ2014 ዓ/ም የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲተሮች ለጊዜያዊ የኦዲት ሥራ የተረከቡትን ቢሮ ኦዲት አድርገው በሚወጡበት ጊዜ የኮሚሽኑ ሠራተኞች በመግባት #ሰነድ እያወጡ መሆኑን መረጃ አለኝ።

° ይህ ኮሚሽን ለፈጸማቸው ክፍያዎች ሰነድ ማቅረብ አለመቻሉ መሠረታዊ ችግሩ ነው።

° ከዚህ በፊት የበላይ ኃላፊው ቢታሰሩም ኮሚሽኑ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልተነቀለም፣ በመሠረታዊነት ችግሩ አልተቀረፈም።

° በመጋዘኖች ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ከፍተኛ ችግር አለ። ገንዘቡ አንዴት እንደሚመጣ እናውቀዋለን ነገር ግን እዚህ ያለው ሥራ የተዝረከረከ ነው፡፡

° በ2013 ዓ.ም. #ድሬዳዋ እና #ሻሸመኔ በሚገኙ መጋዘኖች ከታዩ ችግሮች በመነሳት የኦዲት አስተያየት የተሰጠንባቸው ጉዳዮች በ2014 ዓ.ም በድጋሚ ኦዲት ሲደረግ በነበሩበት እንጂ ተስተካክለው አልተገኙም።

° " ደመወዝ የምንበላበት ተቋም ነው፣ ስለዚህ እዚያ ያለውንም ሥራ ልክ እንደ ቤታችን ማየት አለብን፡፡ ይህ ሁሉ ቁሳቁስ የሚገዛው በብድር ነው እናውቃለን፡፡ እዚህ አምጥተን በአግባቡ የማይውል ከሆነ፣ መሬት ላይ የሚደፋና ከጋዝ ጋር ተቀላቅሎ የሚበላሽ ከሆነ ሥራው ትርጉም አልባ ነው "

° በዚህ ውይይት ላይ ያልተገኙት #ኮሚሽነሩ የቀሩት ዕርዳታ ለማፈላለግ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ተቋሙ የተገኘውን ንብረት በተገቢው መንገድ ማስተዳደር ካልተቻለ፣ ዕርዳታ ማፈላለጉ ብቻ ትርጉም የሌለውና በቀዳዳ በርሜል ውኃ እንደመሙላት የሚቆጠር ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የኢንስፔክሽን መምርያ ኮሚሽኑ በኮፒ ደረሰኝ ሒሳብ እንደሚያወራረድ በተደጋጋሚ ቢነገርም ሊስተካከል ባለመቻሉ ይህንን ያደረገ ኃላፊ መጠየቅ አለበት ብሏል።

More - https://telegra.ph/Reporter-12-14-2

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ "ሪፖርተር ጋዜጣ " መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia