TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሞንቴኔግሮ ከኮቪድ-19 ነፃ መሆኗን አሳውቃለች!

ሞንቴኔግሮ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) #ነፃ መሆኗን በትላንትናው ዕለት አሳውቃለች። በአጠቃላይ 324 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 315 ሰዎች አገግመዋል።

ምንም እንኳን ሞንቴኔግሮ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ነፃ ብትሆንም የቫይረሱ ስርጭት ዳግም እንዳያገረሽ የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደሚቀጥሉ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀገሪቱ ከግንቦት 24 ጀምሮ ያወጣችውን መስፈርት ለሚያሟሉ የአውሮፓ ሀገራት ዜጎች #ድንበሯን ለመክፈት እየተዘጋጀች እንደሆነ ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,500 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1934 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 75 ወንድ እና 54 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት…
#TikvahEthiopia #AtoKanGalwak

በጋምቤላ ክልል የተመዘገበው የመጀመሪያው ኬዝ !

የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካን ጋልዋክ ዛሬ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ28 ዓመት እድሜ ያለው ደቡብ ሱዳናዊ መሆኑን ነገረውናል።

ድንበር ከተዘጋ በኃላ ደንበሩን አቋርጦ ወደ ጋምቤላ ክልል የገባና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ነው።

ግለሰቡ ወደ ማቆያ እንዲገባ የተደረገው የዛሬ ሁለት ሳምንት ሲሆን በተደረገለት ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። ወደ ህክምና ማዕከልም እንዲገባ ተደርጓል።

ከእሱ በተጨማሪ ወንድሙ አብሮት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ሲሆን በተደረገለት ምርመራ ከቫይረሱ #ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብ ደንበር በማቋረጥ ተደጋጋሚ ምልልሶች የነበሩት ሲሆን ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎችን ወደ ኳራንቲን ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የደህንነት ኃላፊ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አቶ ኃይለማርያም እና ቤተሰባቸው ምርመራ እስኪደረግላቸው እራሳቸውን አግልለው የቆዩ ሲሆን የምርመራ ውጤታቸው #ነፃ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሶማሊያ አሚሶም ሰላም ማስከበር የሴክተር ሶስት 6ኛው ዙር የሠላም አስከባሪ ዘማቾች በአዲሱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግንባታ ስትራቴጅ እና የሰራዊት ግንባታ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሂሳዊ እይታ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ውውይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት የሴክተር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አለሙ አየነ ሠራዊቱ የህገ-መንግስቱ ጠባቂና የዜጎች ሃብት እንጂ መንግስታት እና ፓርቲዎች በተቀያየሩ ቁጥር የሚቀያየር እና የሚበተን ሃይል እንዳልሆነ ገልፀዋል። ሰራዊቱ በፖለቲካ ፓርቲዎች እና በድርጅቶች በሚራመዱ አስተሳሰቦች ሰለባ እንዳይሆንም መጠንቀቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

እኛ እንደ ሰራዊት የድርጅቶችና የፓርቲዎች ርዮት አለም ሃሳብ ተሸካሚዎችና አራማጆች ሳንሆን ፣ ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት #ነፃ በመሆን በህገ መንግስቱ መሰረት በህዝብ ተመርጦ ወደ ስልጣን የመጣን ሃይል የማክበርና የመደገፍ እንጂ በሃይል መሳሪያ ታጥቆ ህገ መንግስቱን ለማፍረስ እና አገርን ስጋት ላይ የሚጥል ሃይል ካለ ተቀባይነት የለውም ሲሉ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት የፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራምና ሜሴንጀር መቋረጥ ለሌሎች ተመሳሳይ አይነት አገልግሎት ለሚሰጡ መተግበሪያዎች ትልቅ በር ከፍቶ ነው ያለፈው።

ትዊትር በትላንትናው ዕለት በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አስመዝግቧል።

ዛሬ ምሽት የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ይፋ ባደረጉት መረጃ ፥ በአንድ ቀን ብቻ ከሌሎች ፕላትፎርሞች 70 ሚሊዮን አዳዲስ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ተመዝግበዋል።

ፓቬል ዱሮቭ ፤ አዳዲስ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን "ወደ ትልቁ #ነፃ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ወደ #ቴሌግራም እንኳን በደህና መጡ" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ነፃ_ዋይፋይ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ፣ እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ እና የወዳጅነት አደባባዮች በከፍተኛ ወጪ የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት ገንብቶ በነጻ ማቅረቡን ዛሬ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም !

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

👉 1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

👉 45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

👉 100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

👉 የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

(ማስታወሻ ፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።

@tikvahethmagazine
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአዲሱ ረቂቅ የትምህርት እና ጥናት ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ከፍል የሚሰጥ ትምህርት #ነፃ እና #አስገዳጅ እንደሚሆን አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋረገድ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል " በአዲሱ የትምህርት ፍኖታ ካርታ ግኝት መሰረት ዜጎች ከቅድመ አንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በግዴታ እንዲማሩ ለማስቻልና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን የተሳለጠ ለማድረግ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ይደረጋል " ብለዋል።

ፍኖተ ካርታውን ለማዘጋጀት ሲሞከር የትምህርት ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ሊያሳይ የሚያስችል ጥናት መደረጉን ገልፀው መንግስት ለትምህርት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ መልክ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/MoE-08-16 (ኢቢሲ)

@tikvahethiopia
* የታክስ ማሻሻያ

ገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንትንና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አሳወቀ።

ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ እንደሚደረጉ ታውቋል፡፡

የታክስ ማሻሻያው አላማ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የተሽከርካሪዎች ቁጥር በፖሊሲ ማዕቀፍ ከአካባቢ ደህንነት ጋር የሚስማማ ለማድረግ፣ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት የማያስከትል፣ በአየር ንብረትና በብዝሃ ህይወት ላይ ተጽእኖ የማያሳርፍ እና ታዳሽ የኃይል ምንጮችን በአግባቡ የሚጠቀም የመጓጓዣ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ለማስቻልም ነው፡፡

በታክስ ማሻሻያው መሰረት የኤሌክትሪክ የቤት አውቶሞቢሎችን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶ ሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ ደግሞ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ለማስቻል ነው።

በታክስ ማሻሻያው መሰረት (የቤት አውቶሞቢሎች) ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶ ሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

@tikvahethiopia
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩና የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢመርጀርሲ ሜዲካል ቴክኒሽያን ባለሙያ ደረጃ 4 ውስን ሰልጣኞችን ተቀብሎ የነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት አሳውቋል።

የመግቢያ መስፈርቶች ፦

1. ከ2011 - 2013 ባለው የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ውጤታቸው ለወንዶች ከ293 በላይ ለሴቶች ከ278 በላይ  ያመጡ፡፡

2. የ2014 ዓ.ም (በ2015 ዓ.ም ) ፈተና ለወሰዱ
ሀ.ለተፈጥሮ ሳይንስ  ተማሪዎች ለወንዶች ከ158 በላይ ለሴቶች ከ157 በላይ፤

ለ. ለሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ለወንዶች 149 በላይ ለሴቶች ከ145 በላይ ውጤት ያለቸው

3. ዕድሜ ከ30 ዓመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፡፡

4. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና  ማለፍ  የሚችል/የምትችል፡፡

5. ከፍለው ለመማር  የማይችሉ  መሆኑን   የሚገልጽ  ከሚኖሩበት ቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6. ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል

7. ስልጠናውን ለ20 ወራት በመደበኛ ፕሮግራም የሚሰጥ በመሆኑ ሙሉ ጊዜውን ለስልጠናው ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፡፡

የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 27 - መጋቢት  2/2015 ዓ.ም ድረስ ከላይ መስፈርቱን በሟሟላት በጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ። ( 👉 አድራሻውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ)

ለምዝገባ ሲመጡ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ትራንስክሪፕት፤ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ  በ8035 ወይም 0943302400 /0923514151 በስራ ሰዓት መደወል ይቻላሉ።

@tikvahethiopia
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩ የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጾ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም እንዳሉት ጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተጨማሪ ይመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethmagazine/18949

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ 7 ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች የሚፈጸሙ ቢሆንም በሪፖርት ውስጥ እንደማይካተቱ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በዓለም ባንክ ዕገዛ በሚከናወኑ ሰባት ፕሮጀክቶችን በሚመለከት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በነበረው የውይይት መድረክ ነው፡፡

ኮሚሽኑ ምንድነው ያለው ?

- በዓለም ባንክ ድጋፍ ከሚከናወኑ ፕሮጀክቶች የከተማና መሠረተ ልማት፣ የግብርና ዘርፍ፣ የትምህርት ጥራትን ጨምሮ ሌሎችም ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡

- ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በዓመት ሁለት ጊዜ ሪፖርት ይቀርባል ፤ በዚህም ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች #ነፃ መሆናቸው ተጠቅሶ ለዓለም ባንክ ሪፖርት ይደረጋል።

- ኮሚሽኑ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በቅርበት በመከታተል ሪፖርት እንዲያቀርብ ከዓለም ባንክ ጋር ስምምነት አለው ፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ከሙስናና ከብልሹ አሠራሮች የፀዱ ስለመሆናቸው የማረጋገጫ ሪፖርት ይቀርባል። ይሁን እንጂ ፕሮጀክቶቹ ክፍተቶች አሉባቸው ፤ ሌሎች ድጋፎች እንዳይቋረጡ በማለት ሪፖርቱ ሙሉ በሙሉ ወይም ከእነ ችግሮቻቸው አይቀርብም።

-  የዓለም ባንክ ብድርና ድጋፎችን የሚሰጠው የኮሚሽኑን ሪፖርት እንደ ቅድመ ሁኔታ በመውሰድ ነው።

- ለዓለም ባንክ ሪፖርት ማቅረብ የስምምነት ማሟያ ብቻ አይደለም፤ ገንዘብ ሚኒስቴርም ከባንኩ ለአገር ኢኮኖሚ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማምጣት ጭምር ነው።

- ዓለም ባንክ የኮሚሽኑን ሪፖርት እንደ መሥፈርትነት ይጠቀሜ ፤ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ነው።

- ዓለም ባንክ ሰባቱ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ድጋፍ ያደረገ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘሙ ፕሮጀክቶችና ሊጠናቀቁ የደረሱ አሉ።

- ፕሮጀክቶቹን በዋናነት የሚያስፈጽሙ ተቋማት ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ጥቆማዎችን ለመቀበልና ሪፖርቱን ለመላክ ይዘገያሉ፡፡

- ሙስና ሳይፈጸም በፊት ጥቆማዎች ሲደርሳቸው ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸውን፣ ሙስናን ለመከላከል ያለመፈለግና ተፈጽሞ ሲገኝ አስተማሪ ዕርምጃ መውሰድ ላይ ተቋማቱ ክፍተት አለባቸው።

- ሰባቱን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚያሠሩ ተቋማት ሙስናና ተያያዥ ጉዳዮችን ሪፖርት በጊዜው አያቀርቡም።

- ኮሚሽኑ ለዓለም ባንክ ሪፖርት ከማቅረብ በተጨማሪ፣ በሙስናና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተሳተፉትን ለሕግ ለማቅረብ በርካታ ሥራዎች እየሰራ ነው።

- ፕሮጀክቶቹ ወደ ታች መዋቅር ሲደርሱ በተለያዩ ምክንያቶች በጀቱ ይሸራረፋል።

- ፕሮጀክቱ በታችኛው መዋቅር ላይ በታሰበለት ጊዜ ያለመፈጸም፣ የካሳ ክፍያ በጊዜ ያለ መክፈል ሙስናና ማጭበርበር ወንጀል ላይ የታዩ ግለሰቦች አሉ።

- በተያዘው በጀት ዓመት በ6 ወራት ሪፖርት አፈጻጸም፣ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ምክንያት 357 ጥቆማዎች ለኮሚሽኑ ደርሷል። በዚህ ጥቆማ መሠረት ከ4.9 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሸሽ የነበረ ሀብት ወደ መንግሥት ካዝና ተመልሷል። ሕጋዊ ዕርምጃም የተወሰደባቸው አሉ። ከእነዚህ ውስጥ 11 ኃላፊዎች አስተዳደራዊ ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል ፤ ስድስቱ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው ተይዟል።

Credit : Reporter Newspaper

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
1287_2015_የኤክሳይዝ_ታክስ_አዋጅ_ማሻሻያ_.pdf
የተሻሻለው ኤክሳይዝ ታክስ . . .

አዲስ የተጨመሩ ፦

- የሞባይል አገልግሎቶች (ኢንተርኔት ፣ የድምፅና የፅሁፍ መልዕክት)፣  የገመድ አልባ ስልክ አገልግሎት፣ የገመድም ሆነ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎቶች 👉 የማስከፈያ ምጣኔ 5%

የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ዋጋቸው የቀነሰ ፦

➤ ስኳር ለህክምና ከሚውለው በስተቀር
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10%

➤ ማስቲካ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10%

➤ በቀጥታ ለምግብነት እንዲውል የተዘጋጀ ቸኮሌት እና ጣፋጭ ከረሜላዎች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 20%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10%

➤ ባህሪው ያልተለወጠ ኢቴል አልኮል
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 60%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10%

➤ ጨው
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 25%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 10%

➤ ኬሮሲን፣ ቤንዚን እና ናፍጣ ነዳጆች
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 30%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 15%

➤ ጨርቅና ልብስ
- የበፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 8%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 5%

➤ ምንጣፎች፣ ከጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ የወለል መሸፈኛዎች
- በፊቱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 30%
- አዲሱ የማስከፈያ ምጣኔ 👉 15%

በአዲሱ አዋጅ ነፃ የሆኑ የማይመለከታቸው ፦

📹 ቪድዮ መቅረጫ ወይም ማባዣ መሳሪያዎች፣ የቴሌቪዥን ስርጭት መቀበያዎች፣ ፎቶ ወይም ቪድዮ ካሜራ 👉 #ነፃ (ነባሩ ማስከፈያ ምጣኔ 10% ነበር)

ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የሆኑ ዕቃዎች ፦

የሚከተሉት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡

1. አውሮፕላን በዓለምዐቀፍ ትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለበት ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በጉዞ ወቅት የሚጠቀሙባቸው በነፃ የሚሰጡ ዕቃዎች፤

2. የዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱለር ሚሲዮኖች ወይም ዲፕሎማቶች አና ቆንስላዎች ወይም በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ የዲፕሎማቱ እና የቆንስላው ቤተሰቦች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዟቸው በዲፕሎማቶች መብትና ጥቅም ደንብ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፣

3. በመንግሥት ጥሪ መሰረት በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመርጃ እንዲውሉ ወደአገር የሚገቡ ዕቃዎች፣

4. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወይም የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወደአገር የሚያስገቧቸው ወይም ከአገር ውስጥ የሚገዙዋቸው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤

5. ከተሽከርካሪ በስተቀር ወደአገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፤

PDF : https://t.iss.one/tikvahethiopia/78549

@tikvahethiopia
#CBE

ኢትዮ-ዳይሬክት (EthioDirect)

• በሞባይል ስልክዎ
• የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን በመጠቀም
• ያለምንም ክፍያ
• ከውጭ ሀገራት 
• ወደ ሀገር ውስጥ 
• ቀጥታ ወደተቀባዩ ሂሳብ 
• ገንዘብ የሚልኩበት የሞባይል መተግበሪያ!

#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ 
=============
የEthioDirect  መተግበሪያን ከPlay Store ወይም ከApp Store በማውረድ የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ!

•  ለአንድሮይድ ስልኮች፡- https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
•  ለአይፎን ስልኮች፡- https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
#CBE

ባሻዎት ጊዜና ቦታ ይላኩ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ መላክ ይችላሉ፡፡

#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
#CBE
በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
===========
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
ልገሳዎን ቀጥታ ያድርሱ!
EthioDirect
***********
በኢትዮ-ዳይሬክት ለተቸገረ ወገንዎ ወይም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ልገሳዎን ቀጥታ ወደ ሂሳባቸው ይላኩ!
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም  App Store በማውረድ  አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመድ የሚላክልዎትን ገንዘብ
በኢትዮ ዳይሬክት ቀጥታ ወደ ሂሳብዎ ያስልኩ!
EthioDirect
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
=============
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
#CBE
በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
===========
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491